Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

5 8 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

እንደገና እግዚአበሄር እንደ ሙሸራ በህዝቡ ለመደሰት መወሰኑነ እናነባል፡፡

ኢሳ 62፡4 “ከእንግዲህ ወዲህ፦ የተተወች አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፦ ውድማ አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፦ ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም፦ ባል ያገባች ትባላለች።” የጌታ ጽድቅ በሰርግ ላይ እንደ ሙሽራ ያጌጣል-በራሱ ሰርግ ላይ (ኢሳ61፡10) “አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።” የሰማዩ አምላክ ህዝቡን እንደ ሙሽራይቱ ይመለከታል፣እራሱን ደግሞ እንደ ሙሽራዋነ እንደ አፍቃሪዋ፤ በክስቶስና በቤተክርስትያን መካከል ያለውድራማ ተመሳሳይመስል ይሰጣል፤ጌታችን እንደሙሽራውና እንደ ቤተከርሰትያን እንደ ሙሽረይቱ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት ክፍሎች ኢየሱስ ለህዝቡ እንደ ሙሽራ መጠቀሱን ያሳያሉ፡- ማቴ 9፡15 “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።” ዮሐ 3፡29 “ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።” ራዕይ 21፡2 “ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።” ከሁሉ ይልቅ በጣም ግልጽና ቀጥተኛ ዝምድና የምናገኘው እኛ ለdevotion የምንጠቀምበት ክፍል ወስጥ ነው፡፡ ኤፌ 5፡25-27 “ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ።” በዚህ ክፍል መሰረት አንድ ሰው ለሚስቱ ሊኖረው የሚገባው ፍቅር ኢየሱስ ለህዝቡ ያለውን ፍቅር የተከለከለ መሆን ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የሐዋሪያዊው አገልግሎት ግብና ማዕከል የእግዚአብሔርን ህዝብ ለሚመጣው ውህደትና ስነ ስርአት ማዘጋጀት መሆን አለበት፡፡ “በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፤” (2ቆሮ 11:2)፡፡ ክርስቶስ ቤተክርስቲያኑን እየገነባ ነው፤ ከሁሉም ዘመን፣ ቦታና ጊዜ የተሰባሰቡ ቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ፣ እርሱ ለራሱ የገዛቸውና የገሀነም ደጆች እንኳን እስከማይችሏቸው የሚያገለግሉት ናቸው (ማቴ 16፡15-19)። ወደ ሰርግ የታደምን ሁላችን ሙሽራይቱ በሌላ ጊዜ ከምታደርገው በተለየ በሰርግዋ እለት ተሸልማ በመቅረብዋ ውስጥ ያለውን ልዩነት በቀላሉ እንረዳለን። እንዲሁ ደግሞ እግዚአብሔር ለልጁ ሙሽራ

2

Made with FlippingBook - Online catalogs