Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 5 3
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ክርስቲያን ሚሽን እና ድሆች
ት ም ህ ር ት 4
የትምህርቱ አላማዎች
ሃያል በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን ! የዚህን ትምህርት መጽሀፍ ካነበብክ፣ ካጠናህ፣ ውይይት ካካሄድክና ወደ ተግባር ከቀየርከው በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው የሻሎም ወይም ምሉዕነት አንጻር የድሃ አደግን ጽንሰ ሀሳብ መተርጎም ትችላለህ፡፡ ሻሎም የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም ከእግዚአብሔር ጋር እና አርስ በእርስ ባለ ህብረት ውስጥ ያለ የሰው ማህበረሰባዊ ሙሉነት ማለት ነው፡፡ • የሻሎምን አካላት ማለትም የጤናና ደህንነት እና ጥበቃን በጎረቤት መካከል ያለን መልካም ግንኙነት፤ ብቃትን ብልጽግናና የቁሳዊ ፍላጎት መሟላትን እና የክፋትና የግጭትን አለመኖር፤ እውነተኛ ሰላምን ጨምሮ ያሉትን ልምምዶች መዘርዘር ትችላለህ፡፡ ይህም ሰላምን እንደ እግዚአብሔር ቸርነት የተደረገ ስጦታን ይመለከታል፤ የሰላም ንጉስ ከሆነው ከመሲሁ መምጣት ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ • ድህነት እንዴት የእግዚአብሔርን ሻሎም መካድ እንደሆነ፤ የእርሱ በረከት ድህነትን ለመከላከል እንደሆነ፤ ለኪዳኑ ህዝብ የተሰጡት ትዕዛዝ በያህዌ ህዝብ ዘንድ ፍትህና ጽድቅን ለማረጋገጥ የተቀየሱ መሆናቸውን እና ለትእዛዛቱ የሚያሳዩት ታማኝነት እንዴት እስራኤላውያን ቃሉን እሰከታዘዙትና ፍቃዱን እሰከተከሉ ድረስ መልካም ይሆንላቸው ዘንድ እንደተፈቀደላቸው ማብራራት ትችላለህ፡፡ • እግዚአብሔር ከድሀ አደጎች ጋር እንዴት እንደሚቆም፥ ማለትም የሚጨቁናቸው ይቀጣ ዘንድ ድሆችን ከመሬት አንስቶ መባረኩን እና ለእርሱ የተጨቆኑት፣ የተጠቁትና ለድሆች ግድ እንደሚለው እንዲሁ እነርሱ ደግሞ ግድ ይላቸው ዘንድ መፈለጉን ትገነዘባለህ፡፡ የዘጸዓቱ ክስተት እንዴት እግዚአብሔር ከድሆችና ከተጨቆኑት ጋር እንደሚቆም ያሳያል፤ የቅድስና ነጸብራቅ፣ የፍትህና የምህረት ምሳሌ እና ለአህዛብ መልክት እንዲሆን ለጠራው የኪዳን ህዝብ የፍትህ ልቡን በማሳየት ተገልጧል፡፡ • የተፈጥሮ አደጋና ጥፋት (ለምሳሌ ረሀብ፣ ድርቅ፣ አውሎነፋስ ወ.ዘ.ተ)፣ የግል ስንፍናና ስልቹነት (ለምሳሌ መጥፎ ውሳኔዎች፣ ስለ-ምግባር የጎደለው ባህርይ፣ ስራ ፈትነት፣ ልበ ደንዳናነት፣ ወ.ዘ.ተ) እና ጭቆናና ግፍ (ለምሳሌ በደል፣ ብዝበዛ፣ የደሞዝ ማጭበርበር ወዘተ) ጨምሮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የድህነት መንስኤዎችን ማንሳት ትችላለህ፡፡ ደሀ አደግ የሚለው ቃል በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ የተለያየ ትርጓሜ ከሚሰጣቸው ጽንሰ ሀሳቦች ጋር ተያይዞ ይገኛል፡፡ ከነዚህም ውስጥ “መበለት”፣ “ወላጅ አልባ” እና “እንግዳ” የሚሉት ይገኙበታል፡፡
4
Made with FlippingBook - Online catalogs