Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 5

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

• በዚህ ዘመን በሚሽን ሚና እና በናዝሬቱ በኢየሱስ ፊት የአብርሃምና የዳዊት ተስፋ እንደተፈጸመ በመግለጽ መካከል ያለውን ትስስር ማሳየት ትችላለህ፤ አሁንም በተልእኮው የወንጌል አዋጅ አማካይነት ለአህዛብ በሚደረግ የመስቀሉ ስብከት በኩል የአዲሱ ሕይወት ተስፋ መሰጠቱን ትገነዘባለህ፡፡

“ሁልጊዜም የታሪክ ጊዜ ነው” የእግዚአብሔር ክብር ታሪክ እና የሚሽን ጥሪ

ጥሞና

ሮሜ 16፡25- 27 “እንግዲህ እንደ ወንጌሌ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም እንደ ተሰበከ፥ ከዘላለም ዘመንም የተሰወረው አሁን ግን የታየው በነቢያትም መጻሕፍት የዘላለም እግዚአብሔር እንደ አዘዘ ለእምነት መታዘዝ ይሆን ዘንድ ለአሕዛብ ሁሉ የታወቀው ምሥጢር እንደ ተገለጠ መጠን ሊያበረታችሁ ለሚችለው፥ ብቻውን ጥበብ ላለው ለእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።” ምናልባትም “ከእለታት አንድ ቀን” ወይም የሱ ዘመድ የሆነው “በደስታና በተድላ አብርረው ኖሩ” እንደሚሉት ሀረጎች ትኩረትን የሚስብ ላይኖር ይችላል፡፡ ብዙዎቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የሰማናቸው ተረቶች የመጀመሪያ ሀረጎች ናቸው፡፡ እነዚህን ቃላት መስማት ወድያው ቆም ብለን ራሳችንን እንድናዞርና ታሪኩ ከየት ተነስቶ ወዴት እንደሚሄድ የማወቅ ጉጉት ይፈጥርብናል፡፡ እንግዲህ እኛ ሰዎች ሶቅራጥስ እንደሚለው ምክንያታዊ ፍጥረቶች ብቻ ሳንሆን ታሪክ ተናጋሪዎችም ጭምር ነን፡፡ ራሳችንን በምንነጋገራቸው ታሪኮች ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ ሁላችንም ስለሀገራችን፣ ስለቤተሰባችን፣ ስለራሳችን በምንናገራቸው ታሪኮች ውስጥ የተሻለ የራስ ግንዛቤ እና በራስ መተማመን ይፈጥሩልናል። የታሪኮቻችን ገፀ ባህሪያት፣ ጭብጦችና ሴራዎች የምንኖርበትን እውነታ ሞራልና ዕሴቶች ይወስኑልናል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የራሱ ማህበራዊ፣ ባህላዊና ሃገራዊ የፍልስፍና ታሪክ በገዛ በራሱ ታሪክ ውስጥ የሚመለከት ግለሰብ፣ ቤተሰብ፣ ጎሳ፣ ባህል ወይም ህዝብ ማግኘት እጅግ ያስቸግራል፡፡ ሆኖም ግን የእውነት የምንኖረው በምንናገራቸው፣ በምናምንባቸውና ህይወታችንን በመሰረትንባቸው ታሪኮች ውስጥ ነው፡፡ ይህ የታሪኮች ማህበራዊም ሆነ ግለሰባዊ ሚና (ታሪካዊ ወይም ልብ ወለዳዊ ሊሆኑ ይችላል) በዚህ ዘመን ባሉት አብዛኛው አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የተዘነጋ ይመስላል፡፡ ብዙውን ጊዜ በየቤተክርስቲያኖቻችን ትኩረት የምንሰጠው ለቀረበው እውነት፣ ለእምነት አቋም መግለጫዎች እና ጥሩ ተደርገው ለተዋቀሩና በቀላሉ አንብበንና ሸምድደን ለምናልፋቸው የወንጌል ታሪኮች ነው፡፡ ምንም እንኳን እንዲህ አይነቱ ስነመለኮት ጠቃሚ ቢሆንም የወንጌል ልብ ትርታና መሰረት ግን በዚህ መልክ በቀላሉ ሊጠቃለል በሚችለው በኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ የተመሰረተ ነው፡፡ ይልቁንም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስጋ መልበስ፤ በቀራንዮ መሰቀል፤ በትንሳኤው ድል፤ በእርገቱና በአባቱ ቀኝ በመቀመጡ አማካኝነት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ፍቅሩን የገለጸበትን ታሪክ በታላቅ ደስታ መነሳሳትና መደነቅ መናገር ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ የኢየሱስ ክርስቶስን ሃይልና ጸጋ በእምነት መግለጫዎች ብቻ መለማመድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ቃልና በቅዱስ ቁርባንም ጭምር መጽደቅ እና መነገር ይኖርበታል። ይህን ታሪክ

1

Made with FlippingBook - Online catalogs