Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 3 9

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

6. በዘመናዊው አለም የተጨቆኑ፣ የተጠቁና ድሆች ወደ ከተሞች እንዲሰደዱ የሚያደርጋቸው ምክንያት ምንድነው? ከምን አንጻር ነው ከተማነት “የዘመናዊው አለም ዋነኛ ባህሪይ ነው” ማለት የምንችለው? 7. መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለድሆች ያለውን ልብ አስመልክቶ የሚሰጠው ግልጽና የማያሻማ ምስክርነት ምንድነው? እግዚአብሔር ለድሆች ግድ ይለዋል ብለን ካሰብን ታዲያ በምን መልኩ ነው እግዚአብሔር በአሜሪካ ውስጠኛ ከተሞችን ጨምሮ ለአለም ታላላቅ ከተሞች ግድ እንደሚለው የምንመለከተው? 8. በምን መልኩ ነው የአዲሲቷ ከተማ ኢየሩሳሌም እውነታ እግዚአብሔር ከተማን እንደ መዳረሻችንና ርስታችን ማሳያነት መምረጡን የሚያሳየው? አዲሱቷ ኢየሩሳሌም ቀደም ብለው ከነበሩት ታላላቅ አለማዊ ከተሞች የምትለየው በምንድነው? 9. የጻድቃን መኖሪያ ከሆነችው ከአዲሲቷ ኢየሩሳሌም እና ከጠፋው አለም ከተሞች አንጻር ሲታይ የሚሽን ዋናው ግብ ምን መሆን አለበት? 10. በመጨረሻም ለምንድነው የከተማ አገልግሎትን እና ሚሽንን በጸሎታችን፣ በመስጠታችን፣ በመሄድና ሌሎችን በመላካችን ውስጥ መካካለኛ ማድረግ ያስፈለገን? በጌታ ቃል መሰረት በምንኖርበት አያሌ ፍላጎቶችና ጉዳቶች በሞሉበት ከተማዊ ማህበረሰብ መካከል ደህንነታችንን ማረጋገጥ የምንችለው እንዴት ነው? ከከተማ ፍላጎት አንጻር የቤተክርስቲያን ሚሽን ምንድነው? የቤተክርስቲያን ሚሽን በአምስት አጠቃላይ ተግባራት ሊጠቃለል ይችላል። ቀጥሎ የቀረቡበት ቅደም ተከተል ነጥቦቹ የሚኖራቸውን ቅደም ተከተል አያመለክቱም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ እያንዳንዳቸው በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ አንዳንድ ክርስቲያኖች አንዱን ነጥብ ከሌላው ይልቅ አጽንኦት በመስጠት እንደ አማራጮች ይመለከቷቸዋል፥ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ግን ምርጫ እንድናደርጋቸው አይፈልግም፡፡ 1. የተፈጥሮ ጸጋዎችን በባለአደራነት ማስተዳደር ይኖርባታል፡፡ ይህ ማለት እግዚአብሔር የፈጠራቸውንና ያበጃቸውን የተፈጥሮ ስርዓቶች በጥበብና በአግባቡ መጠቀምን እና አከባቢ ጥበቃንና ብክለት መቀነስን ማበረታታትን ያጠቃልላል፡፡ ቤተክርስቲያን ስስትን እና ከልክ ያለፈ ቁሳዊ ደስታን በማስቀረትና ለመጪዎቹ ትውልዶች ዘላቂ ሕይወት በማሰብ እግዚአብሔር የሰጠንን ህይወት መንከባከብ ይኖርባታል፡፡

3

Made with FlippingBook - Online catalogs