Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 3 3

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

የሰጣቸው ተልእኮ (ማቴ 28፡18—20፣ሐዋ ሥራ 1፡8) እንደሆነ ያሳያል፡፡ የታሪክ ጥናት ማህበረሰቦችና ጥናቶች ላይ ያመጣውን ተጽዕኖ ይዳስሳል፡፡ ሲስተማቲክ ቲዎሎጂ የክርስትና እምነት ከአለማዊው ፍልስፍና ርዕዮተ አለም እንዲሁም ከሌሎች የእምነት ዘርፎች ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጠና ዘርፍ ነው፡፡ የስነ ምግባር ጥናቶችም የሚሲዮሎጂ አንድ አካል በመሆን ተካተዋል ቤተክርስቲያን ለሁለንተናዊው ህይወት የእግዚብሔርን ፍቃድ የማወጅ ኃላፊነት ስላለበት ፓስቶራል ቲዎሎጂ ለአዳዲስ ነፍሳት መመሪያ በመስጠት ከቤተክርስትያን ጋር እንዲዋሃዱ መንገዶች ይፈልጋል፡፡ ሚሲዮሎጂ ሰፊ እንደ መሆኑ መጠን ከሌሎች ስራዎች ጋር የሚኖረው ጥምረት ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ በሌላ አነጋገር እያንዳንዱ የስነመለኮት ገጽታ የማይታለፍ ሚሲዮናዊ አቅጣጫ አለው ምክንያቱም እያንዳንዱ ያለው ለቤተክርስቲያን ሚሽን ሲባል ነው። ~ J. A. Kirk. “Missiology.” The New Dictionary of Theology. S. B. Ferguson, ed. (electronic ed.). Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2000. p. 434.

1

የክርስትያን ሚሽን ራዕይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት: ክፍል 1

ሴግመንት 2፡ ሚሽን እንደ መለኮታዊው ተስፋ ቃል ፍጻሜ

ሬቨረንድ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ

ሚሽን እንደ መኮታዊ የተስፋ ቃል ፍጻሜ የእግዚአብሔርን ስራ ለአብርሃምና ዳዊት እንደገባላቸው ቃል ኪዳን መፈጸም አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳዊው የኪዳን ሚና ላይ እንደመመስረቱ ይህ ዋና ሃሳብ የሚነሳው እግዚአብሔር ለአብርሀም ከሰጠው ኪዳን ሲሆን፥ በልጆቹና በአባቶች ይጸናና በመቀጠልም በይሁዳ ነገድ ተለይቶ ይታወቃል፡፡ ይህ ትውልድን የመባረክ የዘር ተስፋ እግዚአብሔር ለዳዊት ከዙፋኑ ወራሽ እንደማይታጣ በገባለት ተስፋ ተብራርቶና ተስተጋብቶ እናገኘዋለን፡፡ እንግዲህ በተመሳሳይ በዚህ ዘመን እና በኢየሱስ ማንነት የአብርሀምና የዳዊት የተስፋ ቃል ተፈጽሟል፡፡ በተመሳሳይ በዚህ ዘመን በሚሽን አማካኝነት ወንጌል ሲታወጅ በመስቀሉ ስብከት አማካኝነት የአዲስ ህይወት ተስፋ ለሰዎች ሁሉ ተሰጥቷል፡፡ ለዚህ ሚሽን እንደ መለኮታዊው የተስፋ ቃል ፍጻሜ ለተሰኘ ሴግመንት አለማችን የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት ትችል ዘንድ ነው፡፡ • ሚሽንን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚያብራሩት አራት ዋነኛ ኃሳቦች ወይም ጭብጦች አንዱ ሚሽን እንደ መለኮታዊ የተስፋ ቃል ፍጻሜ የሚለው ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ስናየው ቃል ኪዳን ማለት በሁለት ወገኖች መካከል በግለሰቦች፣ በጎሳዎች ወይም ህዝቦች መካከል የሚደረግ የሚደረግ ስምምነት ሲሆን ይህም ስምምነት ለሁለቱም ወገኖች የሚገቡትን ግዴታና የሚያኙትን ጥቅም ያካትታል፡፡

የሴግመንት 2 ማጠቃለያ

Made with FlippingBook - Online catalogs