Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 5
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የሞጁሉ (የትምህርቱ) መግቢያ
ኃያል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለእናንተ ይሁን፥
የሚሽን/ተልእኮ ጽንሰ ሃሳብ በከተማ አብያተ ክርስቲያኖቻችን ዘንድ ሊኖረው የሚገባውን ያህል ትኩረት ሲያገኝ አንመለከትም፡፡ ከውቅያኖስ ማዶ ተሻግሮ በሁሉም የዓለም ማዕዘናት ውስጥ እንዳለ ሥራ በስፋት ከተመለከትነው ፣ ለሚሽን የሚገባውን ዓይነት ትንታኔ ለመስጠት አለመቻላችንን እንረዳለን ፡፡ በአንድ በኩል የክርስትና እምነት በጥቅሉ እንደ ተልእኮው ምላሽ ተደርጎ ሊታይ ይችላል፣ ይህም ምላሽ ወደ አሕዛብ ሄዶ የናዝሬቱ የኢየሱስን የእግዚአብሔር መንግሥት ጌትነት እና ንግስና ለማወጅ የተደረገው ጥሪ ምላሽ ተደርጎ ሊታይ ይችላል ፡፡ አዲስ ኪዳን በክርስትና እምነት ውስጥ ፈር ቀዳጅና ዋና ሚስዮናውያን በነበሩ ሐዋርያት ለተመሰረቱት አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠ የሚስዮናዊ ሰነዶች ስብስብ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በክርስቶስ በኩል ወደ ዓለም በመምጣትና ዓለምን ከራሱ ጋር በማስታረቅ የመጀመሪያው ሚስዮናዊ ነው (2 ቆሮ. 5፥18-21)፤ በእርግጥም ክርስትና ተልእኮ ነው ፡፡ በመሆኑም ይህ ሞጁል ከዚህ ቁልፍ ርዕሰ-ጉዳይ ጋር ይዛመዳል ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር የሚሽንን ሥነ-መለኮት እና ጉዳቶቹንም ለመረዳት ይረዳሃል ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የእግዚአብሔርን አጠቃላይ አላማና ተግባር ሳንረዳ እግዚአብሔር በዓለም ውስጥ በሚሽን አማካኝነት ምን እየሰራ እንዳለ ልንረዳ አንችልም። ስለዚህ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ትምህርቶቻችን ሚሽንን በአራት የተለያዩ መነጽሮች እንመለከታለን - ሚሽንን እንደ ትእይንት እና ተስፋ ፣ ሚሽንን እንደ ፍቅር እና ጦርነት በቅደም ተከተል እንመለከታለን ፡፡ የክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት - ክፍል አንድ በተሰኘው የመጀመሪያው ትምህርታችን ውስጥሚሽንን እንደ ዘወትር ድራማወይም ክስተት የሚያየውን ምልከታ እንዳስሳለን ፡፡ እዚህ ላይ ዓላማችን የሚሽንን ተግባር ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር ለመረዳት የሚያስችለውን ማዕቀፍ ለማቅረብ ነው ፡፡ ስለ ሚሽን አጠቃላይ ፍቺ በመስጠት እንጀምራለን ከዚያም ስለ ሚሽን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤ ጠቅለል ያለ ሃሳብ ይዘረዘራል ፡፡ ሚሽን በታሪክ ውስጥ እና በየዘመናቱ እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ለሰው ልጆች ቤዛነትን ለማምጣት የተጠቀመበት መሳሪያ መሆኑን ከቅዱሳት መጻሕፍት በማጣቀስ ሚሽንን በታሪክ እና በድራማ መነፅር እንመለከታለን። የክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት - ክፍል ሁለት በተሰኘው የሁለተኛው ትምህርታችን ውስጥ ደግሞሚሽንን እንደ ዘመናት ፍቅር እና እንደ አመፀኞ ጦርነት እንመረምራለን ፡፡ እነዚህ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙት ምስሎች እንደ አማኞች ለሥነ-መለኮታዊ መረዳታችን ሚሽን ምን ያህል ወሳኝ እንደ ሆነ እንድንመለከት ያስችሉናል ፡፡ እግዚአብሔር ከፍቅሩ የተነሳ ለእርሱ ርስት የሚሆንን ህዝብ ከዓለም ለመጥራት ያለውን የእግዚአብሔርን ቁርጠኝነት እናያለን ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ሚስት ከተሳለው የእስራኤል ታሪክ በመጀመር በጣዖት አምልኮ እና ባለመታዘዝ የሚቀጥለውን የዚህን ታላቅ ታሪክ ዋና ጭብጥ እንገመግማለን ፡፡ ይህንን ጭብጥ በኢየሱስ ማንነት ውስጥ እንመለከታለን ፣ ከዚያም አዲሱ ቃል ኪዳን የእግዚአብሔርን ሰዎች አህዛብን እንዴት እንዳካተተ እንመለከታለን ፡፡ የዘመናት ጦርነትን በተመለከተ ደግሞ በናዝሬቱ በኢየሱስ ሰውነት በኩል የእግዚአብሔርን መንግሥት አገዛዝ መታወጅ እንመለከታለን ፡፡ ከእግዚአብሔር ሉዓላዊነት ግልፅ ማረጋገጫ በመጀመር ፣ እግዚአብሔር በሀጢአት፣ በዲያቢሎስ እና በሰው ልጆች ዓመፅ ከፀጋው የወደቀውን ፍጥረቱን እንደገና ለማቋቋም እንደወሰነ እናያለን ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር
Made with FlippingBook - Online catalogs