Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
5 6 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
• በእግዚአብሔርና በክርስቶስ የተለየችውን ሙሽራይቱ እንዲሁም የእርሱ የሆኑትና ከእርሱ ጋር አብረው ወራሽ ለመሆን የተጠሩት ህዝቡ መካከል ስላለው መለኮታዊ ፍቅርና እና የእግዚአብሔርና የህዝቡ መኖሪያ ሰስለሆችው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በጥልቀት ትረዳለህ፡፡ • እግዚአብሔር ከአህዛብ መካከል ለራሱ ህዝብን ለይቶ የማውጣቱን የመለኮታዊ ፍቅር አንድምታ መረዳት ትችላለህ፤ ይህ መጥራት አይሁድንና አህዛብን ሁሉ ያካተተ ነው፡፡ ስለዚህ ሚሽን ማለት እግዚአበሔር ከእርሱ ጋር ለዘላለም የሚኖሩትን የእርሱን መንግስት አባላት ከአይሁድና ከአህዛብ መካከል መጥራቱን መመስከር ነው፡፡ • ሚሽን እንደ ሽፍቶች ጦርነት በሚለው ማዕቀፍ ውስጥ ምናልባትም አስደናቂ የሆነውን የሚሽን ምስል ከቅዱሳት መጽሐፍት ትረዳለህ፤ ይህ ማዕቀፍ በጌታ በኢየሱስ አማካኝነት የእግዚአብሔርን መንግስት አገዛዝ ስለማወጅ ያትታል። • ከቅዱሳት መጻሕፍት ስለ እግዚአብሔር አገዛዝ ግንዛቤ ይኖርሃል፤ ይህም ጌታ እንደ ሁሉ ፈጣሪና አኗሪ ከመሆኑ ተነስቶ የበደል ምስጢር (በሰማያዊው ስፍራ የነበረው ሰይጣናዊ አመጽ)፣ ከዚያም ያስከተለው ፈተና፣ የሰው ልጆች ውድቀትና እርግማን፤ ሆኖም ግን የተጠናቀቀው በሴቲቱ ዘር አማካኝነት የእባቡ ራስ እንደሚቀጠቀጥ እግዚአበሔር በሰጠው የተስፋ ቃል ነው፡፡ በውድቀት ምክንያት ፍጥረት ሁሉ ውጊያ ላይ ነው፤ እግዚአብሔር ደግሞ ተዋጊ ነው፡፡ • እግዚአብሔር በወንዝና በባህር የተመሰለውን ክፉ እንደሚያሸንፍ ተዋጊ መሆኑን፤ ፈርኦንንና ሰራዊቱን ማሸነፉን፤ እንደ ሰራዊት ጌታ ህዝቡን ወደ ድል መምራቱን እና ባለመታዘዛቸውና በአመጻቸው ምክንያት እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር መጣላቱን ጨምሮ እግዚአበሔር በብሉይ ኪዳን እንደ መለኮታዊ ተዋጊ የተገለጠባቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ማስቀመጥ ትችላለህ፡፡ በተጨማሪም የእስራኤል ነብያት እግዚአበሔርን ክፋትን ሁሉ ለዘላለም በመሲሁ በኩል የሚያጠፋ መለኮታዊ ተዋጊ አድርገው እንደሳሉት ትመለከታለህ፡፡ • በዳዊት ሀረግ ውስጥ የመሲሁ የመምጣተ ተስፋ እንዴት እንደተወከለ፣ እግዚአበሔር ለህዝቡ መንግስት የሚመልስን ንጉስ የመስጠት ፍላጎቱን፤ አህዘብን ሁሉ በጽድቅና በፍትህ ማስተዳደር መፈለጉን፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ጌታና ንጉስ እንደሆነ ምድር ሁሉ እንዲያውቅ እግዚአብሔር ያለውን ፍላጎት ማሳየት ትችላለህ፡፡ • ተስፋ የተገባው የእግዚአብሔር አገዛዝ እንዴት አገዛዙን ለመመለስ ከዳዊት ስር በሚወጣው በኢየሱስ ክርሰቶስ ሰውነት በኩል እንደተከፈተ ከቅዱሳት መጻህፍት አንጻር መሞገት ትችላለህ፤ በእርሱና በውልደቱ፤ ትምህርቶቹ፣ ተአምራቱ፣ አጋንንት ማስወጣቱ፣ ተግባራቱ እና ትንሳኤው አማካኝነት የእግዚአብሔር መንግስት አሁን እዚህ ናት፤ በቤተክርስቲያን ህይወት ውስጥ አለች፡፡ • “የእግዚአብሔርን መንግስት መጥቷል ደግሞም ይመጣል” ከሚለው አቅጣጫ ማብራራት ትችላለህ፡፡ ምንም እንኳን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት አማካኝነት በተፈጸመው የመሲሁ ተስፋ የእግዚአብሔር መንግስት የመጣ ቢሆንም በሙላት የሚገለጠው ግን ሁሉ በሚፈጸምበት የኢየሱ ዳግም ምጽአት ነው፡፡ ቤተክርሰቲያን በሰይጣን ላይ የክርስቶስን
2
Made with FlippingBook - Online catalogs