Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

1 5 6 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ነበር፡፡ የዮሐንስ አገልግሎት እየቀነሰ በሄደ መጠን የኢየሱስ ደግሞ በአድማስና በተጽዕኖ ይጨምር ነበር (ዮሐ3፡30)፡፡ ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር መንግስት የኢየሱስን አዋጅ መገለጥ በመጠባበቅ አህዛብን ለንስሐ ያጠመቀ ሲሆን ኢየሱስ ደግሞ በተአምራቱ፣ ስብከቶቹ፣ በራሱ ባህርይና ሕይወት፣ ኃይሉን ገልጧል፡፡ እያንዳንዱ አየሱስ ያደረገውና የሆነው ነገር ሁሉ የእርሱን የይገባኛል ጥያቄ ትክክለኛነት ያረጋግጣል፡፡ የናዝሬቱ ኢየሱስ በእርሱ ሰው ሆኖ ወደ ምድር መምጣት ውስጥ ያለውን መንግስት ያወጀ የእግዚአብሔር መሲህ ነበር፡፡ ስለ ኢየሱስ ድንቅ ስራዎች ወሬው በይሁዳና በአከባቢው ሁሉ በወጣ ጊዜ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ሰምተው ሄደው ለዮሐንስ ነገሩት፥ ዮሐንስም ቀጥተኛ ከሆነ ጥያቄ ጋር ሁለቱን ደቀመዛሙርት ወደ ኢየሱስ ላካቸው፡፡ የምትመጣው አንተ ነህ ወይስ ሌላ እንጠብቅ? በኢየሱስ ስራዎችና አቋም ውስጥ የሚገለጥ በቂ ማስረጃ ነበር፡፡ ቢያንስ ናዝራዊ በሆነው ህይወት ላይ ያለው ትንቢታዊ ጥሪ እንኳን በቂ ነው፡፡ የዮሐንስ ጥሪ እንደ ጥርጣሬ ወይም እንደመረዳት ሊወሰድበት አይገባም፡፡ ጥያቄው ዮሐንስ ወይም ኢየሱስ ስለ ራሱ ስለሰጠውምስክርነት አንጻር እውነትና ግልጽነትን መፈለጉን ያሳያል፡፡ ኢየሱስ ከዮሐንስ ደቀመዝሙር ጥያቄውን እንደሰማ በርካቶችን ከህመሞቻቸውና ከስቃዮቻቸው መፈወሱንና አጋንንትና ማስወጣቱን ሉቃስ ይነግረናል፡፡ ዕውራንን አበራ፤ ማንነቱን በተመለከተ ኢየሱስ ከዚህ የተሻለ ምን ማስረጃ ማቅረብ ይችል ይሆን! በአይነትም ሆነ በብዛት የእግዚአብሔር የመንግስቱ ኃይል በእርሱ ውስጥ በመገለጥ እግዚአብሔር እየሰራ እንደሆነ ደቀ መዛሙርቱ ስላከናወነው ነገር ትርጉም ከሚሰጥ ማብራሪያ ጋር ምላሽ ሰጣቸው፡፡ ኢየሱስ እነርሱ ራሳቸው ያዩትንና የሰሙትን ሄደው ለዮሐንስ እንዲነግሩት አዘዛቸው፡፡ በተለይም እነርሱ ራሳቸው የሚመሰክሯቸው ስራዎችን ለዮሐንስ እንዲነግሩት አዘዘ፡፡ “እውሮች ያያሉ፣ አንካሶችም ይሄዳሉ፣ ሙታንም ይነሳሉ፣ ለድሆች ወንጌል ይሰበካል፡፡” ኢየሱስ በእርሱ የማይሰናከሉ ሁሉ ብጹዕ መሆናቸውን በሚገልጽ አስደናቂ ንግግር ይዘጋዋል፡፡ እዚህ ጋር ግልጽ የሆነ የኢየሱስ የራሱ የሆነ የማንነት ማረጋገጫ አግኝተናል፡፡ ኢየሱስ ተአምራቱን፣ ፈውሱን፣ መሲህነቱን ለማስረዳት ስለሰጡት ትርጉም ዮሐንስ እንደሚረደ እንዴት ሊያውቅ ቻለ? ለድሆች የመንግስቱ ወንጌል እየተሰበከላቸው መሆኑን ለዮሐንስ መንገር በእርግጥ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መሲህ ስለመሆኑ የሚያረጋግጠው በምን መልኩ ነው? ምናልባት ጥቂት ምንባቦች ለምን እንደሆነ ያሰረዱህ ይሆናል:- ኢሳይያስ 32: 3 - 4 “የሚያዩትም ሰዎች ዓይኖች አይጨፈኑም፥ የሚሰሙትም ጆሮች ያደምጣሉ። ጥንቃቄ የሌላቸው ሰዎች ልብ እውቀትን ታስተውላለች፥ የተብታቦችም ምላስ ደኅና አድርጋ ትናገራለች።” ኢሳይያስ 35: 5 - 6 “በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል። በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፥ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።” ኢሳይያስ 42: 6 - 7 “እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፥ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ፥ የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።”

4

Made with FlippingBook - Online catalogs