Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 5 1

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

Roberts, Vaughan. God’s Big Picture: Tracing the Story-Line of the Bible. Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2003. -----.Life’s Big Questions: Six Major Themes Traced Through the Bible. Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2005.

የቅዱሳት መጻሕፍትን ጭብጦች እና አመለካከቶች በራስህ ሕይወትና አገልግሎት ላይ ተግባራዊ የማድረግ ችሎታህ እነዚህን ዘይቤዎች ለሌሎች ግልጽ የማድረግ አቅምህን ያሳያል። የቅዱሳት መጻሕፍት ትዕይንት ፣ የእግዚአብሔር ተስፋና በክርስቶስ የተስፋው ፍጻሜ፣ የእውነትና የሕይወት ኃይልን እንደሚሰጥ ለሌሎች ከማወጅህ ወይም ለመጋበዝ ከማሰብህ በፊት መጀመሪያ ለአንተ ነው ፡፡ በእነዚህ እውነቶች ላይ በማሰላሰል በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ ወደምታስበውና ወደምትጸልይበት እውነተኛ ተግባራዊ የአገልግሎት ግንኙነት እንዲመራህ መንፈስ ቅዱስን ጠይቅ ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እግዚአብሔር ትእይንት እንድታስብ ብቻ አይፈልግም፥ ይልቁንም እንድትኖረው ይፈልጋል። በተመመሳሳይ መልኩ እግዚአብሔር ስለ ተስፋውና በኢየሱስ ስለተስፋው ፍጻሜ እንድታነብ ብቻ አይፈልግም፥ ተስፋውን በሙሉ ልብህ እንድትጠይቅም ይፈልጋል ፡፡ በዚህ ሳምንት በእነዚህ እውነቶች ላይ እያሰላሰልክ መንፈስ ቅዱስ እንዲመራህ ራስህን በመስጠት እነዚህን እውነቶች እና ምልከታዎች በሕይወትህ ላይ ተግባራዊ እንዲያደርግ መንፈስ ቅዱስን ጠይቅ ፡፡ እነዚህን እውነቶች በራስህና አብረውህ በሚማሩ ተማሪዎች ህይወት ለመረዳትና ተግባራዊ ለማድረግ ጌታ ብርታት እንዲሰጣችሁ ጸልይ፡፡ ይህን አስታውስ፡- የዚህ ግብ እኛ ራሳችንን በክርስቶስ የተፈጸመው የተስፋ ቃል አካል አድርገን እንድንመለከት ታሪኩ እንዲያስገድደን ነው፡፡ እነዚህን እውነቶች በሕይወትህና በአገልግሎትህ አዲስ ትርጉም እንዲይዝና መጽሐፍ ቅዱስን እኛ የምንተውንበት የእግዚአብሔር የማይታጠፍ ታሪክ እንደሆነ እንድትገነዘብ መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳህ ጸልይ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን የብሉይ ኪዳንን ለክርስቶስ ስራ መዘጋጀትና ሚሽንን እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን የሰጠውን ተስፋ በአዲስ ኪዳን በክርስቶስ የፈጸመበትን አንድነት መረዳት እንድንችል ወደ ትግበራ የእግዚአብሔር ኃሳብ እነዚህን እውነቶች በህይወትህ ህያው እንዲያደርጋቸው ጌታን ጠይቅ፡፡

የአገልግሎት ግንኙነቶች

1

ምክር እና ጸሎት

ASSIGNMENTS

ዕብራውያን 6.17-18

የቃል ጥናት ትውስታ

ለክፍል ለመዘጋጀትና የሚቀጥለውን ሳምንት የምንባብ ምደባ ለማግኘት www.tumi.org/books ን ጎብኝ ወይም መምህርህን ጠይቅ።

የንባብ የቤት ስራ

Made with FlippingBook - Online catalogs