Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

1 3 8 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ማጠቃለያ

» ለቤተክርስቲያን የሚሽን ተሳትፎ ሦስት አሳማኝ ምክንያቶች አሉ።

» ከተሞች የዓለም የተጽእኖ ፣ የኃይል እና የመንፈሳዊ እንቅስቃሴ መቀመጫዎች ሲሆኑ ፣ ለተጨቆኑ ፣ ለተጠቁ እና ለድሆች እንደ መጠጊያ በመሆን የመንፈሳዊ እጣ ክፍላችን እና ውርሳችን ዋና ምስል እና ምልክት ናቸው ፡፡

ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ጥያቄዎች በዚህ በሁለተኛው ሴግመንት የቀረቡትን ሃሳቦች መለስ ብለህ ለመቃኘት እንዲረዱህ ነው። በዚህ ክፍል በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ከተማ ለሚሽን ስራ ስለሚኖረው ጠቀሜታ ሶስት እሳቤዎች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ከተሞች የተጽዕኖ፣ የኃይልና የመንፈሳዊ እንቅስቃሴ መቀመጫ መሆናቸው ነው፡፡ በከተማ ልማትና በፍልሰት ምክንያት ከተሞች ለተጠቁ፣ ለተጨቆኑና ለድሆች መጠጊያ በመሆን ላይ ናቸው፡፡ በመጨረሻም ከተማ የመዳረሻችንና የርስታችን የመጨረሻ ምስልና ማሳያ መሆኑን ግልጽ አድርጎ አስቀምጦልናል፡፡ እነዚህ ምክንያቶች የተጠናከረና በደንብ የተቀየሰ ከተሞችን የመድረስ ስትራቴጂን አስፈላጊነት አጉልተው ያሳያሉ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በቀረቡት ጥያቄዎች አማካኝነት ስለተነሱት ምክንያቶች ማእከላዊ የሆኑትን ነጥቦች ለመቃኘት ሞክር፡፡ 1. ዛሬ ላለው አጠቃላይ የሚሽን እንቅስቃሴ ኧርባን ሚሽን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን የሚጠቁሙ ሶስት ምክንያቶችን አቅርብ፤ ከሶስቱ ምክንያቶች ደግሞ የትኛው ይበልጥ አስገዳጅ ይመስልሃል? መልስህን አብራራ። 2. በኢየሱስና በሐዋርያት አገልግሎትውስጥ የከተማድርሻ ምን ነበር? መንግስቱን በማስፋፋት ስራቸው ውስጥ የኢየሩሳሌም ሚና ምን ነበር? በሮማ ግዛቶች ዘንድ የክርሰትና መልእክት የተስፋፋው እንዴት ነበር? ይህስ በተለይ በጳውሎስ ጉዞዎች ውስጥ እንዴት ታይቷል? 3. በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን የወንጌል ስራ ውስጥ እነዚህ የሮማ ግዛት ታላላቅ ከተሞች የተጫወቱት ሚና ምንድነው (ለምሳሌ ደማስቆ፣ አንጾኪያ፣ ፊልጵሲዩስ፣ ቆሮንቶስ፣ ተሰሎንቄ፣ አቴንስና ሮም)? 4. በጥንታውያኑ ከተሞች የነበሩ ችግሮች ዛሬ በዘመናዊው አለም ከተሞች ከሚታዩት ችግሮችና እድሎች አንጻር እንዴት ይነጻጸራሉ? ዛሬ ከተሞች በመጠን፣ በይዘት፣ በተጽዕኖና በህዝብ ብዛት እንዴት ይለያያሉ? ከምን አንጻር ነው ዘመናዊዎቹ ከተሞች የመንግስት፣ የትምህርት፣ የጤና-ክብካቤ፣ የመረጃ፣ የመዝናኛ፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ የህግ፣ የወታደራዊና የሃይማኖት ተቋማት ማዕከል ናቸው ማለት የምንችለው? 5. አንትሮፖሎጂስቶች ከተሞችን የመደቡባቸውን መንገዶች አስቀምጥ፤ ለእያንዳንዱ ምድቦች ትርጓሜና ምሳሌዎችን ስጥ፤ የባህል ከተሞች፣ የፖለቲካ የአስተዳደር ከተሞች፣ የንግድ ከተሞች፣ ታሪካዊ ከተሞችና ዋና ከተሞች።

መሸጋገሪያ 2

የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሽ

3

Made with FlippingBook - Online catalogs