Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

5 0 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

ስለ አለም አዳኝ የተሰጠውን የእግዚአብሔር ተስፋ በቀላሉ ግላዊ ማድረግ ይቻላል ወይስ በጣም የተጋነነው ግለሰባዊ ወቅታዊ አዝማሚያ በአዲስ ኪዳንም ሆነ በብሉይ ኪዳን ከ”እግዚአብሔር ሕዝብ” መለየትን ይወክላል?

የክርስቲያን አፈ ታሪኮች ተመልሶ መምጣት ዛሬ ወንጌልን ለጠፋው አለም ለማድረስ ከሁሉ የላቀው ቋንቋ ምንድነው? ጊልፎርድ ዱድሊ 3ኛ የአፈ ታሪክ ቋንቋ መልሰን ልናገኘው የሚገባ ቋንቋ መሆኑን ይከራከራሉ፡፡ ዱድሊ ይህን ቃል የተጠቀሙበት ታሪክ አልባ ስለሆኑት ጣዖታት ሳይሆን ባጠቃላይ ህይወትንና የዓለምን ታሪክ በትዕይንቱ ሊናገር የሚደፍርን ዓይነቱን ታሪክ ነው፡፡ “በአሜሪካ የፕሮቴስታንት እምነት ውስጥ አንድ ታዋቂ ሰው በተደጋጋሚ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በክርስትና መውደቅ ውስጥ በብርሀን መጓዝ ያስፈልጋል፡፡” በተቻለን መጠን ስነ መለኮታዊ ሸክሞቼን ማራገፍ እፈልጋለሁ፡፡ ይህ ቁንጽል አባባል በዚህች ሀገር ውስጥ በፕሮቴስታንት አብተክርስትያናት መካከል እያደገ የመጣውን አመለካከት ያሳያል፡፡ የክርስትና ውድቀት የሚባለውን ነገር በቁጥጥር ስር ለማዋል ካላቸው ቅናት የተነሳ አብያተ ክርስቲያናት እነሱን ዘመናዊ ቀኖናዎች እንዳይሆኑ የማይጣጣሙትን ሁሉንም ጽንሰ ሀሳቦችና ቋንቋዎች ለማስቀረት በከፍተኛ ዝግጁነት ላይ ናቸው፡፡ በጣም በፈቃደኝነት በቀላሉ የተዉት ቋንቋ ምልክት እና አፈታሪክ ነው፡፡ ይህውሳኔ ደግሞ ከባህላችን ጋር እውነተኛ ግንኑነትማድረግ እንዳይችሉ እጅግ አሳሳቢ ጎዳና ላይ ጥሎአቸዋል፡፡ የዘመናዊነትንና የወንጌልን ቋንቋ በመገደብ ባህል በተሳሳተ መንገድ ገምግመዋል። ይህ መጽሐፍ አፈ ታሪካዊው ቋንቋ ምን ያህል አደጋ ላይ እንደወደቀና ምንም እንኳን አብያተክርስትያናት ለመካድ ቢጣደፉም ቋንቋው በባህላች ውስጥ ምን ያህል እየሞተ እንዳለ ያጠናል፡፡ ምንም እንኳን አፈ ታሪካዊ ቋንቋ ከቤተክርስትያን ኦፊሲያላዊ ቋንቋነት የተባረረ ቢመስልም ህያው ለሆነው ኃይሉ ምስክር በሆኑት ዋና የሥነ ጽሁፍ ስራዎች ውስጥ እንደገና ታይቷል፡፡ (GulifordDudley 111,The recovery of chrstian myth.Eugere,OR:Wife and stock publisher ,2004,p.13). ምንም እንኳን በ60ዎቹ መገባደጃ የተጻፈ ቢሆንም፣ የዱድሊ ስራ እምነትን አስመልክቶ የክርስትና “ዋና ቋንቋ” ምስልን፣ አፈ ታሪክን እና ተረትን ለሳይነሳዊ ማብራሪያዎች አሳልፈን እንደሰጠን ይሞግታል፡፡ ስለዱድሊ መከራከሪያ ምን ትችላለህ? የእምነታችንን የግንኙነት መስመር አዕምሮአችን ወደ ለመደው አቅጣጫ መመለስ ክርስቲያናዊው ሚሽን ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ የሚኖረው ይመስልሃል?

3

1

የትምህርቱን ንድፋዊ ሃሳብ በድጋሚ መጻፍ

ሚሽን እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርሰቶስ ሰውነትና ስራ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለሰው ልጆች ሁሉ ያደረገውን ማዳንና ቤዛነት ማወጅ ነው ፡፡

ማጣቀሻዎች

ስለ ክርስቲያን ሚሽን ራእይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ክፍል - 1 ተጨማሪ ሀሳቦችን ለመከታተል ፍላጎት ካለህ እነዚህን መጻሕፍት መመልከት ይረዳህ ይሆናል: Bartholomew, Craig G., and Michael W. Goheen. The Drama of Scripture: Finding Our Place in the Biblical Story . Grand Rapids: Baker Academic Books, 2004. Goldsworthy, Graeme. According to Plan: The Unfolding Revelation of God in the Bible . Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2002.

Made with FlippingBook - Online catalogs