Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
6 0 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
የኒቂያ የእምነት መግለጫ እና ጸሎት
የኒቂያን የእምነት መግለጫ (በአባሪው ውስጥ የሚገኝ) ካነበብክ እና/ወይም ከዘመርክ በኋላ የሚከተለውን ጸሎት ጸልይ: ባሪያህን አብርሃምን የመረጥከውና ጥሪህን እንዲታዘዝ ታማኝ ያደረግኸው ፥ አህዛብ ሁሉ በርሱ እንደሚባረኩ በሰጠኸው ተስፋ እንዲደሰት የረዳኸው ሁሉን ቻይ አባት እግዚአብሔር ሆይ ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰጠኸን ተስፋ በእኛ ይፈጸም ዘንድ የጸና እምነት ስጠን። ~ The Church of the Province of South Africa. Minister’s Book for Use With the Holy Eucharist and Morning and Evening Prayer. Braamfontein: Publishing Department of the Church of the Province of South Africa. p. 15
አጭር ፈተና
ማስታወሻዎችህን አስቀምጥ ፣ ሀሳብህን ሰብስበህ የትምህርት 1ን ፈተና ውሰድ ፣ የክርስቲያን ሚሽን ራዕይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት - ክፍል 1
2
የቃል ጥናት ክፍል ቅኝት
ከሌላ ሰው ጋር በመሆን ላለፈው ክፍለ ጊዜ የተመደበውን የቃል ጥናት ክፍል ፃፍ ወይም በቃልህ አንብብ: ዕብ. 6.17-18
የቤት ስራ ማስረከቢያ
ባለፈው ሳምንት ለተሰጠው የንባብ የቤት ስራ መምህርህ የሚጠብቅብህን ዋና ዋና ነጥቦችና ማጠቃለያ አቅርብ (ንባብ ማጠናቀቂያ ገጽ)።
CONTACT
የሙሽራይቱ ምስል ዳግም መነሳት ዛሬ በአንዳንድ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሙሽራዊ ምስላዊ አጠቃቀም በቤተክርስቲያን ህይወትና አምልኮ ውስጥ እንደገና መነሳት ይታያል፡፡ ሆኖም የዚህ ምስል ዳግም መነሳት ለጋራ አካሉ ምስላዊ ገለጻ ሳይሆን የሚሰራው ግለሰቡ ከክርስቶስ ጋር ባለው አካሄድ ነው፡፡ ይህ ምስል የሚሰጠውን ግላዊ ጥብቅ ግንኙነት ለማግኘት አንዳንዱ ጉባኤዎች ጭብጡ የግለሰብ መሆኑን ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ መምህራን ምስሉን እነርሱ ከእግዚአብሔር ጋር ስላላቸው የግል ጉዞ ለማስተማር ይጠቀሙበታል፡፡ የምስጋናና የአምልኮ ዝማሬዎች የሚጻፉት አማኙ ከክርስቶስ ጋር ያለውን ግላዊ ጋብቻ ተመርኩዘው ነው፡፡ በአማኙ ህይወትና አካሄድ ውስጥ ስለዚህ ዋና ሃሳብ ግላዊ አተገባበር ያለህ አመለካከት ምን ይመስላል? ይህ አይነቱ አተገባባር በእግዚአብሔር ልጆች ዘርን መወሰን ሲኖርበት እኛ በግለሰብ ደረጃ ከክርስቶስ ጋር እንደተጋባን አድርገን እየተሳሳትን ይሆን? የክህደት ምስጢር በክርስቲያኑ ማህበረሰብ ዘንድ ስለስልጣናትና ኃይላት ካለው የተጋነነ ግምት የተነሳ በቅዱሳት መጻህፍት ስለተጠቀሱት የጨለማው ኃይላት እንዴት መናገርና ማሰብ እንዳለብን ጥያቄዎች አሉ፡፡ የአጋንንትን አሰራርና አጋንንትን ስለማስወጣት ወይም በነዚህ ጉዳዮች ላይ ስለሚሰጡ መመሪያዎች
1
2
Made with FlippingBook - Online catalogs