Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
1 4 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
³ በኢየሱስና በሐዋርያት ዘመን በነበሩ ከተሞች ውስጥ የነበሩ ተመሳሳይ ችግሮች እና እድሎች አሁን ባሉት ዘመናዊ ከተሞች ውስጥም የመታየታቸው ዕውነታ ግልፅ ነው፡፡ እነዚህ ዘመናዊ ከተሞች በመጠን፣ በስፋትና በህዝብ ብዛትም ታላላቅ ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ከተሞች የመንግስት፣ የትምህርት፣ የጤና-ክብካቤ፣ የመረጃ፣ የመዝናኛ፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ የህግ፣ የወታደራዊና የሃይማኖት ተቋማት በመሆን ያገለግላሉ፡፡ ³ አንትሮፖሎጂስቶች ከተሞችን ከሚሰጡት አገልግሎት አንጻር በትኩረታቸውና በአይነታቸው ለይተው ያስቀምጣሉ፡፡ የባህል፣ የፖለቲካና የአስተዳደር፣ የንግድ፣ የኢንዱስትሪ፣ ታሪካዊ ወይም ዋና ከተማ በመባል ተከፍለዋል። ³ እግዚአብሔር ለድሆች ስላለው ልብ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ በመነሳት በአሁን ወቅት ከተሞች ለተጠቁት፣ለተጨቆኑት እና ለድሆች እንዴት እንደ ሚስብ ኃይል እንደሚያገለግሉ ይታያል፡፡ ሌላው ደግሞ እግዚአብሔር ስለ ድሆች ግድ የሚለው ከሆነ አሜሪካ ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና በድህነት ስለሚሰቃዩት ከተሞች ግድ ይለዋል ማለት ነው ስለሚለው ክርክር ግንዛቤ እንጨብጣለን፡፡ ³ ከተማ የመዳረሻችንና የርስታችን ምስል እና ምሳሌ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ማጠቃለያ ይሰጡናል፡፡ ይህም እግዚአብሔር ስለሚገኝባትና ኢየሱስም እንደ ሁሉ ጌታ የሚደነቅባት አዲሲቱ ኢየሩሳሌምን እንዲሞሉ ነው (የእግዚአብሔር የመጨረሻ የከተማ ተሃድሶ ፕሮጀክት)፡፡ ³ የሚሽን ዋናው ግብ የአለምን ከተሞች የአማኞች ሁሉ እናት የሆነችውን አዲሲቷን ኢየሩሳሌምን እንዲሞሉ መማረክ ነው (የእግዚአብሔር የመጨረሻው የከተማ ተሃድሶ ፕሮጀክት)፡ ³ ከተማ በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በዘመናዊው አለም ካለው ጠቀሜታ አንጻር በሚሽን አገልግሎት ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ አሁን አብረውህ ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን ስለ ከተማና ዛሬ ከተማ በሚሽን ውስጥ ስለሚኖረው ሚና የምትወያይበት ሰአት ነው፡፡ ይህ አንተ ስለ ከተማ እና ስለ ሚሽን ከተማርከው ትምህርት አንጻር ያለህን ዕይታ የምትወያይበት እድል ነው - እዚህ ጋር ቅድሚያ የሚሰጠው ለጥያቄዎችህ ነው፤ አንተ ያሉህን ጥያቄዎችና ጉዳዮች ቀጥሎ ከቀረቡት ጥያቄዎች አንጻር ለመመልከት ሞክር: • ለከተማ ያለህ አመለካከት ምን ይመስላል? - የት አደግህ? ቤተሰብህና የኖርክበት ማህበረሰብ ከተማን የሚመለከቱት እንዴት ነው? ዛሬ ስለከተማ ያለህን ስሜት እንዴት ትገልጸዋለህ? • በሰዎች አመጽ፣ ምንዝር፣ አለመገዛትና እብሪት እና በዘመናዊቷ የአሜሪካ ከተማ መካከል ያለውን ግንኙነት መረዳት ላንተ ቀላል ነው? በቀደመው ጊዜ ጥንታዊ ከተሞችን ከኃጢአታቸውና ከልባቸውድንዳኔ የተነሳ እንደቀጣቸው እግዚአብሔር አሁንም ዘመናዊቷን የአሜሪካን ከተማ የሚቀጣ ይመስልሃል? አብራራ።
3
የተማሪው ትግበራና አንድምታዎች
Made with FlippingBook - Online catalogs