Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 7 3

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

8. እነዚህን የእግዚአብሔር የኪዳኑ ማህብረሰብ መመዘኛዎች ስንመለከት አንድምታቸው ምንድነው? እነዚህ መመዘኛዎች እኛ ዛሬ ፍትህን፣ ደቀመዛሙርት ማፍራትን እና ሚሽንን በተመለከተ ያለንን መረዳት እንዴት ያዳብሩታል?

ክርስቲያን ሚሽን እና ድሆች ሴግመንት 2 - የከተማ ውስጥ አገልግሎት ሚሽናዊ መርሆዎች እና አንድምታዎች

ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ

ኢየሱስ በዛሬው ጊዜ በእግዚአብሔር ህዝቦች መካከል የእግዚአብሔርን ሰላም (ሻሎም) ታሳይ ዘንድ የተጠራችው የእግዚአብሔር አዲሱ የኪዳን መንግሥት ማህበረሰብ የሆነችው የቤተክርስቲያን መስራች እና ራስ ነው። ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ነብያት እና የተስፋ ቃሎች እንደተነበዩለት መሲህ ራሱን ገልጧል። መሲሃዊ አገልግሎቱን የጀመረው ለተጨቆኑት ፈውስን በማድረግና ለድሆች ወንጌልን በመስበክ ሲሆን ከሁሉ ለሚያንሱ (ለተራቡ፣ ለተጠሙ፣ ለታረዙ፣ ለመጻተኞች፣ ለበሽተኞች እና ለታሰሩ) በሚደረግ አያያዝ መዳንን አረጋግጧል። ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ማህብረሰብ ናት፤ የተጠራችውም ወንጌልን ለድሆች ትሰብክ ዘንድ፣ እርስ በርሳቸው እንደ ክርስቶስ አካል ይተያዩ ዘንድ እና በዚህ አለም ውስጥ ፍትህን በማድረግ የመጪውን ዘመን ህይወት ምን እንደሚመስል ታሳይ ዘንድ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ሃይል በተሞላችው ቤተክርስቲያን ህይወትና ተልዕኮ ውስጥ የእግዚአብሔር ብሉይ ኪዳናዊ የኪዳን ማህብረሰብ ሰላም ተገልጦና ጥቅም ላይ ውሎ ይታያል። በአለም ውስጥ እንዳለች የክርስቶስ አካል ቤተክርስቲያን ለድሆች ጥብቅና ትቆም ዘንድ ተጠርታለች፣ ይህም የእውነተኛው የክርስቲያን ሚሽን ምልክት ነው። ኧርባን ሚሽንን በተመለከተ ደግሞ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ራሱን አብሮ ያደረጋቸውን ድሆችን እንደተመረጡ ህዝቦች ለመመልክትና ለመንከባከብ ተጠርታለች። ዝም ብለን ለመርዳት ብቻ ሳይሆን ለመለወጥ በመንግሥቱ መስፋፋት ውስጥ ያላቸውን አቅም በመተማመን በፍትሃዊነትና በርህራሄ ልንይዛቸው ይገባናል። ይህም በመካከላችን ላሉ ለችግር የተጋለጡ ወገኖች ፍትህና እኩልነትን በመሻት እውነተኛውን “የብልጽግና ወንጌል” እየኖርን የምናደርገው ነው። ወለል ላይ ያሉ ፍላጎቶችን ለማሟላት ብቻ ሳይሆን ፍትሃዊ ወደሆኑ ጉዳዮች የሚወስዱ መዋቅሮችና ግንኙነቶች ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ይኖርብናል፤ በዚህ “የከተማ ውስጥ አገልግሎት ሚሽናዊ መርሆዎች እና አንድምታዎች” በተሰኘው ሴግመንት፥ አላማችን የሚከተሉትን መመልከት ትችል ዘንድ ነው:- • ኢየሱስ በዛሬው ጊዜ በእግዚአብሔር ህዝቦች መካከል የእግዚአብሔርን ሰላም (ሻሎም) ታሳይ ዘንድ የተጠራችው የእግዚአብሔር አዲሱ የኪዳን መንግሥት ማህበረሰብ የሆነችው የቤተክርስቲያን መስራች እና ራስ ነው።

የሴግመንት 2 ማጠቃለያ

4

Made with FlippingBook - Online catalogs