Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 1 9

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋ የብዙዎችን ልብና አዕምሮ ለመንካት ሲባል ችላ ተብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለው ስነ ምግባራዊ ትምህርትና በቀጥታ ለቀረበው ስነ መለኮታዊ ይዘት የተሰጠው ትኩረት ባህልን በተሳሳተ መነገድ ከመረዳት የመጣ ይመስልሃል? አንተ ምን ይመስልሃል -ባህል ትኩረታቸውንና ዕይታቸውን የሚይዘ ታሪክ እየፈለገ ነው ወይስ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚችል ማብረሪያ? አብራራ

በዚህ ዘመን ማንም ቃሉን አይጠብቅም የተስፋን ቃል እንደቁምነገር በማይወስዱት ህብረተሰብ ውስጥ እንዴት የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ግልጽና አሳማኝ ማድረግ እንችላለን? ቃል ኪዳኖች አስገራሚ በሆነ መንገድ ሲበሰሩ እየተመለከትን ነው፤ የጋብቻ ቃል ኪዳኖች በአስፈሪ መነገድ በፍቺ እተጠናቀቁ ነው፤ ፖለቲከኞች በሙስና ምክንያቶች ቃል ኪዳናቸውን ይሰብራሉ፤ ሰባኪያን ስለ አሳፋሪው የለሊት ስራቸው (ከተያዙ ብቻ) የፀፀት የአዞ እነባቸውን ሲያፈሱ ይታያሉ፡፡ በዚህ ዘመን ቃልኪዳንን የመጠበቅን ዋጋና ኃይል የተገነዘቡ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ይመስላሉ፡፡ ይሁን እንጂ የክርስትና እምነት ሙሉ በሙሉ የተመሰረተው የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል አስፈላጊነትና የተስፋ ቃሉንም በክርሰቶስ በኩል መፈጸሙን በመገንዘብ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ እኛ እንዳለንበት አይነት ህብረተሰብ ውስጥ የተስፋ ቃልም መስጠትና መጠበቅ የክርስትናን እምነት ከመረዳት አንጻርና አገልግሎትና ሚሽንን ከማከናወን አንፃር የሚኖረው ተፅዕኖ ምን ይመስላል? ህብረተሰባችን ውስጥ ያለው ታማኝነት የጎደለው አኗኗር እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ባደረገልን ማዳን ያሳየውን ታማኝነት እንድንረዳና እንድናደንቅ ተጽዕኖ ሳድራል ብለህ ታምናለህ? አብራራ

3

1

የክርስቲያን ሚሽን ራዕይና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት - ክፍል1 ክፍል 1: ሚሽን እንደ ሁል ጊዜ ክስትት

CONTENT

ሬቨረንድ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ

ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትና ስራ እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለሰው ልጆች ሁሉ ያረገውን ማዳን እና ቤዛነት ማወጅ ነው፡፡ ይህን ከእግዚአብሔር አንጻር ስንመለከተው ከዘመን መጀመር አስቀድሞ ከዘመን ፍጻሜ በኋላ ድረስ እግዚአብሔር ስላሴ ነገሮችን ሁሉ ለራሱ ክብርና ለእኛ ጥቅም በሚሆን ሚሽን ላይ እንዳለ እንረዳለን፡፡ ለዚህም ሚሽን እንደ ሁል ጊዜ ክስተት ለተሰኘ ክፍል አላማችን የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት እንድንችል ነው:- • “ፕሮሌጎሜና” ማለት “የመጀመሪያው ቃል” ማለት ሲሆን ለሚሽንም ፕሮሌጎሜና መጀመር ያለበት እግዚአብሔር በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርሰቶስ አማካኝነት በዚህ ምድር ላይ ሚሰራውን ስራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕይታ መመልከት ነው፡፡

የክፍል 1 አጭር ማብራሪያ

Made with FlippingBook - Online catalogs