Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

1 6 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ደግሞ ደጋግሞ መናገር የክርስትና እምነት ባህሪይ ነው። እኛ የዳንነው “ታላቅ ደስታ” በሆነው “የምስራቹ ቃል” ላይ ህይወታችንን ስለቀረጽንና ስላጸናን ነው። የክርስቲያን ሚሽንን ተፈጥሮ ሊሰሙት ለሚገባቸው ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ መንገር ነው የሚል ትርጓሜ መስጠት አስገራሚ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሁልጊዜም ቢሆን ሚሽን ማለት ወንጌልን ወዳልሰሙት በመሄድ ለሰሚዎቹ ግልጽና ተስማሚ በሆነ መንገድ በናዝሬቱ ኢየሱስ በኩል ስለተገለጠው የእግዚአብሔር የፍቅር ቃል መንገር ነው። የሰሚዎቹን ቋንቋ፣ ባህልና ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእነርሱ ተስማሚ በሆነ መንገድ የእግዚአብሔርን የጸጋውን ወንጌል ማድረስ ያስፈልጋል። በመሆኑም ሁልጊዜም ቢሆን ሚሽን ማለት በክርስቶስ በኩል ስለ እግዚአብሔር ክብር ደግሞ ደጋግሞ መናገር ነው። ዋናው አላማ ይህን ታሪክ ላልሰሙት ሁሉ እስከ ምድር ጫፍ ድረስ በማድረስ ሰምተው የተቀበሉት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር በመታረቅ የዘላለምን ህይወት ይወርሱ ዘንድ ነው። ግልጽና ቀጥተኛ በሆነ ቋንቋ ለማስቀመጥ ያህል ከክርስቲያናዊ ሚሽን መሰረቶች አንዱን ይወክላል - የቆየውን በጣም የቆየውን የኢየሱስን እና የፍቅሩን ታሪክ መንገር። እንዳለመታደል ሆኖ በዛሬዎቹ ክርስቲያኖች ዘንድ ይህን የተከተለ የቃሉ ህይወት፣ የጌታ ኢየሱስ ወንጌል እና ይህን ታሪክ ያማከለ የሚሽን አካሄድ ችላ ተብሎ ሳይንሳዊ ዘዴን ያማከለ የሚሽን ስራ ሲተገበር ይታያል። ብዙ ክርስቲያኖች ይበልጥ ሳይንሳዊ ለሆነው ዘዴ ሲሉ ታሪክን የመንገርን ሃይል ችላ ይሉታል፤ በዚህም ምክንያት በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ በመናገር ውስጥ ያለውን ድንቅ ነገር አጥተናል። አንድ የፍልስፍና ወይም ሳይንሳዊ ጽሑፍ ሊገልጠው በማይችለው ልክ ታሪክ መናገር አንድን እውነታ በተጨባጭ የማሳየትና በአጥንት የማስቀረት አቅም አለው። በደንብ በተጠኑ ስብከቶች፣ ሳይንሳዊ ተዓማኒነትን ባተረፉ የቃሉ ትርጉም ዘዴዎች ላይ በመመርኮዝ ብዙዎች የራሳቸውን ቋንቋ በመተው ለደረቅ፣ ከአዕምሮ ለሆነና እርባና ለሌለውወንጌል ተላልፈው ተሰጥተዋል፤ እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳን ምድራዊውን ዘዴ ቢመርጡም ያን ያህል አሳማኝ አይደለም። ታሪኩን በደንብ አድርገን መናገርን በተቃወምን መጠን የናዝሬቱ ኢየሱስን ታሪካዊ ዕውነታዎች በወንጌል “ዋና ቋንቋ” አለመግለጻችን ብቻ ሳይሆን አሳማኝም አይደለንም። እንዳብዛኛዎቹ የዘመኑ ወንጌላውያን ምሁራን ሊላንድ ራይከንም የመጽሐፍ ቅዱስን ምስላዊና ታሪካዊ የትረካ ዘዴ አስተውለዋል። የኢየሱስን መልዕክት በማስረጃ ተደግፎ እንደቀረበ ስነመለኮታዊ ሳይንስ ብቻ አድርጎ የመመልከት አደጋውን ያስረዳሉ። ክርስትያኖች መጽሐፍ ቅዱስን በማስረጃ ተደግፎ የቀረበ ስነ መለኮታዊ መመሪያ ብቻ አድርገው ከመመልከታቸው የተነሳ ወደ ስህተት ማምረታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ከማብራሪያዎቹና ከሀሳቦች ይልቅ ምስሎችና የምናባዊ ጭብጦች መጽሐፍ ነው፡፡ ይህን ደግሞ ሰባኪያንና የስነ መለኮት ምሁራን በቀላሉና ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ወደ መልዕክቶች መጽሐፍት ሲሳቡ እንመለከታለን፡፡ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር እንዳሉት መጽሐፍ ቅዱስ በስፋት የሚናገረው በምስሎች አማከኝነት ነው፡፡ የመጽሀፍ ቅዱሰ ታሪኮች፤ ምሳሌዎች፤ የነቢያት ስብከቶች፤ የጥበበኞቹ ምልከታ፤ የመጪው ዘመን ምስሎች፤ ያለፉት ክስተቶች ትርጓሜዎች በሙሉ ከልምምድ በመነጩ ምስሎች ይገለጻሉ፡፡

1

~ Leland Ryken. Dictionary of Biblical Imagery. (electronic ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2000.

Made with FlippingBook - Online catalogs