Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 9 1
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
አቅመ ደካሞች መልካምን ለማድረግ ባለ ቁርጠኝነት እና በተለይም በእግዚአብሄር ቤት ያሉ ጉዳተኞችን ተግባራዊ ፍላጎት ለማሟላት በሚደረግ ጥረት ውስጥ የሚገለጥ ነው፡ ³ ቤተክርስትያን በእኛና በአለም ውስጥ ፍትህና እኩልነትን መሻት ይኖርባታል፡፡ መሰረታዊ ፍላጎታችን ለመማሟላት ብቻ ሳይሆን ወደ ፍትሀዊነት የሚወስዱን መዋቅሮችና ግንኙነቶች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እንተጋለን፡፡ በብሉይ ኪዳን ጌታ የኪዳኑን ማህበረሰብ ለድሆች ሀብት እንዲሰጥ እንደተጠበቀበት እንዲሁ ደግሞ ቤተክርስትያን በሁሉም ግንኙነቶች እና ጉዳዮች ውስጥ በድሆች ስም ፍትህና እኩልነት በመፈለግ እውነተኛውን የብልጽግና ወንጌል መኖር አለበት፡፡
አሁን አብረውህ ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመሆን ስለ ክርስቲያን ሚሽን እና ድሆች የምትወያበት ሰአት ነው፡፡ ይህ አንተ ስለ ድሆች እና ስለ ሚሽን ከተማርከው ትምህርት አንጻር ያለህን ዕይታ የምትወያይበት እድል ነው - እዚህ ጋር ቅድሚያ የሚሰጠው ለጥያቄዎችህ ነው፤ አንተ ያሉህን ጥያቄዎችና ጉዳዮች ቀጥሎ ከቀረቡት ጥያቄዎች አንጻር ለመመልከት ሞክር:
የተማሪው ትግበራና አንድምታዎች
CASE STUDIES
የካትሪና ችግር መላው አሜሪካ ካትሪና ወጀብ ደቡባዊውን የኒው ኦርሊያን ከተማ ስትመታ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማ ድሆች ያለ ምግብ ፣ ውሃ እና ዕርዳታ ተጎድተዋል ፡፡ እጅግ በጣም አዛውንት ፣ ወጣት እና ችግረኛ ሰዎች ከደረጃ በታች በሆነ የኑሮ ሁኔታ ሲሰቃዩ ማየቱ በጣም አሳዛኝ ነበር ፡፡ ምንም ዓይነት ማመካኛ ፣ ማላከክ ወይም “በሚቀጥለው ጊዜ” የሚል የተስፋ ቃል ያለ ምንም ሥራ ፣ የገንዘብ ድጋፍ ወይም በሕይወታቸው ውስጥ ስለሚቀጥሉት እርምጃዎች ምንም ሳያውቁ ለሚሰቃዩት ብዙዎች እፎይታ ወይም ማጽናኛ ሊያመጣላቸው አይችልም ፡፡ ለድሆች አገልግሎት አለመስጠት ብዙ ምክንያቶች ተሰጥተዋል - “ህዝቡ ድሃ እና ጥቁር ነበር ፣ እናም ይህ ህዝብ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ብዙም ተቆጥሮ አያውቅም ፣” “እነዚህ ሰዎች እድሉ እያላቸው ከተማውን ለቀው እንዲወጡ የቀረበውን ጥሪ አልሰሙም ፡፡” “ የመንግሥት ኤጀንሲዎች ችግሩ ከደረሰባቸው በኋላ መፍትሔ ለመስጠት በጣም ይዘገዩ ነበር” - እነዚህና ሌሎች ምክንያቶች በብዙዎች ሕይወት ላይ ጉዳት ያደረሰውን አስከፊ የተፈጥሮ አደጋ ትርጉም እንዲሰጥ አድርገዋል ፡፡ ስለ ጥፋት እና የተፈጥሮ አደጋ ሊኖር በሚችልበት ጊዜ በእነዚህ ክስተቶች ወቅት እና ከዚያ በኋላ ለእንክብካቤው ተጠያቂው ማን ነው? - ህዝቡ ራሱ ፣ የመንግስት ኤጀንሲዎች እና ባለሥልጣናት ፣ ቤተክርስቲያን እና ሌሎች ረዳት ኤጄንሲዎች ፣ ወይስ ሁሉም፣ በሆነ አንድ ዓይነት ጥምረት ወይስ ሌላ? የነጻነት ስነ-መለኮት እና ድሆች የነፃነት ሥነ-መለኮት በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን እጅግ አስፈላጊ ሥነ-መለኮታዊ እድገት ነው ማለት ይቻላል ፡፡ የተለያዩ የነፃነት ሥነ-መለኮት ዓይነቶች የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር የድሆች እና የተጨቆኑት አምላክ መሆኑን ተቀዳሚ ትኩረታቸው ያደርጋሉ ፡፡ ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘቶች እና ሥነ-መለኮታዊ ትምህርቶች ይህንን የእግዚአብሔር መሠረታዊ ማንነት ከድሆች ፣ ከተገለሉ ፣
1
4
2
Made with FlippingBook - Online catalogs