Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 2 1

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ቪድዮ ሴግመንት 1 ዝርዝር

I. ፕሮሌጎሜና ለሚሽን: ትልቁ ምስል

የእግዚአብሔር ሚሽን ስለክርስቶስ አካል ነው፡፡ ሁሉን አቀፍ አካል የተሰቀለው ክርስቶስ ስጋና ኤክሌሽያዊው አካል (ቤተ ክርስትያን) መነጣጠል አይችሉም፡፡ ለዚህ ምስል በርካታ የሆኑ ውጤቶችን ልናገኝ እንችላለን፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ቀደም ባሉ መልዕክቶች፤ በተለይም በቆሮንቶስና በሮሜ መጻህፍት ትኩረቱ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን አንድነትን በተሰቀለውና ህያው በሆነው በክርስቶስ ላይ ማድረጉ ነው፡፡ ነገር ግን በኋለኞቹ መልእክቶች ቆላስይስና ኤፌሶን ይሄ ምስል ሰፋ ብሎ ዓለም አቀፉን ቤተክርስትያን ሲያቅፍ እንመለከታለን (ቆላ1፡48፣2፡19 ፤ ኤፌ1፡22-23፣4፡16)። ክርስቶስ የአካሉ “ራስ” ነው፤ ይህ ደግሞ ከአንድ አጥቢያ እምነት ማህበረሰብ የሰፋ ነው፡፡ ይህ የምስል ለውጥ ደግሞ እጅግ አስፈላጊ የሚሆንበት ምክንያት ቤተክርስቲያን “ፍሬ እንድታፈራ እና እንድታድግ… በአለም ሁሉ ላይ” (ቆላ 1፡6) የሚሽን ጥሪ መቀበሏንና ይህም ጥሪ የአጥቢያን የእምነት ማህበረሰብም የሚያንጽ እንደሆነ እንድንገነዘብ ይረዳናል፡፡

1

~ Leland Ryken. Dictionary of Biblical Imagery. (electronic ed.) Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2000, p. 109.

ሀ / ትርጓሜ: - ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እና ሥራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለሰው ልጆች ሁሉ ያደረገውን ማዳን እና ቤዛነት ማወጅ ነው።

1. የእግዚአብሔር የማዳን እና የመቤዠት አዋጅ - ሚሽን የእግዚአብሔርን ዓላማዎች እና የእርሱን የጸጋ እና የይቅርታ አቅርቦትን ይመለከታል ፡፡

ሀ. 2 ጢሞ. 1.8-10

ለ. ሮሜ. 5.8

ሐ. ኤፌ. 1.6-8

መ. ኤፌ. 2.7

Made with FlippingBook - Online catalogs