Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 5 5
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
• አዲሱ ማህበረሰብ የእውነተኛው ክርስቲያናዊ ሚሽን ምልክት ወደ ሆነው ለድሀ አደጎች ጥብቅና መቆም እንዴት እንደተጠራ ማስረዳት ትችላለህ፡፡ ይህ ተሟጋችነት በአካሉ አባላት መካከል በመደብና በልዩነት ላይ ያልተመሰረተና በወገንተኝነትና ጎጠኝነት ላይ ያልሆነ ነው፤ ነገር ግን በአንጻሩ ለድሆችና ለአቅመ ደካሞች መልካምን ለማድረግ ባለ ቁርጠኝነት እና በተለይም በእግዚአብሔር ቤት ያሉ ጉዳተኞችን ተግባራዊ ፍላጎት ለማሟላት በሚደረግ ጥረት ውስጥ የሚገለጥ ነው፡ • ወንጌልን ለድሆች መስበክን ጨምሮ ለኧርባን ሚሽን የቤተክርስቲያንን አዲሱ የማህበረሰብ አንድምታዎች መገንዘብ ትችላለህ፡፡ ይህም ድሆችን በእግዚአብሔር እንደተመረጡ አይቶ ማክበር፤ ኢየሱስ ራሱ አብሮአቸው የቆመና በፍትህና በርህራሄ የሚመለከታቸው መሆናቸውን መገንዘብ ነው፡፡ • ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ድሆችን በመረጣቸው መሰረት ተቀብላ መንከባከብ አለባት የሚለውን ጨምሮ ሌሎችንም የኢህ ምልከታ አንድምታዎች ጠቅለል አድርገህ ማቅረብ ትችላለህ፡፡ (ማለትም ጉዳያቸውን መከላከል፣ መብታቸውን ማስጠበቅ፣ ለእነርሱ ጥብቅና መቆምና በቤተክርስቲያን ውስጥ አድሎ አለማሳየት)፤ የድሆችን ፍላጎት ለማሟላት ያለንን በማካፈል፣ መጻተኞችና እስረኞችን በመቀበል እና እኛም የተካፈልነውን ፍቅር ለሌሎች በማካፈል ለጋስና እንግዳ ተቀባይ ልንሆን ያስፈልገናል፡፡ • የመጨረሻው (ምናልባትም ከሁሉም ይልቅ አስፈላጊውን) አንድምታ ትረዳለህ፤ ይህም ቤተክርስቲያን በእኛና በአለም ውስጥ ፍትህና እኩልነትን መሻት ይኖርባታል፡፡ መሰረታዊ ፍላጎታችንን ለማሟላት ብቻ ሳይሆን ወደ ፍትሃዊነት የሚወስዱን መዋቅሮችና ግንኙነቶች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እንተጋለን፡፡ በብሉይ ኪዳን ጌታ የኪዳኑን ማህበረሰብ ለድሆች ሃብት እንዲሰጥ እንደተጠበቀበት እንዲሁ ደግሞ ቤተክርስቲያን በሁሉም ግንኙነቶች እና ጉዳዮች ውስጥ በድሆች ስም ፍትህና እኩልነት በመፈለግ እውነተኛውን የብልጽግና ወንጌል መኖር አለበት፡፡ ንገረኝ፥ ያ ሰው አንተ ነህ? ሉቃስ 7:18 - 23 “ደቀ መዛሙርቱም ለዮሐንስ እነዚህን ሁሉ አወሩ። ዮሐንስም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ወደ እርሱ ጠርቶ። የሚመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላውን እንጠብቅ? ብሎ ወደ ኢየሱስ ላከ። ሰዎቹም ወደ እርሱ መጥተው፦ መጥምቁ ዮሐንስ፦ የሚመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላውን እንጠብቅ? ብሎ ወደ አንተ ላከን አሉት። በዚያች ሰዓት ከደዌና ከሥቃይ ከክፉዎች መናፍስትም ብዙዎችን ፈወሰ፥ ለብዙ ዕውሮችም ማየትን ሰጠ። ኢየሱስም መልሶ፦ ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት፤ ዕውሮች ያያሉ፥ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ፥ ደንቆሮዎችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ፥ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው አላቸው።” የኢየሱስ የመሲህነት አገልግሎት በይሁዳ ላይ በታላቅ ደስታና ጉጉት የተገለጠ ቢሆንም ለመጥምቁ ዮሐንስ ሳይቀር መሲህነቱ ለሁላቸውም በቶሎ የተገለጠ ነገር አልነበረም፡፡ የኢየሱስ ተአምራትና ድንቅ ስራዎች ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ተመልካቾችን ያገኙት በመጥምቁ ዮሐንስ የመጨረሻ ቀናት
4
ጥሞና
Made with FlippingBook - Online catalogs