Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
6 2 /
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
ጋር መደሰቱ ነው። የአብርሃማዊውን ኪዳንና የአህዛብን መካተት ጨምሮ የተሰጡ ዋና ዋና የብሉይ ኪዳን ተስፋዎችና የሙሽራይቱ ምሳሌያዊ ዘይቤ በኢየሱስ ፍጻሜ አግኝቷል፡፡ ኢየሱስ የአዲሲቱ ሙሽራ የቤተክርስትያን ምንጭና ሕይወት ሆኗል፤ መጥምቁ ዮሃንስ ደግሞ የሙሽራ ወዳጅ፡፡ አህዛብ ከአይሁድ ጋር አብረው ወራሽ መሆናቸውና በዚያም ምክኒያት ወደ አዲሱ የእግዚአብሔር ቤተሰብነትና ወደ ክርስቶስ ሙሽራነት ስለመግባት በሐዋርያትና በነቢያት የተገለጠው የእግዚአብሔር ሀሳብ ሚስጥር ተገልጧል፡፡ በእግዚአብሔርና በክርስቶስ በተለየችው ሙሽራይቱ እንዲሁም የእርሱ በሆኑትና ከእርሱ ጋር አብረው ወራሽ ለመሆን በተጠሩት ህዝቡ መካከል ያለው መለኮታዊ ፍቅር ሙላቱን የሚያገኘው የእግዚአብሔርና የህዝቡ መኖሪያ የሆችው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከሰማይ በምትወርድበት ወቅት ነው፡፡ የዚህ ሚሽን እንደ ዘመናት ፍቅር የተሰኘ ሴግመንት አላማ የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት ትችል ዘንድ ነው: • እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር የገባበትን መለኮታዊ ፍቅር ለመጽሐፍ ቅዱሳዊው ሚሽን እንደ አንዱ ዋነኛ ጭብጥ መሆኑን፤ ይህም እግዚአብሔር ለእርሱ የተለየን ህዝብና፤ ከዚያም በክርስቶስ ኢየሱስ ህያው የሆነችውን ቤተክርስትያን ከአህዛብ መካከል ማውጣቱ ነው፡፡ • በብሉይ ኪዳን ውስጥ የሙሽራይቱና የሙሽራውን ሃሳብ በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ካለው የደስታና የፈንጠዝያ ሀሳብ ጋር ያለውን ዝምድና ፤ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ስላለው ግንኙነት መሰረታዊ ምስል (በመኃልየ መኃልይ እንደተመከተው) እና ከእስራኤል አሳዛኝ ጅማሮ አንስቶ ባለመታመንዋ እስከመጣባት ፍርድና ስደት ደረስ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ያለው ግንኙነት የጎለበተበትን መንገድ መረዳት ትችላለህ፡፡ • በቂሮስ ትዕዛዝ መሰረት በእዝራ፣ ዘሩባቤልና ነህምያ አማካኝነት የቅሬታዎቹ ወደ ምድራቸው ዳግም መመለሳቸውን በጥልቀት ታያለህ ፤ ነገር ግን በመታዘዛቸውና ከማንነታቸው የተነሳ ሳይሆን እርሱ ራሱ ህጉን በልባቸው ስለጻፈውና አዲስን መንፈስ ስለሰጣቸው ነው፡፡ በዋነኝነት ሙሽራ በሙሽራይቱ ደስ እንደሚሰኝ እንዲሁ ህዝቡ ተሃድሶ ሆኖላቸው እግዚአብሔርም በልጁ ደስ መሰኘቱ ነው፡፡ • የአብርሃማዊውን ኪዳንና የአህዛብን መካተት ጨምሮ የተሰጡ ዋና ዋና የብሉይ ኪዳን ተስፋዎችን አስደግፈህ የሙሽራይቱ ምሳሌያዊ ዘይቤ እንዴት በኢየሱስ ፍጻሜ እንዳገኘ ታያለህ፡፡ ኢየሱስ የአዲሲቱ ሙሽራ የቤተክርስትያን ምንጭና ሕይወት ሆኗል፤ መጥምቁ ዮሃንስ ደግሞ የሙሽራ ወዳጅ፡፡ • አህዛብ ከአይሁድ ጋር አብረው ወራሽ መሆናቸውና በዚያም ምክንያት ወደ አዲሱ የእግዚአብሔር ቤተሰብነትና ወደ ክርስቶስ ሙሽራነት ስለመግባት በሐዋርያትና በነቢያት የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ሃሳብ ምስጢር ትረዳለህ፡፡ • እንደ ክርስቶስ ሙሽራ ከአህዛብ መካተት ጋር የተያያዙ ዋና ዋና የዶክትሪን ጉዳዮችን የተደረገላቸውን የእምነት ግብዣ ጨምሮ፣ በኢየሩሳሌም ጉባኤ ስለተሰጠው መፍትሄ፣ እነርሱን በኪዳኑ ውስጥ ስለማካተት፣ የኢየሱስ ደም ስላለው ኃይል ፣ እንዴት ሐዋርያዊ አገልግሎት የእግዚአብሔርን ህዝብ ለክርስቶስ ነውር እንደሌለባት ሙሽራ እያዘጋጀ እንደሆነ በዝርዝር መመልከት ትችላለህ።
2
Made with FlippingBook - Online catalogs