Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 4 9
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
* እግዚአብሔር ባለፉት መቶ ዘመናት ሲያከናውን ከነበረው ነገር በተቃራኒ በሕይወታችን ውስጥ ምን እየተከናወነ እንዳለ ማየት ሁልጊዜም ቢሆን አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው ? አንድ የሚሽን ራዕይ እና ትኩረት እንዴት እንዲህ ያለ ዳራ ሊሰጠን ይችላል? * የሚከተለውን ዓረፍተ-ነገር አጠናቅቅ: - “እግዚአብሔር በዓለም ውስጥ ዛሬ እያደረገ ስላለው ነገር ያለኝን አመለካከት እንዲሰፋ የረዳኝ አንድ ነገር ... “ ሚሽን ታሪክ እንደ መንገር - የአገልግሎት ሞዴል ቶም ስቴፈን Reconnecting God’s Story to Ministry: Cross-cultural Storytelling At Home and Abroad በተሰኘው አስደናቂ መጽሐፋቸው ውስጥ በወንጌላዊነት እና በደቀመዝሙርነት ስራ ውስጥ ትረካ እና ታሪክ መንገርን ስለለመመለስ አጥብቀው ይሞግታሉ፡፡ እርሳቸው በተለያዩ የሰዎች ቡድኖች መካከል “የታሪክ መሬቶች” ብለው የሰየሟቸውን አካባቢዎች በመለየት ላልተደረሱ ህዝቦችና ለጠፉት የምስራች የማሰማት የቤተክርስቲያን የሚሽን ተግባር ለእግዚአብሔር ታሪክ ታማኝ በመሆንና ለሌሎችና ለራሳችን ታሪኮች ደግሞ ክፍት በመሆን ስለመንገር ይከራከራሉ። በአንድ በተወሰነ የታሪክ መሬት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ለመድረስ ታሪክ ጸሐፊው የመጽሐፍ ቅዱስን ዓውድ ብቻ ሳይሆን ሰዎቹ የሚገኙበትን ጨምሮ የራሳቸውንም መልክዓ ምድራዊ አውድ ማወቅ አለባቸው ፡፡ ”(Tom Steffen, Reconnecting God’s Story to Ministry. La Habra, CA: Center for Organizational and Ministry Development, 1996, p. 15). እያንዳንዳቸው እነዚህ “የታሪክ መሬቶች” በዛሬው ዓለም ውስጥ ሚሽንን ለመፈፀም መሰረቶች እና ወሳኝ ናቸው ብለው ያምናሉ። የሚሽን እና የአገልግሎት ማዕከል የሌሎችንና የራሳችንን ታሪኮች ከእውነተኛው መሠረታዊው የእግዚአብሔር ታሪክ ጋር በማገናኘት ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ እና በእርሱ ስላለው መዳን የሚሉትን መንገር እና መስማት መማር ነው የሚለውን የእርሳቸው አጠቃላይ እይታ እንዴት ታየዋለህ? የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ግለሰባዊ ማድረግ ግን ትንሽ አልበዛም? በዚህ ዘመን ሁሉም ነገር ግለሳብ ተኮር በመሆኑ ምክንያት ክርስትናም የግል ጉዳይ ሆኗል፡፡ ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ቃላት፣ የይገባኛል ጥያቄዎችና ማረጋገጫዎች ከመጠን በላይ በሆነ ግላዊ መንገድ ሲወሰዱ ይታያል እናም ብዙዎች መላውን ክርስትያናዊ ልምምድ “በእኔና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ግንኙነት” እስከማለት ደርሰዋል፡፡ ይህ አዝማሚያ በተለያዩ በርካታ መንገዶች ይታያል፡፡ በአምላኪው ግላዊና ስነልቦናዊ ሁኔታ ላይ ሙሉ በሙሉ ያተኮረው አፈንጋጭ የአምልኮ መዝሙር፣ የግለሰቦችን ችግሮች መፍታት ላይ አጽንኦት የሰጠው የሜጋ ቤተክርሰትያን ክስትት፣ የግለሰቦች የግል ጉዳዮቻቸው እና ችግሮቻቸውን እንዲያሸንፉ ለማገዝ የቀየሱት የፓራ-ቤተክርስቲያን አገልግሎቶች ፍንዳታ እና የብዙዎች ከቤተክርስትያን በጅምላ መኮብለል፡፡ ብዙዎች ዛሬ ቤተክርስቲያንን አባልነት ችላ ብለውታል፤ ቤተክርስቲያን መሄድ አስፈላጊ እንዳልሆነ ወይም ደግሞ አስፈላጊ የሚሆነው የግለሰቦቹን ወይም የቤተሰቦቻቸውን ፍላጎት እስከ ዳሰሰ ብቻ እንደሆነ ያስባሉ፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም ህያው ማህበረሰብ ከመሆን ይልቅ እንደ ሃይማኖታዊ መደብሮች በመሆን ለዚህ አዝማሚያ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ስለ ክርስትያናዊ የ”ፕራይቬታይዜሽን” ልምምድ ምን ታደርጋለህ?
CASE STUDIES
1
1
2
Made with FlippingBook - Online catalogs