Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
1 4 4 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
CASE STUDIES
ክህነትን መጠበቅ ወይስ ማመቻመች? ቤተክርስቲያን ለከተማው እንደ ካህን የሚለው ሃሳብ የይሁዳ ሰዎች በባቢሎን ለግዞት ከመወሰዳቸው በፊት እግዚአብሔር በነብዩ በኤርሚያስ በኩል በሰጠው መመሪያ ውስጥ ይገኛል፡፡ በባቢሎን ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ቤተሰቦቻቸው በውስጥዋ እንዲያሳድጉና ደህንነትዋንም እንዲሹ እግዚአብሔር አዝዟቸዋል፡፡ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ላስማረክኋቸው ምርኮኞች ሁሉ እንዲህ ይላል፦ቤት ሠርታችሁ ተቀመጡ፥ አታክልትም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ፤ ተጋቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፥ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ። በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ (ኤር 29፡ 4-7)። ይህ የባቢሎናውያን የምርኮ ጉዳይ አማኞች ስለ ክፉና ፈሪሃ እግዚአብሔር ለሌለባት ከተማ መውሰድ ስለሚኖርባቸው አቋም ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ከተቃውሞና ችግር ከማስነሳት ይልቅ በዚያው ከተማ ሆነው ቤተሰቦቻቸውን እንዲገነቡና እንዲያሳድጉ አልፎም ተርፎም እንዲባዙና እንዲያድጉ እግዚአብሔር ሲቀሰቅሳቸው እናያለን፡፡ የከተማዋን ደህንነት ይሹ ዘንድ የተሰጣቸው ትእዛዝ አወዛጋቢ ነው፤ የእግዚአብሔር ህዝብ ደህንነት በእግዚአብሔር ፊት የጣዖት አምልኮና የአመጽ ምልክት ከሆነችው ከባቢሎን ደህንነት ጋር በቀጥታ እንዴት ሊገናኝ ይችላል? እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በቀጥታ የሰጠው መመሪያ ከከተማ አንጻር ስለ እግዚአብሔር ህዝብ ምንነት ምን ይነግረናል? ለዛሬውስ እኛ ከዚህ ምን እንማራለን? ባሉበት መቀመጥ ወይስ መውጣት እና መሄድ? ዋናውና እያደገ የሚገኘው የከተማው የአፍሪካ አሜሪካውያን ቤተክርስቲያን አሁን በሚገኝበት ስፍራ መቆየት ወይም ከፍ ወዳለው የህብረተሰብ ክፍል ከፍ ማለት በሚሉት ሃሳቦች መካከል ለውሳኔ ተቸግሯል። ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝና ለመንግስቱ መስፋት በተሰጠው ድንቅ መጋቢያቸው አማካኝነት ቤተክርስቲያኒቱ በቁጥር፣ በተጽእኖ እና በሃብትም እድገት አሳይታለች። ብቁ እና ትሁታን መሪዎችንና ለማገልገል የተሰጡ ምዕመናንን ይዛ ቤተክርስቲያኒቱ ስፍራ መቀየር እንዳለባት መሪዎቿ አጽንኦት ሰጥተው እያሰቡበት ይገኛሉ። በይዞታቸው ሁኔታ ምክንያት ነገሮች ተዘግተውባቸዋል? አሁን ባላቸው ይዞታ ላይ ግንባታ ማካሄድ አልቻሉም። በአካባቢው ማህብረሰብ ዘንድ በጣም ችግረኛ አባሎቻቸውን ማዕከል ያደረጉ በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ፤ ቤተክርስቲያኒቱም ለበርካታ አመታት በዚያ ስፍራ ነበረች፥ አሁን ግን እውነተኛ ተሃድሶ በማድረግ ላይ ትገኛለች። የቤተክርስቲያኒቱ መጋቢ ከተማ እና አገር አቀፍ ተቀባይነቱ እና ተጽዕኖ ፈጣሪነቱ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች ስፍራ መቀየር እና ግንባታ ማካሄድ የአገልግሎት እድሎቻቸውን እንደሚያሰፋላቸውና ከተማውን ይበልጥ በትጽዕኖ ለማገልገል እንደሚረዳቸው ያምናሉ። በአንጻሩ ቤተክርስቲያኒቱ አሁን ላለችበት ዝቅተኛ የከተማው አካባቢ እንደ ጨው እና እንደ ብርሃን ማገልገሏን የሚያዩት ሌሎች ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱ እጅግ አስፈላጊ ከሆነችበት ስፍራ ለቅቃ ምቹና “ደህንነቱ አስተማማኝ” ወደሆነ ስፍራ መሄዷን ለመቀበል ይቸገራሉ። የቤተክርስቲያኒቱን መጋቢ እና መሪዎች ማድረግ ስላለባቸው ውሳኔ የማማከር እድል ቢገጥምህ ምን አይነት መርሆዎችና ምልከታዎችን ታካፍላቸው ነበር?
1
3
2
Made with FlippingBook - Online catalogs