Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 1 8 9
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
³ የድሆች ጽንሰ ሃሳብ የተመሰረተው በመጽሐፍ ቅዱሳዊው የሻሎም ወይም ሙሉነት ጽንሰ ሀሳብ ላይ ነው፡፡ ሻሎም የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ትረጓሜውም ከእግዚአብሄር ጋር እና አርስ በእርስ ባለ ህብረት ውስጥ ያለ የሰው ማህበረሰባዊ ሙሉነት ማለት ነው፡፡ ³ መጽሐፍ ቅዱሳዊው የሻሎምን አካላት የጤናና ደህንነት እና ጥበቃን በጎረቤት መካከል ያለን መልካም ግንኙነት፤ብቃትን ብልጽግናና እና የቁሰቀዊ ፍላጎት መሟላትን እና የክፋትና የግጭትን አለመኖር እውነተኛ ሰላምን ጨምሮ ያሉትን ልምምዶች ያካትታሉ፡፡ ይህም ሰላምን እንደ እግዚአብሄር ቸርነት የተደረገ ስጦታን ይመለከታል፤የሰላም ንጉስ ከሆነው ከመሲሁ መምጣት ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ ³ ድህነት የእግዚአብሄርን ሻሎም መካድ ሲሆን የእርሱ በረከት ድህነትን ለመከላከል እንደሆነ፤ለኪዳኑ ህዝብ የተሰጡት ትዕዛዝ በያህዌ ህዝብ ዘንድ ፍትህና ጽድቅን ለማረጋገጥ የተቀየሱ መሆናቸውን እና ለትእዛዛቱ የሚያሳዩት ታማኝነት እንዴት እስራኤላውያን ቃሉን እሰከታዘዙትና ፍቃዱን እሰከተከሉ ድረስ መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ³ እግዚአብሄር ከድሀ አደጎች ጋር ይቆማል ማለትም የሚጨቁናቸው ይቀጣ ዘንድ ድሆችን ከመሬት አንስቶ መባረኩን እና ለእርሱ የተጨቆኑት፣የተጠቁትነ ለድሆች ግድ እንደሚለው እንዲሁ እነርሱ ደግሞ ግድ ይላቸው ዘንድ ይፈልጋል፡፡ የዘጸዓቱ ክስተት እንዴት እግዚአብሄር ከድሆችና ከተጨቆኑት ጋር እንደሚቆም ያሳያል፣የቅድስና ነጸብራቅ፣የፍትና የምህረት ምሳሌ እና ለአህዛብ መልክት እንዲሆን ለጠራው የኪዳን ህዝብ የፍትህ ልቡን በማሳየት ተገልጧል፡፡ ³ የተፈጥሮ አደጋና ጥፋት (ለምሳሌ ረሀብ፣ድርቅ፣አውሎነፋስ ወ.ዘ.ተ)፣ የግል ስንፍናና ስልቹነት (ለምሳሌ መጥፎ ውሳኔዎች፣ ስለ-ምግባር የጎደለው ባህርይ፣ ስራ ፈትነት፣ ልበ ደንዳናነት፣ ወ.ዘ.ተ) እና ጭቆናና ግፍ (ለምሳሌ በደል፣ ብዝበዛ፣ የደሞዝ ማጭበርበር ወዘተ) እነዚህን ጨምሮ የድህነት መንስኤዎች መሆናቸውን መጽሀፍ ቅዱስ ይነግረናል። ድሀ አደግ የሚለው ቃል በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ የተለያየ ትርጓሜ ከሚሰጣቸው ጽንሰ ሀሳቦች ጋር ተያይዞ ይገኛል፡፡ ከነዚህም መበለት ወላጅ አልባ እና እንግዳ ይገኙበታል፡፡ ³ ድሆችን እንደ ምስክሮች በቸርነትና በፍትህ ከመያዝ አንጻር እግዚአብሄር ለኪዳን ህዝቡ የሰጠውን መስፈርት አለ፤ ይህም በህግ የተካተተ የፍትህ ጉዳዮችን፣ልድሆች የሚደረግ ልዩ አቅርቦት፣ያለ እድሎ የሚደረግ በሀቅና በትክክለኝነት ላይ የተመሰረተ፣ሁሉም ጉዳዮች መመዘኛዎችና ሽግግሮች በፍትሀዊ መንገድ የሚካሄድበት እንዲሁም ድሆች ከእርሻችና ከወይን ምርቶች በየሰባት አመቱ ድርሻ የሚያገኙበት ነው፡፡ ³ የእግዚአብሀር ህዝቦች ድሆችን መቅረጥ ተከልክለዋል፣ ለእለታዊ ስራ ተገቢውን ክፍያ መስጠት(ማለትም ደሞዝ መከፈል ያለበት በእለተና ያለምን ጭቆናና ማጭበርበር መካሄድ አለበት)፣ድሆችን የመቀበልን ልምምድ(በተዘረጋ እጅ) እና ሀብቶችን ለድሆች ማስቀመጥ(በህብረተሰቡ ውስጥ የሚገኙ እጅግ ችግረኛ ለሆኑ ሰዎች ከአስራትና ከመባ ድረሻ ማካፈል) አለባቸው፡፡ ድሆች በኢዮቤልዩ አመት በሚካሄዱ በሁሉም አይነት ክብረበአላት ላይ መሳተፍና ንብረታቸውን ማደስ መቻላቸውን ጨምሮ ያሉ መመዘኛዎች ተዘርዝረዋል፡፡
4
Made with FlippingBook - Online catalogs