Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 8 7
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
በግልጽ ሰለታየው የመንግስቱ ሰላም ዛሬም በእኛ ህይወትና አገልግሎት ውስጥ በምን መልኩ ይገለጥ ዘንድ አግዚአብሔር እንደሚፈልግ አስብ፡፡ እንደተለመደው ሁልጊዜም መልሶችህ አጭርና ግልጽ ይሁኑ፣ እንደ አስፈላጊነቱም በመጽሐፍ ቅዱስ አስደግፍ፡፡ 1. ኢየሱስ እንደ አዲሱ የእግዚአብሔር መንግስት ማህበረሰብ ከቤተክርስቲያን ጋር ያለው ግንኙነት ምንድነው? 2. የኢየሱስ መሲሀዊ ሚና በድሆች ዘንድ የተጀመረው የተረጋገጠውና የተለየው እንዴት ነው? የቤተክርስትያን ስራ ውስጥ ለድሆች መስጠት ቅድሚያ ይህ ለእኛ ምን ይጠቅመናል? 3. ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግስት ማህበረሰብ ናት ማለት ምን ማለት ነው? የክርስቶስ አካል እንደመሆኗ ዛሬም በአለም ላይ የክርስቶስን አገልግሎት እንድትመስልና እንድትፈጽም የተጠራችው እንዴት ነው? ቤተክርስቲያን በስራዋ በቃልዋና በምስክርነትዋ ዛሬም በአለም ላይ ስለሚመጣው ዘመን የህይወት ምስክር የምትሆነው እንዴት ነው? 4. ከመንፈስ ቅዱስ እንደተቀበለችው በቤተክርስትያን ተልዕኮ አማካኝነት የእግዚአብሔር ሰላም (ሻሎም) በምድር ላይ ይገለጣል ማለት የምንችለው በምን መልኩ ነው? 5. ቤተክርስቲያን ለመንግስት ምስክርና ትሆን ዘንድ ለችግረኞች (በተለይም ለመበለቶች፣ አባት ለሌላቸውና ለድሆች) የሚደረግ ልግስናና መስተንግዶ ለምን አስፈላጊ ሆነ? 6. የእግዚአብሔር ህዝብ በህብረተሰቡ ውስጥ ላሉ ድሆችና ድምጽ አልባዎች ጠበቃ መሆን የሚችሉት በምንድነው? የእንደዚህ ዓይነቱ የጥብቅና አገልግሎት ባህርያት ምንድናቸው? ለድሆች “ክፍተቱን መሙላት” የእውነተኛ ክርሰቲያናዊ ተልዕኮ መለያ ምልክት ነው የምንለው ለምንድነው? 7. ሁልጊዜም ከድሆች ጋር በምናደርጋቸው ግንኙነቶች ሁሉ ልናከብራቸው እንጂ ልንገፋቸው የማይገባው ለምንድነው? ድሆችን የሚያገለግሉ ሰዎች እግዚአብሔር የድሆችን ሁኔታ ለውጦ በመንግስቱ መስፋፋት ውስጥ ዋና አስተዋጽኦ አድራጊዎች ሊያደርጋቸው በእግዚአብሔር ችሎታ ላይ መተማመናቸው በጣም አስፈላጊ ነው የምንለው በምን መልኩ ነው? 8. “ቤተክርስቲያን ልክ እግዚአብሔር ድሆችን በመረጠበት መሰረት ልታያቸው ይገባል” የሚለውን ዓረፍተ ነገር አብራራ፡፡ እግዚአብሔር ድሆችን በእምነት ባለጠጎች ይሆኑ ዘንድ መርጧቸዋል (ያዕቆብ2፡5) የምንለው በምን መልኩ ነው? ለምንድነው ሁልጊዜ ለመጻተኞችና ለእስረኞች ቸርነትን ማሳየት ያለብን? 9. ለድሆች የምናደርገው እንክብካቤና የምንሰጣቸው አገልግሎት ዝም ብሎ ከላይ ያሉ ፍላጎቶቻቸውን ከማሟላት ባለፈ ለእነርሱ ፍትሀዊ ሁኔታ ወደ መፍጠር የሚመሩ የመዋቅርና ግንኙነት ለውጦችን የሚያመጡ መሆን የሚኖርባቸው ለምንድነው? 10. ድሆችን በእግዚአብሔር የሻሎምመለኪያ መሰረት መረዳት “የብልጽግና ወንጌል” የተሻለው ትርጓሜ የሚሆነው ለምንድነው? እኛን ወክሎ ምን እንደሚያደርግልን መተማመን እንችላለን፡፡
4
Made with FlippingBook - Online catalogs