Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 7

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

1 በወንጌል ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔርን ታሪክ ግልጽና ጉልህ በሆነ መንገድ ተስሎ እንመለከታለን፤ የእግዚአብሔር በግ ለአለም ሃጥያት ምትክ መስዋዕት ሆኖ እንጨት ላይ ተንጠልጥሏል፡፡ ይህ የሞተው፤ በሶስተኛው ቀን ከሙታን የተነሳው ክርስቶስ እንደሆነ የሚያምን ከኃጥያቱ ነጻ ይወጣል፤ በዚህ አለም በሚኖረው ህይወት በውስጡ የሚኖርና በመጨረሻውም ቀን ከሙታን የሚያስነሳውን መንፈስ ቅዱስን ይቀበላል፡፡ ይህ ታሪክ ለሰው ልጆች ሁሉ ድነትና ሕይወት የምስራች እንደሆነ ለተቀበሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ጎልማሶችና ወንዶችና ሴቶች ልጆች ከ2000 አመታት በላይ ተደጋግሞ በመነገር ላይ ይገኛል፡፡ ሚሽን የዚህ ታሪክ ዋነኛ ተዋናይ ስለሆነው ስለእግዚአብሔር ፍቅርና ጸጋ ለአለም ሕዝቦች በሚረዱትና በሚያደንቁት መንገድ ታሪኩን መናገር ነው፡፡ እግዚአብሔር የራሱ ታሪክ ጀግና ነው፤ የመዳንም ታሪክ ቢሆን “ከእርሱ ታሪክ” ውጪ ምንም አይደለም፡፡ እኛም በርግጥ በእውነት ከተቀበልነው የእግዚአብሔር የፍቅር ታሪክ የእኛም የራሳችን ታሪክ ሊሆን ይችላል፡፡ የክርስትናን መልዕክት እንደ ታሪክ መልሶ ማግኘት በጣም ረጅም ጊዜ የሚፈልግ ነገር ነው፡፡ የክርስትናዊ ደቀ መዝሙርነትና የሚሽን መሰረቶችን ለመረዳት የ”ስቶሪ ቴዎሎጂ” እና የ”ናሬቲቭ ቴዎሎጂ” ምልክቶች ቀድሞ ወደ ነበሩበት መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ የእምነታቸን መሰረት እግዚአብሔር አባቴ ነው በሚል አንድ አይሁዳዊ ተጓዥ ሰባኪ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ነው የሚለውን ታሪክ ያመንን ሁላችን ህይወታችንን፤ ተስፋችንን እና አገልግሎታችንን ሁሉ ከዚያ ጋር አጣብቀናል፡፡ እንግዲህ “ከዕለታት አንድ ቀን” ብሎ የጀመረው ታሪካችን “በደስታና በተድላ አብረው ኖሩ” የሚል ፍጻሜ እንደሚኖረው መዘንጋት የለብንም። በመሆኑም በአካባቢያዊም ሆነ በአለምአቀፋዊ ሚሽን መሳተፍ ማለት ሌሎቹ ከመስማታቸው በፊት እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ የሚፈጽመውን የእግዚአብሔርን ታሪክ ላልሰሙት ማወጅ ነው።

በአለምአቀፍ የሚሽን አለም ውስጥ ሁልጊዜም የታሪክ ጊዜ ነው።

የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ ይገኛል) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ፥ እኛና መላው አለም የእርሱን ድንቅ ስራዎች እናስተውል ዘንድ የአዳኛችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥሪ በፍጥነት እንድንመልስና ለሰዎች ሁሉ የማዳኑን የምስራች እንድናውጅ ጌታ ሆይ ጸጋን ስጠን፤ እርሱም ከአንተና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የሚኖርና የሚነግስ አንድ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም። አሜን! ~ Episcopal Church. The Book of Common Prayer and Administrations of the Sacraments and Other Rites and Ceremonies of the Church, Together with the Psalter or Psalms of David. New York: The Church Hymnal Corporation, 1979. p 215

የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት

Made with FlippingBook - Online catalogs