Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
1 4 8 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
“ስለዚህም ምንም እንኳን እኛ ድንዛዜአችንን የማናስተውልና ያልነቃን ብንሆንም እርሱ ግን ስለኛ ይነሳል፤ ይጠብቀናል ከዚያም አልፎ ሳንጠይቀው እንኳን ይረዳናል፤ ፍላጎታችንን ያለማቋረጥ ለእርሱ ማስታወቃችን በጣም አስፈላጊ ነው። በመጀመሪያ ልባችን ሁልጊዜ በጣም ጠንካራ በሆነ ውስጣዊ ፍላጎት እርሱን ይሻ ዘንድ፥ እርሱን በመውደድና በማገልገል በነገር ሁሉ ወደርሱ መጣበቅ ይሆንልን ዘንድ፤ በሁለተኛ ደረጃ ምኞቶቻች፣ ፍላጎቶቻችን፣ የምናፍርባቸው ነገሮች ሁሉ በፊቱ እንድናኖርና ልባችንንም በፌቱ እናፈስ ዘንድ። በመጨረሻም ከምስጋና ጋር እርሱ ያዘጋጀልንን በረከት ሁሉ ከእጁ እንቀበል ዘንድ፥ ጸሎቶቻችንም ሁሉ ከእርሱ እንደሚወጡ እናስተውል ዘንድ ነው።” ~John Calvin. Institutes of the Christian Religion. Trans. of Institutio Christianae Religionis. Reprint, with new introd. Originally published: Edinburgh: Calvin Translation Society, 1845-1846. (III, xx, 3). (electronic ed.). Oak Harbor, WA: Logos Research Systems, Inc., 1997.
ልብህን ወደ እግዚአብሔር አንስተህ ለራስህና አብረውህ ለሚማሩ ሁሉ ጸልይ፥ ስለ ሚሽን፣ ስለ ከተማ እና ስለ ጥሪህ ወደ ጠለቀና ግልጽ ወደሆነ መረዳትና የቃሉ ፈቃድ ይመራህ ዘንድ ጸልይ።
3
ASSIGNMENTS
ዕብራውያን 11:13-16
የቃል ጥናት ጥቅስ
ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።
የንባብ መልመጃ
እንደተለመደው ለሳምቱ የተሰጠውን የትምህርት ማጠቃለያ የሰራህበትን የንባብ መልመጃ ይዘህ መቅረብ ይጠበቅብሃል። በተጨማሪም ለምትሰራው ኤክሴጄቲካል ፕሮጀክት ምንባብ መርጠህ፥ ለሚኒስትሪ ፕሮጀክትህ ደግሞ ፕሮፖሳል አዘጋጅተህ አቅርብ።
ሌሎች የቤት ስራዎች
Made with FlippingBook - Online catalogs