Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 4 5

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

እንደዚያ አይነቱ መልካም ዜና የሚያበረታታ አይደለም - ምንም የተለወጠ ነገር የለም በዋነኛው የመካከለኛው ምዕራብ ከተማ ውስጥ በጣም ድሃና ገለልተኛ በሆነው አካባቢ ተከታታይ የወንጌል ስራዎችን የጀመረች ቤተክርስቲያን ውስጥ ግጭት ተቀሰቀሰ። ሌሎች አብያተክርስቲያናት እና ሚኒስትሪዎች መሄድ ወደማይፈልጉባቸውና ወደሚፈሯቸው ቦታዎች እንዲሄዱ የቤተክርስቲያኒቱ መጋቢ ጥልቅ በሆነ መነሳሳት የወንጌል ስርጭት ቡድን አሰልጥኖ ወደ መኖሪያ አፓርትመንቶች ልኳቸዋል። የአብዛኛዎቹ የአፓርትመንቱ ነዋሪዎች አቀባበል በጣም አስገራሚ ነበር - የህንጻውን ስራ አስኪያጆች ጨምሮ፤ በመሆኑም ክፍት የሆኑ የህንጻውን ክፍሎች እንዲጠቀሙ ፈቅደውላቸዋል። በአነስተኛ ወለድና ክፍያ ቡድኑ እዚያው የራሱን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመጀመርና ፍሬውን ለማየት ብዙ ጊዜ አልወሰደም - ይካፈሉ የነበሩ የተወሰኑ ግለሰቦችና ቤተሰቦች ወደ ክርስቶስ መጥተዋል። በአንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ምሽት አንድ ተጋባዥ እንግዳ እና የአፓትመንቱ ነዋሪ ስለ ወንጌል ስርጭት ቡድኑ እና ስለላካቸው ቤተክርስቲያን ስሜታቸውን ሲከፋፈሉ እንዲህ ብላለች:- “እኔ እናንተን አላውቃችሁም፥ እውነት ለመናገር ጥሩ ሰዎች ትመስላላችሁ፤ ነገር ግን እንዴት እግዚአብሔር ስለ ኢየሱስ የምስራቹን እንድንናገር ወደዚህ ስፍራ ልኮናል እንደምትሉ አይገባኝም ምክንያቱም በአካባቢው ላይ ምንም የተቀየረ ነገር የለም። ዱርዬዎች አሁንም እያስቸገሩ ነው፣ ስራም የትም የለም እና ሁላችንም እየታገልን ነው የምንኖረው። እንግዲህ እንዴት ነው ከአካባቢያችን ችግር ሳታድኑን ስለመዳን ብቻ ትነግሩን ዘንድ እግዚአብሔር የላካችሁ? እኔ ይሄ ሊገባኝ አይችልም። ይህ አይነቱ የምስራች የሚያበረታታ አይደለም - እዚህ ምንም የተለወጠ ነገር የለም!” የዚህችን የተወደደች እህት ድምዳሜ እና ጥያቄ የምትመልሰው እንዴት ነው? በአሜሪካ ውስጣዊ ከተማ ላይ የተሰራ የወንጌላዊያን ሴራ (በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ) በጣም ታዋቂ የሆነ የክርስቲያን ድህረምረቃ ትምህርት ቤት ሙስሊሞችን፣ ቻይናውያንን እና ስላቪኮችን ጨምሮ ያልተደረሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን በአለም ዙሪያ ለመድረስ እንቅስቃሴዎችን ያደራጅና በገንዝብም ይደግፍ ነበር። በርካታ ነጻ የትምህርት እድሎች የአገልግሎት ሸክም ላላቸው ተማሪዎች የተሰጡ ሲሆን በየመስኩ በመላው አለም ይሰማሩ ዘንድ ትምህርት ቤቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ መንፈሳዊ ሰራተኞችን አሰልጥኖ አሰማርቷል። ይሁን እንጂ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ትልቁ የድሆች መንደር (ጌቶ) የ ሃያ አምስት ደቂቃ ጉዞ ርቀት ላይ ይገኛል። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከደረጃ በታች በሆኑ ቤቶች፣ ግጭት በነገሰበት፣ ዱርዬዎችና ሱሰኞች በሞሉበትና ክርስቲያኖች ደፍረው ገብተው በማያገለግሉበት ሰፈር ውስጥ ይኖራሉ። ለውጭ ሚሽን በሚደረገው ከፍተኛ የሆነ የጊዜና የገንዘብ ድጋፍ እና ለአካባቢያዊው ሚሽን ስለሚደረገው ያልተመጣጠነ ድጋፍ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ተጠይቀው ሲመልሱ ለአሜሪካ የከተማ ድሆች የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት ምን ያህል አስቸጋሪና ከባድ እንደሆነ በማዘን ገልጸዋል። ከሂውስተን ይልቅ ሆንዱራስ፣ ከጄርሲ ከተማ ይልቅ ጃማይካ ውስጥ ለሚደረግ ስልጠና የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት እንደሚቀልል ጠቅሰዋል። ለከተማው ፍላጎትና አቅም ወንጌላውያኑ ያሳዩትን ቸልተኝነት እንዴት ትገልጸዋለህ? ለትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ለአለማቀፍ አገልግሎቶች ጠቀም ያለ ድጋፍ ማሰባሰብ ቀላል በአንጻሩ ደግሞ የአሜሪካ የከተማ ሰራተኞችን ለማገዝ የሚሆንን ድጋፍ ማግኘት ደግሞ የማይቻልበት ደረጃ ላይ የደረሰው ለምንድነው?

3

3

4

Made with FlippingBook - Online catalogs