Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

1 4 0 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

2. ሰዎችን ያለ አድልኦና በየትኛውም ፍላጎቶቻቸው ማገልገል። የተፈናቀሉ በረሃብና በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን የመደገፍ ርህራሄያዊ ተግባር ይጠበቅባታል፡፡ የልማት መርሃግብሮች፣ የትምህርት ዘመቻዎች፣ የጤናና የቤት አቅርቦት ዘዴዎችም መቀየስ እንዲሁ። በተለይም አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ ሐዘንተኞች፣ ለአደጋ የተጋለጡ ህጻናትንና ቤተሰቦችን እንዲሁም ህግ ተላላፊዎችን፣ የመጠጥ የአደገኛ እጽና የቁማር ሱሰኞችን የማገልገል ልዩ ኃላፊነት ተስጥቷታል፡፡ 3. እውነት “በኢየሱስ እንዳለ” ምስክር መሆን ይኖርበታል (ኤፌ 4፡21)። ይህም እንደ አፖሎጄቲክስ፣ ቅድመ ወንጌል ስርጭትና ስብከተ ወንጌልን የመሳሰሉ ተግባራትን ያካትታል፡፡ ምስክር መሆን ማለት ሐዋርያት የሰበኩትን ወንጌል በቃል መናገርና ለሰው ልጆች ደግሞ ህይወትና ተስፋን ያመጣ ዘንድ የወንጌሉን ኃይል በአኗኗር መግለጥ ማለት ነው፡፡ 4. የእግዚአብሔር ፍትህ በህብረተሰቡ ውስጥ እንዲሰፍን ድርሻ መውሰድ አለባት። በተለይም ደግሞ ቤተክርስቲያን እንደ ፍቺ፣ ውርጃ፣ ልቅ ወሲባዊ ግንኙነቶች፣ ፖርኖግራፊ፣ የሴቶችና ህጻናት ጉልበት ብዝበዛ እና እንደነዚህ ያሉትን የቤተሰብ አንድነት ጠላቶች በመዋጋት ልትቆም ይገባታል፡፡ ለቤት አልባዎች፣ ላልተማሩ፣ ለስራ አጦችና ምግብ ለሌላቸው ወገኖች ህይወት መሻሻል አማራጭ ፖሊሲዎችን ማቅረብ ይኖርባታል፡፡ ለሰብዓዊ መብቶች መሟገትና እና በሰዎች መካከል የሚደረግን አድልኦም መቃወም ይኖርባታል፡፡ በመጨረሻም የጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን የማይገታ ግንባታና በበለጸጉትና በድሃ ሃገራት መካከል የሚካሄደውን የጦር መሳሪያ ሽያጭ መቃወም ይኖርባታል፡፡ 5. በዚህ በተበላሸ፣ በተጨነቀና ተስፋ በቆረጠ አለም ውጥ በእርቅና በነጻነት የሚኖር ማህበረሰብ ምን ማለት እንደሆነ በተግባር የማሳየት ኃላፊነት አለባት፡፡ ይቅርታን በመተግበር፣ ሐብቶችን በማከፋፈል፣ ጭፍን ጥላቻና ጥርጣሬን በማስወገድ እንዲሁም ስልጣንን በበላይነትና በቁጥጥር መንፈስ ሳይሆን በአገልጋይነት ስሜት በመጠቀም የእግዚአብሔርን የጸጋ ሁኔታ ለሌሎች ለማሳየት ተልዕኮ ተሰጥቷታል፡፡ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ሰላምና ፍትህ የሚገዛበትን አዲስ ስርዓት ለመፍጠር የእግዚአብሔር አላማ ምልክትና ወኪል መሆን አለባት፡፡

3

~J. A. Kirk. “Missiology.” The New Dictionary of Theology. S. B. Ferguson, ed. (electronic ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2000. p. 435.

Made with FlippingBook - Online catalogs