Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 7 5

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

I. ኢየሱስ እና የቤተክርስቲያን ምስረታ: የእግዚአብሔር አዲሱ ኪዳን መንግስት ማህበረሰብ

የቪድዮ ሴግመንት 2 ዝርዝር

ጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን በድሆች የተዋቀረች ነበረች ለድሆች የሚደረግ እንክብካቤ ጳውሎስና በርናባስ ከያዕቆብ፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ጋር ባላቸው ስምምነት ላይ የተመሰረተ ሃሳብ ነው (ገላ 2:10)። በኢየሩሳሌም የነበሩ የአይሁድ ክርስቲያኖች ድሆች ስለነበሩ አህዛብ የነበሩት ክርስቲያኖች ከኢየሩሳሌም በሚያገኙት መንፈሳዊ በረከቶች ምትክ እነርሱን የመደገፍ ግዴታ አለባቸው (ሮሜ 15:26-27)። ጳውሎስም ገንዘብ ስለማዋጣት በዋንኞቹ መልዕክቶቹ ውስጥ ዳስሶታል፤ የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያንም በዚህ እንድትሳተፍ አበክሮ ይመክራል (1ቆሮ 16:1-4፣ 2 ቆሮ 8-9)። ይህም መዋጮ ያስፈለገበት ምክንያት ምናልባትም ከአይሁድ ማህብረሰብ በደረሰባቸው ጥላቻና ስደት የተነሳ ለተቸገሩ በኢየሩሳሌም ላሉ ክርስቲያኖች ማህበራዊ ፍላጎቶች ድጋፍ ይውል ዘንድ ነው። ከዚያም ባለፈ ይህ ድጋፍ በጳውሎስ በተመሰረቱት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ እንደ አንድነትና ፍቅር ምልክት በመሆን ያገለግላል። አብዛኞቹ የእነዚህ አብያተክርስቲያናት ምዕመናን እጅግ በጣም ድሆች ቢሆኑም (1 ቆሮ 1:26-28) ጳውሎስ ግን በወንጌል ስላገኙት የልግስና ጥልቀት አጽንኦት ሲሰጥ እንመለከታለን “ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው” (2ቆሮ 6:10)። ጳውሎስ መስጠትን ለማበረታታት ሰፋ ባለ አውድ ‘ባለጠጋው’ ኢየሱስ ‘ደሃ’ ሆነ - ስጋ የመልበሱ ማጣቀሻ (ፊሊ 2:6) - አማኞች በእርሱ ባለጠጋ ሆነው ለሌሎች ያካፍሉ ዘንድ። ኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ የእሴት መለኪያ ሰጥቷል (ፊልጵ 3:8) ስለዚህ የወንጌል ውዱ ነገር ለድሆች ማካፈል ነው (1ጢሞ 6:17-19)።

4

~Hans Kvalbein. “Poverty.” The New Dictionary of Biblical Theology. T. D. Alexander, ed. (electronic ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2001.

ሀ / የእግዚአብሔር ልብ የተገለጠው አገልግሎቱን ሲጀምር የኢየሱስ መሲሕነት በታወጀበት ወቅት ነው (የናዝሬቱ ኢየሱስ የመክፈቻ ስብከት) ፣ ሉቃስ 4.16-21 ፡፡

1. ኢየሱስ ለድሆች ወንጌልን ለመስበክ አገልግሎቱ በእግዚአብሔር የተቀባ መሲህ ነው ፣ በመጀመሪያ የገዛ ወንድሙን ስምዖንን አገኘና “መሲሑን አገኘነው” አለው (ትርጉሙም ክርስቶስ ማለት ነው)፡፡

2. ይህም የጽድቅ ቅባት ነው ፣ መዝ. 45.7 ፣ ዝ.ከ. ዕብ. 1.9.

Made with FlippingBook - Online catalogs