Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 5 9
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
እያዘጋጀ ነው - ህዝብ ፥ ለዘላለም በእርሱ ቀኝ ተቀምጦ በሚመጣው መንግስት ለዘላለም የሚነግስ መለኮታዊ ጉባኤ ፡፡ ይህ የሚሽንን ሚና ለመረዳት ቀላል ያደርገዋል:- የሚሽን ተግባር በአባቱ የተሰጠው ቁጥር እስኪሞላ ድረስ ነፍሳትን ለክርስቶስ መማመረክ ነው(ዮሐ6፡44)። በቀላል አነጋገር በክርስቶስ አካል ውስጥ ካሉት የእግዚአብሔር ህዝቦች ተለይቶ ድነት ሊኖር አይችልም፡፡ ቤተ ከርስቲያን ከሌለች ክርስትና አይኖርም፥ ድነት አይኖርም፥ ለዚህች አለም ተስፋ አይኖርም፡፡ የታላቁ የላቲን አባት ሳይፕሪያን ዘመናዊ አባባል የበለጠ ግልጽ ያደርገዋል፡- ቤተክርስቲያን እናትህ ካልሆነች እግዚአብሔርም አባትህ አይደለም! አዎ እና አሜን! አማኞች እንደመሆናችን መጠን ከሙሽራችን ጋር የዘላለምን ህይወት እና መንግስቱን ለመካፈል ታጭተናል፤ እርሱም ደግሞ አዳኛችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ስለዚህ እኛ ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማወቅ ያለን መንገድ ከቤተክርሰቲያን የተለየ አይደለም፥ ይልቁንም በኢየሱስ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አባላት መሆናችን ነው፡፡ በሚያሳዝን መልኩ አንዳንድ ሰዎች ለጥምቀታቸው፤ ለሰርጋቸው ወይም ለቀብራቸው ካልሆነ ወደ ቤተክርስቲያን አይመጡም፡፡ በእኔ አመለካከት አንድ ሰው የተለወጠና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክርስቲያን ነኝ ብሎ ካመነ የቤተክርስቲያንን አስፈላጊነት ሊክድ ይችላል ብዬ አላምንም፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰው ግራ የተጋባ ሲከፋ ደግሞ ክርስቲያን ያልሆነ ነው፡፡ ክርስትያን መሆን ማለት የክርስቶስ ሙሸራ አካል እና የመለኮታዊ ፍቅር አካል መሆን ማለት ነው፡፡ እንግዲህ “ሁለቱም አንድ ይሆናሉ” የሚለው ፍጻሜውን የሚያገኘው በዳግም ምጽዓት ቢሆንም ቤተክርስቲያን ግን ይህ ትስስርና ህብረት አሁንም እንዳለ ታውቃለች፡፡ በእውነት ቤተክርሰቲያን ከናዝሬቱ ኢየሱስ ሰውነት ጋር ሙሉ በሙሉ የተገናኘች እና የተዋሃደች ናት፡፡ ሙሉ በሙሉ በኢየሱስ መታወቅንና ከእርሱ ጋር ህብረት ማድረግን እንወዳለን፡፡ እኛ በክርስቶስ አንድ ሆነናል (1ኛ ቆሮ 6፡ 15-17)፥ ወደ እርሱ ተጠምቀናል(1ኛ ቆሮ 12፡13)፥ በመስቀል ላይ ሞቱ አብረነው ሞተናል (ሮሜ 6፡ 3-4)፡፡ በተጨማሪም ወደ ሞት በሆነ ጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል (ሮሜ 6፡3-4)፥ በትንሳኤውም ከእርሱ ጋር ተነስተናል ((ኤፌ 2፡4-7)፥ ከእርሱ ጋር አርገናል (ኤፌ 2፡6)፥ በሰማዊም ስፍራ እርሱ ጋር ተቀምጠናል (ኤፌ 2፡6)፥ ስናገለግለውም በዚህኛውም ህይወት ከእርሱ ጋር እንሰቃያለን (ሮሜ 8፡17-18)፥ በቅርቡም ከእርሱ ጋር እንከብራለን (ሮሜ 8፡17)፥ በእርሱ ውስጥ እንነሳለን (1ኛ ቆሮ 15፡ 8-49)፥ በሚገለጥበት ጊዜ ስናየው እንደ እርሱ እንሆናለን (1ኛ ዮሐ 3፡2)፥ ከዚያም እንደ አብሮ ወራሾች ሁሉንም ነገር ከእርሱ ጋር እንወርሳለን (ሮሜ 8፡17)፥ ደግሞም እንደ አብሮ ገዚዎች በአዲሱ አስተዳደር አብረነው ለዘላለም እንገዛለን (ራዕይ 3፡21)፡፡ በእርግጥ “ሁለቱ አንድ ስጋ ይሆናሉ” የሚለው እንዴት ያለ አስደናቂ ምስጢር ነው! በመንግስቱውስጥ እንደ ክርስቶስ አማኝ ከክርስቶስ ጋር የሚገዛውን ቅዱስ፣ ሐዋርያዊ፣ ቤተክርስትያን፣ የክርስቶስ ሙሽራ፣ የቅዱሳን ህብረት አካል በመሆን ቦታህን ያዝ። የዚህ መለኮታዊ ፍቅር አካል መሆን እንዴት መታደል ነው፡፡ ድግሱ ተዘጋጅቷል፡፡ ራዕይ 19፡6-8 “እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውኃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሃሌ ሉያ፤ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና። የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ። ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል። ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና።” ተዘጋጅተሃል?በዚያ ትገኛለህ?
2
Made with FlippingBook - Online catalogs