Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
1 9 0 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
³ ለእግዚአብሔር የኪዳን ማህብረሰብ የተቀመጡት መመዘኛዎች አንድምታ ግልፅ ነው፤ የእግዚአብሔር ህዝቦች በሚያደርጉት ነገር ሁሉ እግዚአብሄር ከድሃ አደጎች ጎን መቆሙን ማንጸባረቅ ይኖርባቸዋል፤እግዚአብሄር በዘጸአት ከደረገላቸው ነጻ መውጣት በመነሳት ከሰዎች ሁሉ ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ሁሉ የጌታን ሻሎም ያሰዩ ዘንድ ነው፡፡ ³ የኢየሱስ ቤተክርስትያንን ማግኘት በእግዚአብሄር ህዝቦች መካከል ይህን ሰላም ለማሳየት የተጠራው አዲሱ የእግዚአብሄር የኪዳን ማህረበሰብ ነው፡፡ ³ የኢየሱስ መሲህነት በርሱ ትኩረት፣ጥሪ፣አገልግሎትናአላማ ውስጥ ለሚገኙና ለተጨቆኑ ፈውስን ለድሆች ወንጌልን በመስበክ ውስጥ ጀምሯል ፤ ይህም ለድሆች ወንጌልን በመስበክና ፍትህን በማድረግ በመጥምቁ ዮሀንስ በኩል መሲህነቱ ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም ድሆችን ከተንከባከቡበት መንገድ በመነሳት እነዴት ለሌሎች መዳን እንደሆነና ከሁሉ ከሚያንሱት( ከተራቡት፣ከተጠሙት፣ከአመጸኞች፣ከታረዙት፣ከታመሙትና ከታሰሩት)ጋር ያለመከልከል እንዴት እንደሆነ ማየት እንችላለን፡፡ ³ የክርስቶስ የመንግስቱ ማህበረሰብ በሆነችው በቤተክርስትያንና በዚህ የመንግስቲ ማህበረሰብ ውስጥ ስላለች ምህረትንና ፍትህን የመግለጥ ድረሻ ያላቸውን ግንኙነት ማየት ይቻላል፡፡ ይህም ማለት የተጠራቸው በአለም ውስጥ የክርስቶስ አካል ለድሆች ወንጌልን ለመስበክ እና ለድሆች በሚደረግ ፍትህ አማካኝነት ስለሚመጣው ዘመን አዲስ ህይወት ማሰያ ለመሆን ነው፡፡ በተጨማሪም በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በታጠቀ ችወ የቤተክርስትያን ህይወት እና ተልዕኮ አማካኝነት የእግዚአብሄር ብሉይ ኪዳናዊው የኪዳን ማህበረሰብ ዘንድ ይህ ሰላም(ሻሎም) ታይቷል እንዲሁም ተተግብሯል፡፡ ³ አዲሱ ማህበረሰብ ውስጥ ላሉት ችግሮች በተለይ ለመበለቶች፣ላጅ አልባዎችና ድሆች እንዲሁም በመከራ እና በችግር ጊዜያት ለሌሎች አብያተ ክርስትያናት ስለሚያደርገው ስር ነቀል የሆነ ልግስናና እንከብካቤ ማሳየት አለበት፡፡ ³ ቤተክርስትን እግዚአብሔር ድሆችን በመረጣቸው መሰረት ተቀብላ መንከባከብ አለባት የሚለውን ጨምሪ ሌሎችንም የኢህ ምልከታ አንድታዎች ጠቅለል እድርገህ ማቅረብ እንችላለን፡፡ (ማለትም ጉዳያቸውን መከላከል፣ መብታቸውን ማስጠበቅ፣ ለእነርሱ ጥብቅና መቆምና በቤተክርስጥያን ውስጥ አድሎ አለማሳየት)፤ የድሆችን ፍላጎት ለማሟላት ያለንን በማካፈል፣መጻተኞችን እስረኞችን በመቀበል እና እኛም የተካፈልነውን ፍቅር ለሌሎች በማካፈል ለጋስና እንግዳ ተቀባይ ልንሆን ያስፈልገናል፡፡) ³ ወንጌልን ለድሆች መስበክን ጨምሮ ለአርባን ሚሽን የቤተክርስትንን አዲሱ የማህበረሰብ አንደምታዎች መገነዘብ ይኖርብናል፡፡ ይህም ድሆችን በእግዚአብሄር እንደተመረጡ አይቶ ማክበር፤ ኢየሱስ ራሱ አብሮአቸው የቆመና በፍትህና በርህራሄ የሚመለከታቸው መሆናቸውን መገንዘብ ነው፡፡ ³ አዲሱ ማህበረሰብ የእውነተኛው ከርስትያናዊ ተልእኮ ምልክት ወደ ሆነው ለድሀ አደጎች ጥብቅና ለመቆም ተጠርቷል፡፡ ይህ ተሟጋችነት በአካሉ አባላት መካከል በመደብና በልዩነት ላይ ልተመሰረተና በወገንተኝነትና ጎጠኝነት ላይ ያልሆነ ነው፤ነገር ግን በአንጻሩ ለድሆችና
4
Made with FlippingBook - Online catalogs