Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 6 3

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

• በእግዚአብሔርና በክርስቶስ የተለየችውን ሙሽራይቱ እንዲሁም የእርሱ የሆኑትና ከእርሱ ጋር አብረው ወራሽ ለመሆን የተጠሩት ህዝቡ መካከል ስላለው መለኮታዊ ፍቅርና የእግዚአብሔርና የህዝቡ መኖሪያ ሰስለሆችው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም በጥልቀት ትረዳለህ፡፡ • “የእግዚአብሔር መንግስት መጥቷል ደግሞም ይመጣል” ከሚለው አቅጣጫ ማብራራት ትችላለህ፡፡ ምንም እንኳን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት አማካኝነት በተፈጸመው የመሲሁ ተስፋ የእግዚአበሔር መንግስት የመጣ ቢሆንም በሙላት የሚገለጠው ግን ሁሉ በሚፈጸምበት የኢየሱስ ዳግም ምጽአት ነው፡፡ ቤተክርሰቲያን በሰይጣን ላይ የክርስቶስ ድልና የደረሰበትን እርግማን ለማወጅና ለማሳየት የተሾመች የዛሬይቱ የእግዚአብሔር መንግስት ምልክት እና ቅምሻ ናት፡፡ • ሚሽን እንደ ሽፍቶች ጦርነት የሚለውን ማእቀፍ የሚኖረውን እንድምታ እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ዛሬ በፍጥረታት ላይ ያለውን አገዛዝ ጨምሮ፤ እግዚአበሔር በተቀባው በልጁ በኩል የክፉን ሀይልና የእርግማንን ተጽዕኖ ያሸነፈ ተዋጊ እንደሆነና ሚሽን በዚህ መነጽር ሲታይ እንዴት የእግዚአብሔር መንግስት እዚህና አሁን የመሆኑ ማሳያና አዋጅ መሆኑን ትገነዘባለህ፡፡ አህዛብን ደቀ መዛሙርት ማድረግ ማለት በናዝሬቱ በኢየሱስ ሊመጣ ያለውን የእግዚአበሔር አገዛዝ ማስፋት ማለት ነው፡፡

2

የቪድዮ ሴግመንት 1 ዝርዝር

I. ሚሽን እንደ ዘመናት ፍቅር: - ለዘላለም ለእርሱ የሚሆኑትንና የሚያገለግሉትን ህዝብ ከአህዛብ መካከል ለማውጣት የእግዚአብሔር ውሳኔና ፍላጎት

በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል ያለው ኪዳናዊ አንድነት ክርስቲያንን እና ቤተክርስቲያን በክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመረዳት አዲስ ኪዳን ከብሉይ ኪዳን በእግዚአብሔር እና በሰው ልጆች መካከል ያለውን የቃል ኪዳኑን ጭብጥ ይወስዳል ፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቶስ በእኛ ምትክ በሰራው ሥራ በኩል በሚልቅ ተስፋና በአስተማማኝ መሠረት ላይ በተመሰረተ ቃል ኪዳን ከእርሱ ጋር ህብረት አላቸው ፡፡ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ለመግለጽ አንዳንድ ነብያት የተጠቀሙበት የጋብቻ ምስል በአዲስ ኪዳን ተወስዶ ለክርስቶስ (ሙሽራው) እና ለቤተክርስቲያን (ሙሽራይቱ) ተተግብሯል ፡፡ ይህ የቃልኪዳን አንድነትን ምንነት እንደ አንድ የጋራ ፍቅር ፣ መከባበር ፣ መተማመን እና ታማኝነትን አጉልቶ ያሳያል። (ሌሎች የቤተሰብ ግንኙነት ሥዕሎች እንደ አባት/ልጅ እና እንደ ታላቅ ወንድም እና ሌሎች ልጆችም ጥቅም ላይ ውለዋል)። ከሌሎች ይልቅ በተለይም ፒዩሪታኖች ይህንን ጭብጥ ይወድዳሉ ፡፡ ~ J. P. Baker. “Union With Christ.” The New Dictionary of Theology. S. B. Ferguson, ed. (electronic ed.) Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2000. p. 698.

Made with FlippingBook - Online catalogs