Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 5 5

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

የክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት - ክፍል 2

ት ም ህ ር ት 2

የትምህርቱ አላማዎች

ኃያል በሆነው በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላም ለአንተ ይሁን! የዚህን ሞጁል (ትምህርት) መጽሐፍ ካነበብክ፣ ካጠናህ፣ ውይይት ካደረግህና ወደ ተግባር ከቀየርክ በኋላ የሚከተሉትን ማድረግ ትችላለህ:- • እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር የገባበትን መለኮታዊ ፍቅር ለመጽሐፍ ቅዱሳዊው ሚሽን እንደ አንዱ ዋነኛ ጭብጥ ማስቀመጥ ትችላለህ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእርሱ የተለየን ህዝብና ከዚያም በክርስቶስ ኢየሱስ ህያው የሆነችውን ቤተክርስቲያን ከአህዛብ መካከል ማውጣቱ ነው፡፡ • በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሙሽራይቱና የሙሽራውን ሃሳብ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ካለው የደስታና የፈንጠዝያ ሀሳብ ጋር ያለውን ዝምድና መዘርዘር ትችላለህ፤ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ስላለው ግንኙነት መሰረታዊ ምስል (በመኃልየ መኃልይ እንደተመከተው) እና ከእስራኤል አሳዛኝ ጅማሮ አንስቶ ባለመታመንዋ እስከመጣባት ፍርድና ስደት ድረስ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ያለው ግንኙነት የጎለበተበትን መንገድ መረዳት ትችላለህ፡፡ • በቂሮስ ትዕዛዝ መሰረት በእዝራ፣ ዘሩባቤልና ነህምያ አማካኝነት የቅሬታዎቹ ወደ ምድራቸው ዳግም መመለሳቸውን በጥልቀት ታያለህ ፤ ግን በመታዘዛቸውና ከማንነታቸው የተነሳ ሳይሆን እርሱ ራሱ ህጉን በልባቸው ስለጻፈውና አዲስን መንፈስ ስለሰጣቸው ነው፡፡ በዋነኝነት ሙሽራ በሙሽራይቱ ደስ እንደሚሰኝ እንዲሁ ህዝቡ ተሃድሶ ሆኖላቸው እግዚአብሔርም በልጁ ደስ መሰኘቱ ነው፡፡ • የአብርሃማዊውን ኪዳንና የአህዛብን መካተት ጨምሮ የተሰጡ ዋና ዋና የብሉይ ኪዳን ተስፋዎችን አስደግፈህ የሙሽራይቱ ምሳሌያዊ ዘይቤ እንዴት በኢየሱስ ፍጻሜ እንዳገኘ ታያለህ፡፡ ኢየሱስ የአዲሲቱ ሙሽራ የቤተክርስቲያን ምንጭና ሕይወት ሆኗል፤ መጥምቁ ዮሐንስ ደግሞ የሙሽራው ወዳጅ፡፡ • አህዛብ ከአይሁድ ጋር አብረው ወራሾች መሆናቸውና በዚያም ምክንያት ወደ አዲሱ የእግዚአብሔር ቤተሰብነትና ወደ ክርስቶስ ሙሽራነት ስለመግባት በሐዋርያነትና በነቢያት የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ሃሳብ ምስጢር ትረዳለህ፡፡ • እንደ ክርስቶስ ሙሽራ ከአህዛብ መካተት ጋር የተያያዙ ዋና ዋና የዶክትሪን ጉዳዮችን የተደረገላቸውን የእምነት ግብዣ ጨምሮ፣ በኢየሩሳሌም ጉባኤ ስለተሰጠው መፍትሄ፣ እነርሱን በኪዳኑ ውስጥ ስለማካተት የኢየሱስ ደም ስላለው ኃይል፣ እንዴት ሐዋርያዊው አገልግሎት የእግዚአብሔርን ህዝብ ለክርስቶስ ነውር እነደሌለባት ሙሽራ እያዘጋጀ እንደሆነ በዝርዝር መመልከት ትችላለህ።

2

Made with FlippingBook - Online catalogs