Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 4 9
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
በዚህ ትምህርት የጥንታዊት ከተማ ጽንሰ ሃሳብ ከተማዋ ካላት የራስ ትምክህት፣ ዕብሪት እና እግዚአብሔር ላይ የሚደረግ አመጽ እንዴት እንደሚተሳሰር እና እንዴት እግዚአብሔር የከተማን ጽንሰ ሃሳብ ለራሱ አላማ እንደቀየረውና ከተማን እንዴት የመሸሸጊያ፣ የንስሐና የተሃድሶ ምልክት እንዳደረጋት ተምረናል። ቤተክርስቲያን በኧርባን ሚሽን ውስጥ ለምን መሳተፍ እንዳለባት ሶስት ወሳኝ ምክንያቶችን አይተናል። ከተሞች የተጽእኖ፣ የሃይል እና የመንፈሳዊ እንቅስቃሴ መቀመጫዎች፤ ለተጨቆኑ፣ ለተጠቁና ለድሆች መጠጊያ፤ እና በስተመጨረሻም ከተሞች የመንፈሳዊ መዳረሻችንና ርስታችን ምስል እና ምልክቶች ናቸው። በቀጣዩ ትምህርታችን ትኩረታችንን ከከተማ ስለ ሚሽን መሰረቶች በምናደርገው የመጨረሻ የጥናት ጽንሰ ሃሳብ ወደሆነው ወደ ድሆች ጽንሰ ሃሳብ እንሸጋገራለን። የድሃ እና የሚሽንን ጽንሰ ሃሳብ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው የሻሎም ወይም ምሉዕነት ጽንሰ ሃሳብ መነጽር እንመለከታለን። እንደ የያህዌ የቃልኪዳን ህዝብ እግዚአብሔር የእስራኤልን ህዝብ ለኪዳኑ በታማኝነት ይኖሩ ዘንድ ጠርቷቸዋል። ይህም ሲሆን ድህነትና ግፍ በፍትህ እና ጽድቅ ይተካሉ። ይህ ስልጣን ዛሬም የእግዚአብሔርን ህዝብ ንድፍ ይወክላል። ኢየሱስ ጌታ እና ዛሬ መንግስቱን የሚያስፋፋው የኪዳን ህዝብ የቤተክርስቲያን ራስ ነው። እግዚአብሔር ህዝቡን በሻሎም ይኖሩ ዘንድ እና የርሱን ፍትህ እና ምህረት ለመንግሥቱ አባላትና ለአለም በተለይም በእኛ ዘንድ ላሉ ለተጨቆኑና ለድሆች ይገልጡ ዘንድ ጠርቷቸዋል።
ለቀጣዩ ትምህርት መዘጋጀት
3
Made with FlippingBook - Online catalogs