Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

1 5 8 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ አቤት ድሆችና ሀጥያተኞችን በአዲሱ ኪዳን የድግስስብሰባ ላይ ይገኙ ዘንድ ትጋበዛለህ፡፡ቤተክርስትያን ሁል ጊዜ የጌታን መገኘት ዝቀው በማለትና በመከራ ውስጥ ታክብረው፤እናም በማዕድህ ዙሪያ እንደተሰባሰብን ወንድሞች እና እህቶች እርስ በእርሳችን መከባበርን እንማር፡፡ይህንም ከአብ ጋር በመንፈስ ቅዱስ ህብረት ውስጥ ከዘላለም እሰከ ዘላለም በሚኖርና በሚገዛ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እናምናለን፡፡ አሜን፡፡

የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት

~ Presbyterian Church (U.S.A.) and Cumberland Presbyterian Church. The Theology and Worship Ministry Unit. Book of Common Worship. Louisville, KY: Westminister/John Knox Press, 1993. p. 372.

ማስታወሻዎችህን አስቀምጠህ ፣ ሀሳቦችህን እና ምልከታዎችን ሰብስበህ ለትምህርት 4 “ክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና ድሆች “ የተዘጋጀውን አጭር ፈተና ውሰድ

አጭር ፈተና

ከሌላ ተማሪ ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደቡ የቃል ጥናት ጥቅሶች ገምግሙ ፣ ፃፉ እና/ ወይም አንብቡ - ዕብራውያን 11:13-16

የቃል ጥናት ጥቅስ ቅኝት

ያለፈውን ሳምንት የንባብ ማጠቃለያህን ማለትም መምህሩ በመደበው ንባብ (የንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ) ላይ ለማድረግ የተፈለጉትን ዋና ዋና ነጥቦችን፣ አጭር መግለጫዎን እና ማብራሪያዎን አቅርብ ፡፡

የቤት ስራ/መልመጃ ማስረከቢያ

4

CONTACT

እንዴት እንደዛ ይኖራሉ? ትጋትን፣ ምርታማነትን እና ግለሰባዊ ኃላፊነትን አግዝፎ በሚመለከት ህብረተሰብውስጥ “እውነተኛዎቹ ችግረኞች” ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ለማሳየት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይገጥማቸዋል፡፡ በጠቅላላው ስንመለከት ድሆችን በደረሰባቸው ታሪካዊ ጭቆና በትልቁ ህብረተሰብ ውስጥ ተሳትፎ እነዲኖራቸው ከሚያደርጉ ማህበራዊ መመሪያዎች፣ ስልጣን ላይ ባሉ ሰዎች ከሚደርስባቸው ግፍ በመነሳት ድሆችን ያለመረዳት አዝማሚያ ይታያል፡፡ ይልቁንም በትልቁ የአሜሪካ ባህል ድሀ ድሀ የሆነው መነሳሳት፣ የትጋት፣ የግለሰባዊ ክብርና የሞራል ውድቀት ችግሮች ስላሉበት ነው ብሎ ያምናል፡፡ በእርግጥ ብዙዎች በራሳቸው የሞራል ውድቀት፣ መጥፎ የግል ውሳኔዎች፣ ሱሶችና ክፋቶቻቸው የተነሳ ድህነት እንደደረሰባቸው መስማማት ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ሰዎች የሚበዙት ድሆች እንደሆኑ ይቆጠራሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ ፖሊሲዎችና ለድሆች የሚኖሩት ምላሾች ድሆችን ስነ ስርዓት የጎደላቸውና ሁኔታቸውን ለማሸነፍ ቁርጠኝነት የጎደላቸው አድርጎ ከመመልከት የመነጩ ናቸው፡፡ ከሁኔታቸው በመነሳት ድሆችን ስለድህነታቸው መውቀስ በክርስትያኖችም ዘንድ ሳይቀር የተለመደ ነገር ነው፡፡ ይህ አመለካከት ራሱንና ሁኔታውን ማሻሻል ለሚፈልግ ሁሉ በርካታ እድሎች እንዳሉ

1

Made with FlippingBook - Online catalogs