Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

1 9 6 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ASSIGNMENTS

የቤት ስራ የለም

የቃል ጥናት ጥቅስ

የቤት ስራ የለም

የንባብ መልመጃ

አሁን የሚኒስትሪ ፕሮጀክትህ እና የኤክሴጀሲስ ፕሮጀክትህ በአስተማሪህ ተገምግሞና ተወስኖ ተቀባይነት ሊኖረው ይገባል ፡፡ የተሰጡትን ሥራዎች በጊዜው ማስረከብ ትችል ዘንድ አስቀድመህ ማቀድህን አረጋግጥ።

ሌሎች የቤት ስራዎች

የመጨረሻው በቤት የሚሰራ ፈተና ይሆናል ፤ ከመጀመሪያዎቹ ሶስት ፈተናዎች የተወሰዱ ጥያቄዎችን ፣ ከዚህ ትምህርት የተገኙ አዳዲስ ጥያቄዎችን እና አጫጭር ምላሾችን የሚጠይቁ የጹሑፍ ጥያቄዎችንም ያጠቃልላል ፡፡ እንዲሁም በፈተናው ላይ ለትምህርቱ የተሰጡትን የቃል ጥናት ጥቅሶች በማንበብ ወይም በመፃፍ ላይ መዘጋጀት አለብህ፡፡ ፈተናህን ስታጠናቅቅ እባክህ ለመምህርህ በማሳወቅ ቅጅህን ማግኘቱን አረጋግጥ። ማስታወሻ - የመጨረሻውን ፈተና ካልወሰድክ እና ለአስተማሪህ የተሰጡትን የቤት ስራዎች ሁሉ (የሚኒስትሪ ኘሮጀክት ፣ የኤክሴጀሲስ ፕሮጀክት እና የመጨረሻ ፈተና) ባግባቡ ካላጠናቀቅህ በዚህ ሞጁል የሚኖርህን አጠቃላይ ውጤት ማስላት አይቻልም። በዚህ ትምህርት ውስጥ የድህነትን ፅንሰ-ሀሳብ በሻሎም ፅንሰ-ሀሳብ ወይም የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ማህበረሰብ ምሉዕነት መነጽር ውስጥ ተመልክተናል ፡፡ እስራኤል ምንም እንኳን የእርሱን ፍትህ እና ጽድቅ ለማሳየት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ጥሪ በመጠበቅ ታማኝነታቷን ብታጣም በቃል ኪዳኑ ውስጥ ያለው የሻሎም ምስል ቆንጆ እና እውነተኛ ነበር ፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ከችግረኞች እና ከድሆች ጋር በመቆም የሚታወቅ ሲሆን ሕዝቦቹም ለአሕዛብ ብርሃን እንደመሆናቸው እርስ በርሳቸው በሚያደርጉት ግንኙነት ያንን ሻሎም እንዲያሳዩ ይጠብቅባቸዋል ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ውስጥ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተሟልቶ አዲስ ማህበረሰብ በመንፈስ ቅዱስ ተወለዷል ፡፡ ቤተክርስቲያን አሁን በኢየሱስ መሥራችነት እና ራስነት አማካኝነት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ሲጠበቅ የነበረውን ሻሎም ትፈጽም ዘንድ ተጠርታለች። የእግዚአብሔርን መሲሐዊ ትንቢት የፈጸመ የተሰቃየው አገልጋይ እንደመሆኑ መጠን አሁን አዲስ ማኅበረሰብን ፈጥሯል - ቤተክርስቲያንን ፤ ተልእኮዋም የመንግሥቱን ምሥራች ለድሆች ማወጅ እና የዚያ መንግሥት ሕይወት አባላቱ እና ለሌሎችም ማሳየት ነው ፡፡ እኛ የቤተክርስቲያን አባላት እንደመሆናችን መጠን የእግዚአብሔርን መንግሥት ዛሬ በምድር ላይ ለማሳየት በጥሪያችን ላይ ስንነቃ የተልእኮው ዕይታ (እንደ ቅዱስ ድራማ ፣ እንደ መለኮታዊ ፍቅር ፣ እንደ ተስፋው ፍጻሜ እና እንደ ሽፍቶች ጦርነት) ግልጽ ሆኗል። በመሆኑም ዛሬ በዓለም ላይ ይህ ማሳያ ከሚያስፈልጋቸው ስፍራዎች ሁሉ ከተማዎች ለክርስቶስ እና ለመንግስቱ ህያው ምስክር ፍለጋ ይጮኻሉ ፡፡

የማጠቃለያ ፈተና ማስታወቂያ

4

ስለዚህ ትምህርት (ሞጁል) የመጨረሻ ቃል

Made with FlippingBook - Online catalogs