Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

3 4 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

• መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኪዳኖች የሚጋሯቸው የጋራ የሆኑ ባህሪያት ሲኖራቸው ይህም ውሎች እና ስምምነቶች በምስክሮች ፊት መካሄዳቸውን እና ውል መጣስ የሚያስከትለውን ውጤት (ማለትም ውሎችን መጣስ እንደ ከባድ ስነምግባራዊ ጥሰት ይቆጥራል) ያካትታል፡፡ ቃልኪዳኖች የሚሰጡት ስጦታ በመስጠት፣ ምግብ በመመገብና ብዙ ጊዜ ደግሞ የማስታወሻ ድንጋይ በማስቀመጥ ነው፡፡ የሚረጋገጡት ደግሞ በመስዋዕት በሚደረገግ መሃላ ነው፡፡ • ምናልባትም የመጽሐፍ ቅዱሰቀዊው ኪዳን ዋና ማሳያ የጋብቻ ስነ ስርዓት ሲሆን ሌላው ማሳያ ደግሞ የእስራኤል ታሪክ ውስጥ የምናየው ይሆናል፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሔር ከኖኅ ጋር ያደረገው ኪዳንና እግዚአብሔር በሲና ከእስራኤል ልጆች ጋር ያደረገው ኪዳን፡፡ የእግዚአብሔር ኪዳን በጠቅላለው በእግዚአብሔርና በግለሰቦች ወይም በህዝቡ መካከል በጥንቃቄ የሚደረግ ስምምነት ነው፡፡ • ሚሽን እንደ መለኮታዊ የተስፋ ቃል ፍጻሜ እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር በገባው ቃል ኪዳን ላይ ሊደገፍ ይችላል፤ ከሀገርና ከወገኖቹ ተለይቶ መውጣቱ፣ በዚህም የተነሳ የሚያገኘው የእግዚአብሔር በረከት፤ እግዚአብሄር ታላቅ ህዝብ ያደርገዋል፤ ስሙንም ታላቅ ያደርገዋል፣ የሚባርኩትን ይባርካል፥ የሚረግሙትንም ይረግማል፣ ከእርሱም የተነሳ አህዛብን ሁሉ ይባርካል፡፡ • እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠው ለአህዛብ የሚተርፍ የዘር ተስፋ የታደሰውና የተረጋገጠው በልጆቹ በይስሐቅና ያዕቆብ በኋላም መሲሁ በሚመጣበት ነገድ በይሁዳ ግልጽ ሆኖ ተለይቷል፡፡ ከይሁዳ ወገን የዳዊት ቤት ለአብርሃም የተገባው የንጉስ ዘር የሚመጣበት ለመሆን ተመርጧል፡፡ የዳዊትም ወራሽ ለዘላለም በእስራኤል ላይ ይነግሳል፣ ለአህዛብም በረከት ይሆናል፡፡ • እግዚአብሔር ለአብርሃምና ለዳዊት የሰጠው ተስፋ በአብርሃም ዘርነት እና የእግዚአብሔር አገዛዝ በሚመሰረትበት በዳዊት ልጅነት አማካኝነት በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት በኩል ተፈጽሟል፡፡ በኢየሱስ ሕይወት፣ ሞት፤ ትንሳኤና እርገት በኩል ደግሞ የእግዚአብሔር ኪዳን ተፈጽሟል፡፡ • ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ኪዳኑን የመጠበቁን የምስራች ማረጋገጥና ማወጅ ሲሆን ታላቁ ተልዕኮ ደግሞ ይህን የተፈጸመ ተስፋ ከእስራኤል ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ለሰው ልጆች ሁሉ የማወጅና የማስተማር ተልዕኮ ነው፡፡ • የሚሽን ዋና የልብ ትርታ የሚሆነው በናዝሬቱ ኢየሱስ አማካኝነት የዳዊት ተስፋ መፈጸም እንዲሁም ወንጌልን በማወጅ አማካኝነት ደግሞ በመስቀሉ ስብከት ለአህዛብ ሁሉ የተገባው ተስፋ ፍጻሜ ማግኘት ነው፡፡

1

Made with FlippingBook - Online catalogs