Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
3 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
እባክህ በነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመስጠት ሞክር፡፡ በዚህ ክፍል መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ሚሽን በመለከተ “ፕሮሌጎሜና” ወይም “የመጀመሪያ ቃል” እንደ ማዕቀፍ አቅርበናል፤ በተጨማሪም ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትና ስራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አማካኝነት ለሰው ልጆች ሁሉ ያደረገውን ማዳንና ቤዛነቱን ማወጅ እንደሆን ትረጓሜ ሰጥተናል፡፡ ይህን እንደ እግዚአብሔር ታሪክና ትዕይንት ስንመለከተው ገና ከዘመን መጀመሪያ በፊትም ሆነ ከዘመን ፍጻሜ ባሻገር አምላከ ስላሴ እንዴት እንደሚያደረገው እንገነዘባለን፡፡ እንግዲህ በዚህ ሞጁል (ትምህርት) ማከናወን የምንፈልገው “ትልቁ ምስል” የሆነውን የሚሽን ተፈጥሮ እንደሚወስንና የመጀመሪያውም ደረጃ በዚህ ክፍል ውስጥ የተካተቱትን ዋና ዋና ለመቃኘት ሞክር፡፡ መልሶችህን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አስደግፍ፡፡ 1. “ፕሮሌጎሜና” ማለት ምን ማለት ነው? እግዚአብሔር በናዝሬቱ ኢየሱስ በኩል በምድር ላይ ላለው ሚሽን የሚነሳውን “ፕሮሌጎሜና ሚሽን” የሚለው አተያይ ለምን ያስፈልገናል? 2. ለ”ሚሽን” ትርጓሜ ስጥ፤ ለመጽሐፍ ቅዱሳዊው የሚሽን ግንዛቤ የሚረዱን ዝርዝሮች ስለ ሚሽን ሊኖረን የሚገባውን እይታ ከራሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ መሆን ያለበት ለምንድነው? ለምን ከሚሽነሪዎችና የሚሽን ድርጅቶች አይሆንም? 3. መጽሐፍ ቅዱሳዊው ሚሽን ራሱ በኢየሱስ ማንነትና ስራ ላይ መመስረት ያለበትና መጽሐፍ ቅዱስ ሚሽንን ለማስረዳት የሚከተለውን ምስሎችን፣ ስእሎችን እና ታሪኮችን መጠቀም ያስፈልገው ለምንድነው? 4. አራቱ ዋና ዋና የስነመለኮታዊ ማዕቀፎች /ምስሎች ምንድር ናቸው? የእያንዳንዱን ትርጓሜ ስጥ፡፡ 5. የሁል ጊዜ ትዕይንት ዋና አካላት ዝርዝር በተለያዩ በተለይም ከዘመን በፊት፣ የዘመን ጅማሬና የዘመን መጠቅለል የተመለከቱትን እያንዳንዳቸውን ማዕከላዊ ነጥቦች በማንሳት ሚሽንን ከመረዳት አንጻር የሚኖራቸውን አንደምታ አስቀምጥ፡፡ 6. ሚሽን እንደ ሁልጊዜ ትዕይንት በዘመን ሙላት፣ በዘመን ፍጻሜ፣ በዘመን ሙላትና ከዘመናት ባሻገር ስላለው የእግዚአብሔር የማይጠፋ አላማ አንጻር አስረዳ፡፡ በተጨማሪም እያንዳንዳቸውን ማዕከላዊ ነጥቦች በማንሳት ከአለማቀፋዊው ሚሽን ጋር ስለሚኖራቸው ዝምድናና በዚያ ውስጥ ስለሚኖራቸው ድርሻ ምን እንደሆነ አስረዳ፡፡ 7. የሚሽን እንደሁልጊዜ ትእይንትማዕቀፍ የእግዚአብሔር ሉአላዊ አላማና በመለኮታዊ ድራማ ውስጥ የሚኖረውን ሚና እንዴት ያስረዳል? ይሀ ማዕቀፍ ሚሽንን በዘመን መጀመሪያ የጠፋውን መልሶ እንደማግኘት እና ደቀ መዛሙርት ማድረግን ደግሞ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ትዕይንት ውስጥ የራሳቸውን ድርሻ ማበርከት እንደሆነ እንድንረዳ እንዴት ያግዘናል?
መሸጋገሪያ 1
የተማሪው ጥያቄዎችና ምላሾች
1
ሚሲዮሎጂ መደበኛው የቤተክርስትያን ሚሽን ጥናት ነው፡፡ በስነ መለኮት ጥናት መስክ ውስጥ የሚመደብ ሆኖ በውስጡ በርከት ያሉ ዘርፎችን አቅፎ ይይዛል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱሳዊው ጥናት የቤተክርስትያን ሚሽን መሰረት “ሚሲዮ ዲ” (የእስራኤል አለም ሁሉ ብርሃን የመሆን ጥሪ) (ኢሳ 49፡6) እና ኢየሱስ ለሐዋርያቱ እስከ ምድር ዳር ድረስ ምስክሮቹ ይሆኑ ዘንድ
Made with FlippingBook - Online catalogs