Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

2 0 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

• ሚሽን “እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትና ስራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት ለሰው ልጆች ሁሉ ያዘጋጀው የድነትና የቤዛነት ዓዋጅ” እንደሆነ እንደሆነ መተርጎም እንችላለን። • መጽሐፍ ቅዱሳዊው የሚሽን መረዳት ከቅዱሳት መጽሐፍት የሚቀዱ ነጥቦችን አጠቃሎ ይይዛል፡፡ ሚሽን መመስረት ያለበት ስለ እግዚአብሔርና ለፍጥረት ሁሉ ስላለው አላማ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ በመያዝ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊው የሚሽን ምልከታ መመስረት ያለበት መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ስለ ኢየሱስ ማንነትና ስራ በሚናገረው ላይ ሆኖ ይህም በምስል፣ በስእሎች እና በታሪኮች መተረክ ያስፈልገዋል፡፡ • አራቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሚሽን ማዕቀፎች/ምስሎች ማለትም ሚሽን እንደ ዘወትር ክስተት (በታሪኩ ውስጥ እግዚአብሔር እንደ ዋና ገፀ ባህሪ) ፤ እንደ መለኮታዊ ቃል ኪዳን ውሳኔ (የእግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ኪዳን መጠበቅ)፤ እንደ ዘመናት የፍቅር ግንኙነት እግዚአብሔር ለተዋጀው ህዝቡ እንደ ሙሽራ) እና እንደ ሽፍቶች ጦርነት (እግዚአብሔር በፍጥረት አለም ላይ መንግስቱን በ ድጋሚ እንደሚመሰርት ጦረኛ) እንገነዘባለን፡፡ • ከዘመን በፊት (የእግዚአብሔር ቅድመ ህልውና እና አላማ ፣ የአመፃን ምስጢርና የኢ ፍትሃዊነትን ኃይል የሚያሳይ)፤ የጊዜ መጀመሪያ (የአጽናፈ አለሙንና የሰው ልጅ ፍጥረትን ውድቀትና እርግማን ፕሮቶኢቫንጌሊየምን፤ የኤደን መጨረሻ፤ የሞትን አገዛዝና የመጀመሪያዎቹን የጸጋ ምልክቶች ያጠቃልላል)፤ የጊዜ መገለጥ (አብርሃማዊውን ተስፋ፣ ዘጸአትን፣ የመሬትን ምርኮ፣ የከተማ - መቅደስ - ዙፋን፣ የግዞት እና የቅሬታዎችን መመለስ ያጠቃልላል።) • ስለዘመንፍጻሜየማይታጠፈውየእግዚአብሔርተስፋ፤ የኢየሱስንስጋመልበስ፤ የመንግስቱን መገለጥ፤ የኢየሱስን ህማማት፤ ሞት፤ ትንሳኤና እርገት ያጠቃልላል፡፡ የመጨረሻው ዘመን ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ፤ የቤተክርስትያንን ተሀድሶ፤ የአህዛብን መካተትና የአለማቀፋዊውን ሚሽን ያጠቃልላል፡፡ • የዘመን ፍጻሜ (የአለም አቀፉን ስብከተ ወንጌል ማብቃት፤ የቤተክርስተያንን ክህደት፤ የታላቁን መከራ፤ ፓሩሲያን፤ በምድር ላይ የክርስቶስ አገዛዝ መምጣትን፤ ታላቁን ነጩን ዙፋን፤ የእሳት ባህሩንና የኢየሱስ ክርስቶስ መንግስቱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠትን ያጠቃልላል)፡፡ ከዘመን ፍጻሜ በኋላ (አዲሱን ሰማይና አዲሱን ምድር፣ የአዲሲቷን ኢየሩሳሌም የመታደስ ዘመን እና ሊመጣ ስላለው ዘመን ያጠቃልላል።) • የእግዚአብሔር ሉአላዊ አላማ የሰው ልጆችን ታሪክ እንደሚጽፍ፤ በመለኮታዊ የታሪክ ሂደት ውስጥ እግዚአብሔር እንደ ዋና ገጸ ባህሪ መሆን፤ ሚሽንን በዘመን መጀመሪያ የጠፋውን እንደ ማደስና፤ እግዚአብሔር የሰጠንን ድርሻ ለመወጣት አህዛብን ሁሉ ደቀ መዛሙርት በማድረግ ሚሽን እንደ ሁልጊዜ ክስትት የሚኖረውን ማዕቀፍ ያስረዳል፡፡

1

Made with FlippingBook - Online catalogs