Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

6 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

አጽናፈ ዓለሙን በራሱ አገዛዝ ሥር ለማስመለስ የጦረኛ ቦታን ወስዷል። በናዝሬቱ በኢየሱስ ሰውነት አማካኝነት እግዚአብሔር በአጽናፈ ሰማይ ላይ የመግዛት መብቱን እያረጋገጠ ነው ፣ ሚሽኑም/ ተልእኮው ያ መንግሥት ነው ፡ ክርስቲያን ሚሽን እና ከተማ በተሰኘው ሶስተኛው ትምህርት ውስጥ ትኩረታችንን ወደ ሚሽኑ ዓላማ እና እግዚአብሔር ለከተማ እና ለድሆች ወዳለው ዓላማ እናዞራለን ፡፡ ጥንታዊቷን ከተማ ፣ አደረጃጀቷን እና ባህሪያቷን በተለይም በጌታ ላይ የማመፅ ምልክት ምሳሌያዊ ባህሪዋን በመመልከት እንጀምራለን ፡፡ የከተማን መንፈሳዊ ጠቀሜታ እንመለከታለን ፣ እግዚአብሔር በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከበርካታ ከተሞች ጋር ያለውን መስተጋብር በመመልከት ትርጉማቸውን እንመረምራለን ፡፡ እግዚአብሔር የከተማን ፅንሰ-ሀሳብ ለራሱ ዓላማ እንዴት እንደ ተቀበለ ፣ ከአመፅ እና ከጣዖት አምልኮ ጋር ያለውን ትስስር በመሻር ፣ ለሚሽን እና ለወደፊቱ የመንግሥቱ ክብር እንዴት እንደዋጀ እንመለከታለን ፡፡ ስለዚህ በዚህ ትምህርት ውስጥ በከተማሚሽን ውስጥ ለመሳተፋችን ምክንያቶችን እናቀርባለን ፡፡ እንደ ተጽዕኖ ፣ ኃይል እና መንፈሳዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም ለተጨቆኑ ፣ ለተጠቁ እና ለድሆች መሸሸጊያ እንደመሆናችን መጠን እኛ የ 21ኛው ክፍለ ዘመን ደቀመዛሙርት ለከተማው በትንቢታዊ መልክ ለመናገርና ለመኖር መጣር አለብን ፡፡ የመንፈሳዊ መዳረሻችን እና የውርሳችን ሥዕል እና ምልክት እንደመሆኑ መጠን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ባሉ ከተሞች ውስጥ ወንጌልን ለመስበክ ፣ ደቀ መዝሙሮችን ለማፍራት እና አብያተ ክርስቲያናትን ለመትከል የተቻለንን ሁሉ ማድረግ አለብን ፡፡ በመጨረሻም ፣ በክፍል አራት ውስጥ ሌላ የክርስቲያን ሚሽን ወሳኝ አካል እንመለከታለን ፡፡ ክርስቲያን ሚሽን እና ድሆች በተሰኘው ትምህርት ውስጥ ስለ ድሆች እና ሚሽን ፅንሰ-ሀሳብ በበለፀገው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሻሎም ወይም ምሉዕነት ፅንሰ-ሀሳብ መነፅር እንመረምራለን ፡፡ እንደ ያህዌ የቃል ኪዳን ማህበረሰብ ፣ የእስራኤል ህዝብ ድህነትን በፍትህ እና በጽድቅ በሚተካ ለጌታ ቃልኪዳን በእንደዚህ ያለ ታማኝነት እንዲኖሩ ተጠርተዋል። በዘፀአት ወቅት እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብፅ ነፃ በማውጣቱ እውነታ ላይ በመመስረት ለቃል ኪዳን ሕዝቡ የድህነትና የጭቆና ችግርን የሚቀርፍ ንድፍ አውጥቷል ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረዳት ታጥቀን መሲህ እና የቤተክርስቲያን ራስ የሆነው ኢየሱስ ለድሆች ፍትህ እና ሰላም የሚያመጣውን መሲሃዊ ትንቢት እንዴት እንደሚፈጽም እንመለከታለን ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እና የቤተክርስቲያን ራስ እንደመሆኑ መጠን ለእግዚአብሔር ህዝብ እና በሕዝቦቹ በኩል ለዓለም ሰላም/ሻሎም የሆነውን የእግዚአብሔርን ተልእኮ/ሚሽን መግለጹን ቀጥሏል ፡፡ የእግዚአብሔር አዲስ የቃል ኪዳን ማህበረሰብ የሆነችው ቤተክርስቲያን በኢየሱስ በማመን በሰላም ውስጥ እንድትኖርና ለራሷ አባላት እና በዓለም ላሉ የተጨቆኑ ሰዎች የእግዚአብሔርን ፍትህ ለማሳየት ተጠርታለች ፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው በአሁኑ ዘመን ለእግዚአብሔር ህዝብ ኃይልን በሚሰጥና በሚያስታጥቅ መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ አማኞች እንደመሆናችን መጠን እያንዳንዳችንና እያንዳንዱ ጉባኤ ፣ እርሱ ባስቀመጠን ስፍራ የእግዚአብሔርን እውነት በማወጅ እና በመኖር ሌሎችን እንድንዋጅ ነው ፡፡ በእውነት ክርስቲያን መሆን ሚሽን-ተኮር እና ሚሽን ላይ መመስረት ነው ፤ እኛ ከወልድ ጋር ዓለምን የማሸነፍን ሚሽን ከእግዚአብሔር ጋር አብረን እንድንሠራ ከላይ ተወልደናል (ሐዋ ሥራ 9.15) ፡፡ የእግዚአብሔርን አስደናቂ የክብር ታሪክ እና በልጁ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ዓለምን ወደራሱ በመጠቅለል ሚሽን ውስጥ አንተ የራስህን ድርሻ ትወጣ ዘንድ እግዚአብሔር ይህንን ጥናት ይጠቀም ዘንድ እመኛለሁ!

- ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ

Made with FlippingBook - Online catalogs