Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 5 9
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ያምናል፡፡ አንድ ሰው ለረጅም ጊዜ ደሀ ሆኖ ከቆየ የራሱ ጥፋት ነው፥ ማንም ሰው በዚያ መንገድ የሚኖርበት ምንም ምክንያት የለውም፡፡ በብዙ ክርስቲያን ባልሆኑ፣ የመካከለኛው መደብ ባህሎችና አልፎ ተርፎም በክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘው ስለዚህ አቋም ምን ታደርጋለህ?
እውነተኛ አምልኮ ስለ እምነትና ድነት በሚደረጉ ውይይቶች በክርስትና ታሪክ ውስጥ አብሮ የዘለቀ ዋና ጥያቄ አለ የእውነት የሚያድነው እምነት የቱ ነው? የሚል ነው፡፡ አንድ ሰው በትክክል ከኃጢአቱና ጣኦት አምልኮው ንስሐ ገብቶ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማመኑ እንዴት ይታወቃል? በወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ታሪክ ውስጥ ለእውነተኛው እምነት እንደ ማስረጃ ድነታችን እንዲያገለግሉን ብዙውን ጊዜ በውጫዊ ምክንያቶች ላይ እናተኩራለን፡፡ ከስብከት በኋላ የሚነሳን እጅ ለመዳን ያለውን ፍላጎት ለመግለጽ የተነሳን ሰው ወደ ፊት መጥቶ ከመጋቢው ጋር የሚደረግ ጸሎት መጸለይ እነደሚያድነው እምነት ጠንካራ ማስረጃዎች ስንወስዳቸው ይታያል፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማረጋገጫዎች የሚመጡት በመጀመሪያ ከሚደረገው ውሳኔ በኋላ ነው፤ ይህ ሰው በጌታ ወንድሞችና እህቶችን ይወዳል (ዮሐ 13፡34-35)፤ መሰረታዊ የምግብና አልባሳት ችግር ላለባቸው ሰዎች እውነተኛ ልብ አሳይቷል (ያዕቆብ 2፡14-16)፣ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች የርህራሄ ልቡን ከፍቶላቸዋል (1ኛዮሐ 3፡16-18) በያዕቆብ መሰረት እወነተኛው አምልኮ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅና በአለም ከሚገኝ እድፍ ሰውነታቸውን መጠበቅ ነው (ያዕ1፡ 27)፡፡ በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያለውን ልምምድ ለድሆች ማሳየት ካለብን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባህሪያት አንጻር ምን ያህል ከእግዚአብሔር ጋር ላለን የግል ግንኙነት ማሳያ መሆን ይችላሉ? አሳ ማጥመድ አስተምረው “አንድ ሰው ለአንድ ቀን አሳ ብትሰጠው ለአንድ ቀን ትመግበዋለህ፣ ነገር ግን አሳ ማጥመድ ብታስተምረው ለህይወት ዘመኑ ሁሉ ትመግበዋለህ” የሚለው አባባል ድሆችን ለመርዳት የምንጠቀምበትና ምናልባትም በሁሉም ዘንድ ቅቡልነት ያለው አባባል ነው፡፡ በእውነቱ ብዙዎች በጎ አድራጎት ስራዎች በዚህ ምክንያት እንደከሸፉ ያምናሉ፤ ያልተቋረጠ የገንዘብ ድጋፍና ምንም ወይም በጣም ጥቂት ቁጥጥር ጥገኝነትን እንደማበረታታትና ግላዊ ሃላፊነትን እንደመሸርሸር ይታመናል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ብዙ እርዳታ ተቀባዮች መንግስትን እንደ አቅራቢያቸው ሲመለከቱ የተወሰኑት ደግሞ ለሚያገኙት እርዳታ ሲሉ ስራ መስራት ሲሸሹ ይታያል፡፡ በአሁኑ ወቅት በርካታ የክልልና አከባቢያዊ ድርጅቶች ተሳትፎን ግዴታ እያደረጉ ነው፡፡ እርዳታ ጊዜያዊ ድጋፍ እንጂ ቋሚ እንክብካቤ እንዳልሆነ ይከራከራሉ፡፡ የእነዚህ ሰዎች ውጥኖች ጥሩ ቢመስልም በእርግጥ ሊያድግ የሚችለው ቤተሰብ ውስጥ ያሉ መሰረታዊ የኑሮ ችግሮችን በደሞዙ ይደግፍ ዘንድ አያስችሉም ሲሉም ይሞግታሉ፡፡ እንግዲህ በአንተ አመላከት መንግስት የድሀ ዜጎችን ህይወት በመደገፍ ሚናው የሚኖር ክርስትያናዊ አስተያየት ምንድ ነው?
2
4
3
Made with FlippingBook - Online catalogs