Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
1 7 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
በዚህ ቪዲዮ የተነሱትንም ሆነ ሌሎችን ጥያቄዎች ለመመለስ በቂ ጊዜ ለመውሰድ ሞክር፡፡ በዚህ ክፍል የድህነት ጽንሰ ሃሳብ ከመጽሐፍ ቅደስ የሻሎም ጭብጥ ወይም ከእግዚአብሔር የኪዳን ማህበረሰብ ሙሉነት ጋር እንዴት እንደሚገናኝ ተመልክተናል፡፡ በሁሉም ጥያቄዎችና ትእዛዛቱ ውስጥ እግዚአብሔር ህዝቡ ለድሆች ያለውን ጥልቅ ፍቅርና ለመደገፍ ያለውን መስጠት እንዲያሳይ ያስፈልጋል፡፡ እስራኤል ለድሆች ፍትህና ጽድቅን በማሳየት ሁልጊዜም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ባታደርግም የእርሱ ፍላጎት ግን ግልጽ ነበር፡፡ በችግራቸው ጊዜ እግዚአብሔር ከድሆች ጋር መቆሙን ያሳየናል፡፡ ህዝቡም ለፍትህ፣ ለሰላምና በኪዳኑ ማበረሰብ ውስጥ እርስ በእርሳቸው በሚኖራቸው መስተጋብር ያላቸውን ፍቅር ያሳዩ ዘንድ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የቀረቡትን ጥያቄዎች በመመለስ እነዚህን አስፈላጊ እውነቶች እና ለሚሽን ያላቸውን አንደምታ ገምግም፡- 1. የሻሎም ትርጉም ምንደነው? ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው ትርጓሜ እና የድህነት ግንዛቤ ጋር እንዴት ይዛመዳል? 2. በእግዚአብሔር ህዝቦች መካከል የሻሎም ጽንሰ-ሀሳብን የሚሞሉ አንዳንድ ወሳኝ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አካላት ምንድን ናቸው? ለምንደነው ሻሎም እንደ ሰዎች ስራ ብቻ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር የቸርነቹ ልግስና መወሰድ ያለበት? ከመሲሁ መምጣት ጋርስ እንዴት ይዛመዳል? 3. ድህነትና ውጤቶቹ እንዴት የእግዚአብሔርን ሰላም መካድ እንደሆነ አስረዳ፡፡ የእግዚአብሔር በረከት፣ አቅርቦቶችና ትእዛዛት ድህነትን ለማሸነፍና በህዝቦች መካካል ፍትህና ጽድቅን ለማረጋገጥ እንዴት ነው የተዘጋጁት? 4. እግዚአብሔር ባሉበት ሁኔታና በመከራቸው ውስጥ ከድሆች ጎን ይቆም ነበር ማለት የምንችለው በምን መልኩ ነው? የዘጸአቱ ክስተት እግዚአብሔር ከድሆችና ከተጨነቁት ጎን መቆሙን ቅርጽ የሚሰጠው እንዴት ነው? እስራኤል በኪዳኑ “የቅድስናው ነጸብራቅ፣ የፍትህና የምህረት ተምሳሌት እና ለአህዛብ ብርሃን” መሆን ያለበት እንዴት ነው? 5. በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሶስቱ ዋና ዋና የድህነት መንስኤዎች ምንድን ናቸው? እንዴትስ እርስ በርሳቸው ይዛመዳሉ? “ድሆች” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሌሎች እንደ “መበለት”፣ “ወላጅ አልባ”፣ “መጻተኞች” ካሉ ጽንሰ ሃሳቦች ጋር እንዴት ይዛመዳል? 6. በብሉይ ኪዳን ማህበረሰብ ውስጥ እግዚአብሔር ለድሆች አያያዝ የሰጣቸውን መመዘኛዎች ዘርዝር፤ እነዚህ መመዘኛዎች እግዚአብሔር ለድሆች ስላለው ልብና የእነርሱን ድህነት ለማስወገድ በህዝቡ ዘንድ ስለተቀመጠው ጥበብ እንደ ምስክር የሚያገለግሉት እንዴት ነው? 7. እግዚአብሔር ለህዝቡ ከሰጣቸው መመዘኛዎች ሁለቱን በመጥቀስ ከትርጉማቸው እና ለሻሎም ካላቸው አንድምታ አንጻር በደንብ አብራራቸው። እነዚህ መመዘኛዎች ዛሬ ለድሆች ስላለን አያያዝ ምን ይላሉ? በግልፅ አብራራ።
መሸጋገሪያ 1
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሽ
4
Made with FlippingBook - Online catalogs