Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
4 8 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
³ የሚሽን ዋና የልብ ትርታ የሚሆነው በናዝሬቱ ኢየሱስ አማካኝነት የዳዊት ተስፋ መፈጸም እንዲሁም ወንጌልን በማወጅ አማካኝነት ደግሞ በመስቀሉ ስብከት ለአህዛብ ሁሉ የተገባው ተስፋ ፍጻሜ ማግኘት ነው፡፡
በዚህ ትምህርት ውስጥ የተካተቱትን ጭብጦች እና ማዕቀፎች በተመለከተ ጥያቄዎችዎን አብረውህ ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር ለመወያየት ጊዜው አሁን ነው ፡፡ አሁን ካጠናኸው ትምህርት አንጻር ምን ልዩ ጥያቄዎች አለህ? ምናልባት ከዚህ በታች ያሉት ጥያቄዎች የራስህን ዝርዝርና ወሳኝ ጥያቄዎችን ለመመስረት ይረዱህ ይሆናል ፡፡ * * በቤተክርስቲያናችሁ ውስጥ “ሚሽን” በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያለህ ተሞክሮ ምን ይመስላል? ሚሽን በአንተ ተሞክሮ ውስጥ እንዴት ተስሏል? * * ሚስዮናውያን አጋጥመውህ ያውቃሉ? የት ያገለግሉ ነበር? ከእነሱ ጋር ጊዜ ባሳለፍከው ጊዜ ያተኩሩባቸው የነበሩ ጉዳዮች ፣ ጭብጦች እና ጽንሰ-ሐሳቦች ምን ዓይነት ነበሩ? ከተሞክሮህ አንፃር ሚስዮናውያን የሚሰሩትን ሥራ እና የሚገፋቸውን ውስጣዊ ዓላማ በተመለከተ ምን ምልከታዎችን አደረግህ? * * ስለ ሚሽን መወያየት መጀመር የሚያስፈልገው ቅዱሳት መጻሕፍት በሚያስተምሩት እንጂ በተለያዩ የሚስዮናውያን ልምምዶች እና ታሪኮች ላይ መሆን የሌለበት ለምንድነው? አብራራ። * * ስለ ሙሉ ጊዜ ሚስዮናዊ አገልጋይነት አስበህ ታውቃለህ? እንደዚያ እንድታስብ ያደረጉህ ነገሮች ምንድናቸው? * * ከዘመን በፊት እስከ ዘመን ባሻገር በሚለው የትምህርት ዝርዝር ውስጥ እንደተቀመጠው የእግዚአብሔርን ታሪክ ያለ ማስታወሻ ምን ያህል ማስታወስ ትችላለህ? ሚሽንን እንደ አሁን ጊዜ የእግዚአብሔር ታሪክ ለማወጅ ማለትም በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እና ሥራ አማካኝነት እንዳለ ድነትና ቤዛነትን ለማጠቃለል እንዲህ ዓይነቱ ረቂቅ ምን ያህል ጠቃሚ ነው? * * የሚከተለውን ዓረፍተ-ነገር አጠናቅቅ - “ከዘመን በፊት እስከ ዘመን ባሻገር ባለው ጊዜ ውስጥ ሚሽንን ከእግዚአብሔር ታሪክ አንጻር ሳስብ በጣም የሚያነሳሳኝና የሚሞግተኝ አንድ ነገር . . . ” * * ማስታወሻዎችን ወይም መጽሐፍ ቅዱስን ሳትጠቀም የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ዘፍጥረት 3.15 ላይ ካለው ከሴቲቱ ዘር ጀምሮ በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ተፈፀመበት ድረስ ያለውን አሳይ፡፡ ከኤደን ገነት አንስቶ ፣ ለሴም ፣ ለአብርሃም ፣ ለይስሐቅ እና ለያዕቆብ ፣ ለይሁዳ ፣ ለዳዊት እና በመጨረሻም ለክርስቶስ የገባውን የእግዚአብሔርን ተስፋ አካትት ፡፡ (እንዴት ነህ? የጥቅስ ማጣቀሻዎችንም ማካተት ችለሃል?) * * ከትልቁ ስዕል አንፃር የእግዚአብሔርን ሥራ የማየት አዝማሚያ አለኝ ወይስ ከእግዚአብሔር ጋር ባለኝ የዕለት ተዕለት ጉዞ በሁኔታዎች ተይዤ እጠፋለሁ? አብራራ ፡፡ በክርስቲያናዊ ጉዞህ ውስጥ ይህ አርቆ የማየት ወይም ቅርብ የማየት ልማድ ከየት ነው የጀመረው?
የተማሪው ትግበራ እና አንድምታዎች
1
Made with FlippingBook - Online catalogs