Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
1 5 4 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
• ድሆችን እንደ ምስክሮች በቸርነትና በፍትህ ከመያዝ አንጻር እግዚአብሔር ለኪዳን ህዝቡ የሰጠውን መስፈርት መዘርዘር ትችላለህ፡፡ ይህም በህግ የተካተተ የፍትህ ጉዳዮችን፣ ለድሆች የሚደረግ ልዩ አቅርቦት፣ ያለ እድሎ የሚደረግ በሃቅና በትክክለኝነት ላይ የተመሰረተ፣ ሁሉም ጉዳዮች መመዘኛዎችና ሽግግሮች በፍትሀዊ መንገድ የሚካሄድበት እንዲሁም ድሆች ከእርሻችና ከወይን ምርቶች በየሰባት አመቱ ድርሻ የሚያገኙበት ነው፡፡ • የእግዚአብሔር ህዝቦች ድሆችን መቅረጥ መከልከላቸውን፣ ለእለታዊ ስራ ተገቢውን ክፍያ መስጠት (ማለትም ደሞዝ መከፈል ያለበት በእለቱና ያለምንም ጭቆናና ማጭበርበር መካሄድ አለበት)፣ ድሆችን የመቀበልን ልምምድ (በተዘረጋ እጅ) እና ሃብቶችን ለድሆች ማስቀመጥ (በህብረተሰቡ ውስጥ የሚገኙ እጅግ ችግረኛ ለሆኑ ሰዎች ከአስራትና ከመባ ድርሻ ማካፈል)፡፡ ድሆች በኢዮቤልዩ አመት በሚካሄዱ በሁሉም አይነት ክብረበአላት ላይ መሳተፍና ንብረታቸውን ማደስ መቻላቸውን ጨምሮ ያሉ መመዘኛዎችን መዘርዘር ትችላለህ፡፡ • የእግዚአብሔርን የኪዳን ማህበረሰብ መለኪያዎችና አንድምታዎች መዘርዘር ትችላለህ፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ በሚያደርጉት ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ከድሃ አደጎች ጎን መቆሙን ማንጸባረቅ ይኖርባቸዋል፤ እግዚአብሔር በዘጸአት ካደረገላቸው ነጻ መውጣት በመነሳት ከሰዎች ሁሉ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ሁሉ የጌታን ሰላም ያሳዩ ዘንድ ነው፡፡ • የኢየሱስ ቤተክርስቲያንን ማግኘት በእግዚአብሔር ህዝቦች መካከል ይህን ሰላም ለማሳየት የተጠራው አዲሱ የእግዚአብሔር የኪዳን ማህረበሰብ እንደሆነ ማስረጃ መስጠት ትችላለህ፡፡ • የኢየሱስ መሲህነት በእርሱ ትኩረት፣ ጥሪ፣ አገልግሎትና አላማ ውስጥ ለሚገኙና ለተጨቆኑ ፈውስን ለድሆች ወንጌልን በመስበክ ውስጥ እንዴት እንደጀመረ ማብራራት ትችላለህ፤ ይህም ለድሆች ወንጌልን በመስበክና ፍትህን በማድረግ በመጥምቁ ዮሐንስ በኩል መሲህነቱ ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም ድሆችን ከተንከባከቡበት መንገድ በመነሳት እንዴት ለሌሎች መዳን እንደሆነና ከሁሉ ከሚያንሱት (ከተራቡት፣ ከተጠሙት፣ ከአመጸኞች፣ ከታረዙት፣ ከታመሙትና ከታሰሩት) ጋር ያለመከልከል እንዴት እንደሆነ ማሳየት ትችላለህ፡፡ • የክርስቶስ የመንግስቱ ማህበረሰብ በሆነችው በቤተክርስቲያንና በዚህ የመንግስቱ ማህበረሰብ ውስጥ ስላለች ምህረትንና ፍትህን የመግለጥ ድረሻ ያላቸውን ግንኙነት ማሳየት ትችላለህ፡፡ ይህም ማለት የተጠራቸው በአለም ውስጥ የክርስቶስ አካል ለድሆች ወንጌልን ለመስበክ እና ለድሆች በሚደረግ ፍትህ አማካኝነት ስለሚመጣው ዘመን አዲስ ህይወት ማሳያ ለመሆን ነው፡፡ በተጨማሪም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በታጠቀችው የቤተክርስቲያን ህይወት እና ተልዕኮ አማካኝነት የእግዚአብሔር ብሉይ ኪዳናዊው የኪዳን ማህበረሰብ ዘንድ ይህ ሰላም (ሻሎም) መታየቱንና መተግበሩን ማሳየት ትላለህ፡፡ • አዲሱ ማህበረሰብ ውስጥ ላሉት ችግሮች በተለይ ለመበለቶች፣ ወላጅ አልባዎችና ድሆች እንዲሁም በመከራ እና በችግር ጊዜያት ለሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ስለሚያደርገው ስር ነቀል የሆነ ልግስናና እንከብካቤ ማሳየት ትችላለህ፡፡
4
Made with FlippingBook - Online catalogs