Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 5 7

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ኢሳይያስ 42: 16 “ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፥ በማያውቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፥ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፥ አልተዋቸውምም።” ኢሳይያስ 61: 1 - 3 “የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል። የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤ እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።” የኢየሱስ ምላሽ መሲህ ምን መምሰል እዳለበትና ስራዎቹም ከምስሉ ጋር ለምን እብሮ መሄድ እንዳለባቸው ያሳያል፡፡ የኢየሱስ የፈውስ አገልግሎትና ወንጌልን ለድሆች የመስበክ የመሲሐዊው ዘመን ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር መንግስት የመጣበትንና ከሁሉም ባላይ የናዝሬቱ ኢየሱስ የመንግስቱ መሲህ የሆነበት ዘመን ነው፡፡ ኢየሱስ ያ ለድሆች ያደረገው (እና የተናገረው) መሆኑን እናውቃለን፡፡ እንግዲህ ከመሲሁ ጋር ያለንን ትስስር እንዴት እናሰያለን? የተራቡትን፣ የተጠሙትን፣ የታረዙትን፣ መጻተኞችን፣ የታሰሩትንና የታመሙትን ልክ እንደ እርሱ፣ እርሱም እነርሱን እንደሆነ አድርገን በመውደድና በመቀበል፤ በእርግጥ ለእርሱ የምናደርገው (የማናደርገውም ቢሆን) ሁሉ የምናደርገው ለእርሱ ነው (ማቴ 25፡31-46) ስለዚህ መሲሐዊው ዘመን (እና መሲሐዊውማህበረሰብ) የሚታወቀው ለተጎዱትና ለችግረኞች ፍትህና ጽድቅን በማድረግ ይሆናል፡፡ ይህ ዛሬም ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እውነተኛው መሲህ መንፈሳዊ ማስረጃውን ያቀረበው በእስራኤል ማህበረሰብ ውስጥ ለነበሩ በጣም ለችግር የተጋለጡ፣ ያልተወደዱ እና ችግረኞች ፍቅሩን፣ ርህራሄውን፣ ልግስናውንና ፈውሱን በመስጠት እንዲሁም የእግዚአብሔርን መንግስት የመምጣቱን ወንጌልን ለድሆች በመስበክ ነበር፡፡ አሁንም የእርሱ ተከታዮች እርሱ እንዳረገው ለተመሳሳይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተመሳሳይ ነገሮችን በማድረግ እውነተኛነታቸውን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በእርግጥ በእርሱ እኖራለው የሚል ማንም ሰው እርሱ በተመላለሰበት መንገድ ሊመላለስ ይገባዋል (1ዮሐ2፡6)፡፡ ሁላችንም የምንጠብቀው ብቸኛው ተስፋችን ኢየሱስ ነው፡፡ በነገራችን ላይ አንተ የእርሱ ለዘላለም የሚኖረውመሲሐዊ ማህበረሰብ አባል ነህ? ካምፕፋየር ቲውን እንደሚለው “ክርስትያኖች መሆናችንን በፍቅራችን ያውቃሉ፣ በፍቅራችን አዎ፣ ክርስትያኖቸ መሆናችንን በፍራችን ያውቃሉ”፡፡

4

Made with FlippingBook - Online catalogs