Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 4 3

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

• በትምህርታችን እንደተመለከትነው ከእግዚአብሔር መኖሪያነትና ከበረከት ጋር የምታዛምደው ከተማ ይኖራል? ይህ ለአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ብቻ የሚባል ነገር ነው ወይስ ዛሬ ባሉት ከተሞቻችንም ውስጥ ይህን ለማየት መጓጓት እንችላለን? አብራራ። • በአንድ ሀገር ውስጥ የፈለከው ከተማ ውስጥ መኖር ብትችል የት መኖር ትፈልጋለህ እና ለምን? ለከተሞች ካለህ የተዛባ ግንዛቤ አንጻር መመልከት የማትችላቸው (ጥሩም ይሁን መጥፎ) ነገሮች ምንድናቸው? • በከተማዎች አከባቢ ስለ ኧርባን ሚሽን፣ ቤተክርሰቲያን ተከላና ደቀመዛሙርት ስለማፍራት ታስባለህ? ደሀ የህብረተሰብ ክፍሎችን በእነዚህ አከባቢዎች ለማገልገልም ወይም ላለማገልገል ሸክም ወይም የተዛባ አመለካከት አለህ? • በከተማ የሚኖሩ ሰዎችን እንዴት ታያቸዋለህ? የጭቆና ተጠቂዎች ናቸው ወይስ ዝም ብለው የቸልተኝነታቸውንና የስራቸውን ውጤት እየተቀበሉ ነው? መልስህን አብራራ። • አንዳንድ በአሜሪካ ያሉ ክርስትያኖች የራሳቸው ቋንቋና ባህል ለሌላቸው ቁጥራቸው እያደገ ለመጣው የታችኛው የማህበረሰብ ክፍሎች የሚጨነቁት ለምን ይመስልሃል? ለምንድነው ብዙዎች የከተማን ነዋሪዎች ከሞራላዊ ዝቅጠት እና ግለሰባዊ ኃላፊነት ከማጣት አንጻር እንደሚሰቃዩ አድርገው ሲነቅፉ የሚሰሙት? • ቀጣዩን ዓረፍተ ነገር አጠናቅ - “ወደ ከተማ ሄጄ ወንጌል ለመስራት ከመነሳቴ በፊት ጌታ ራሱ….” • ዛሬ ባሉ ከተሞች ላይ እግዚአብሔር ራሱ ፍርድን እንደሚያመጣ ተመኝተህ ታውቃለህ? አብራራ፡፡ ዛሬ ዘመናዊዎቹ ከተሞች በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን ማዋረድና መመለስ ቢፈልጉ እግዚአብሔር ለነነዌ ሰዎች በሰጠው መልኩ ምላሽ መስጠት አለባቸው ብለህ ታስባለህ? • ብዙዎች ከተማን ለሽርሽርና ለእረፍት ጊዜ እንደሚጎበኙ መዝናኛ ስፍራዎች ብቻ ይመለከቷቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከከተሞችና ከነዋሪዎቻቸው ጋር ያለህን ግንኙነት እንዴት ትገልጸዋለህ? በከተማ ውስጥ ለማገልገል ያንተ የግል ኃላፊነትና ጥረት ምንድነው? ለማገልገል ያንተ የግል ጥሪና ኃላፊነት ምንድነው? • ለአለም ከተሞች ትጸልያለህ? ካልሆነ ለምን? ለከተማህስ ትጸልያለህ - ለመሪዎቿና ለገዢዎቿ፣ ለህዝቡና ለፍላጎቶቻቸው፣ ለእድሎችዋና ለመንፈሳዊ ረሃብ? ከእንግዲህ ወዲያ በከተማ ላለው ማህበረሰብ በትጋት ለመጸለይ እንዴት መጀመር ትችላለህ? በአካባቢህ ኧርባን ሚሽንን ትደግፋለህ? የት? (አባሪው ውስጥ “እግዚአብሔር ይነሳ” የሚለው ተመልከት)። • እግዚአብሔር ለዘላለም እንኖርት ዘንድ ከተማን እያዘጋጀልን መሆኑ ያስደንቅሃል? በምላሽህ በተቻለ መጠን እውነተኛ ሁን፤ ሚሽን የአማኞች ሁሉ እናት የሆነችው አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን ይሞሉ ዘንድ የአለምን ከተሞች መማረክ መሆኑን ትገነዘባለህ?

3

Made with FlippingBook - Online catalogs