Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
1 7 4 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
• ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን ነብያት እና የተስፋ ቃሎች እንደተነበዩለት መሲህ ራሱን ገልጧል። መሲሃዊ አገልግሎቱን የጀመረው ለተጨቆኑት ፈውስን በማድረግና ለድሆች ወንጌልን በመስበክ ሲሆን ከሁሉ ለሚያንሱ (ለተራቡ፣ ለተጠሙ፣ ለታረዙ፣ ለመጻተኞች፣ ለበሽተኞች እና ለታሰሩ) በሚደረግ አያያዝ መዳንን አረጋግጧል። • ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግሥት ማህብረሰብ ናት፤ የተጠራችውም ወንጌልን ለድሆች ትሰብክ ዘንድ፣ እርስ በርሳቸው እንደ ክርስቶስ አካል ይተያዩ ዘንድ እና በዚህ አለም ውስጥ ፍትህን በማድረግ የመጪውን ዘመን ህይወት ምን እንደሚመስል ታሳይ ዘንድ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ሃይል በተሞላችው ቤተክርስቲያን ህይወትና ተልዕኮ ውስጥ የእግዚአብሔር ብሉይ ኪዳናዊ የኪዳን ማህብረሰብ ሰላም ተገልጦና ጥቅም ላይ ውሎ ይታያል። በአለም ውስጥ እንዳለች የክርስቶስ አካል ቤተክርስቲያን ለድሆች ጥብቅና ትቆም ዘንድ ተጠርታለች። • ቤተክርስቲያን በውስጧ ለሚኖሩ ችግረኞች በተለይም ለመበለቶች፣ አባት ለሌላቸውና ለድሆች ልዩ ትኩረት በመስጠት ልግስና እና እንክብካቤ ታደርግ ዘንድ ተጠርታለች። እኛ በመከራና በችግራቸው ጊዜ ለሌሎች አብያተ ክርስቲያናትም ቢሆን ድጋፍ የማድረግ ሃላፊነት አለብን። • በአለም ውስጥ እንዳለች የክርስቶስ አካል ቤተክርስቲያን ለድሆች ጥብቅና ትቆም ዘንድ ተጠርታለች፤ ይህም የእውነተኛው ክርስቲያን ሚሽን ምልክት ነው። ይህ ጥብቅና በአካሉ ውስጥ የሚኖርን ፍትህ ማለትም መደብና ልዩነትን መሰረት ያደረገ አድልኦ እና ነፍጥ)፥ ድሆችና ችግረኞችን ወክሎ መልካምን ስራ መከወንን እና የሌሎችን በተለይም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉትን ችግረኞች ፍላጎቶች ማሟላትን ያጠቃልላል። • ኧርባን ሚሽንን በተመለከተ ደግሞ ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ራሱን አብሮ ያደረጋቸውን ድሆችን እንደተመረጡ ህዝቦች ለመመልክትና ለመንከባከብ ተጠርታለች። ዝም ብለን ለመርዳት ብቻ ሳይሆን ለመለወጥ በመንግሥቱ መስፋፋት ውስጥ ያላቸውን አቅም በመተማመን በፍትሃዊነትና በርህራሄ ልንይዛቸው ይገባናል። • ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ድሆችን በመረጣቸው መሰረት ተቀብላ መንከባከብ ይኖርባታል፤ ይህም ማለት ጉዳያቸውን መከላከል፣ መብታቸውን ማስጠበቅ፣ ለእነርሱ ጥብቅና መቆምና በቤተክርስቲያን ውስጥ አድልኦ አለማሳየት ይጠበቅባታል። የድሆችን ፍላጎት ለማሟላት፣ ያለንን በማካፈል፣ መጻተኞችንና እስረኞችን በመቀበል እና እኛም የተካፈልነውን ፍቅር ለሌሎች በማካፈል ለጋስ እና እንግዳ ተቀባይ ልንሆን ያስፈልገናል። • በመካከላችን ላሉ ለችግር የተጋለጡ ወገኖች በምንሰጥበትና በምንንከባከብበት ጊዜ ለእነርሱም ፍትህ እኩልነትን መሻት ይኖርብናል። ወለል ላይ ያሉ ፍላጎቶችን ለማሟላት ብቻ ሳይሆን ፍትሃዊ ወደሆኑ ጉዳዮች የሚወስዱ መዋቅሮችና ግንኙነቶች ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ይኖርብናል።
4
Made with FlippingBook - Online catalogs