Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook
/ 7 5
የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች
እባክህ በነዚህና በሌሎችም በዚህ ቪዲዮ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ጊዜ ወስደህ ምላሽ ለመስጠት ሞክር፡፡ በዚህ ሴግመንት ሚሽን እንደ ዘመናት ፍቅር እግዚአብሔር ለእርሱ ይሆኑና ያገለግሉት ዘንድ የተለየን ህዝብ ከአህዛብ መካከል ስለማውጣቱ እናያለን፡፡ እዚህ ጋር አህዛብ ከአይሁድ ጋር አብረው ወራሽ መሆናቸውና በዚያም ምክኒያት ወደ አዲሱ የእግዚአብሔር ቤተሰብነትና ወደ ክርስቶስ ሙሽራነት ስለመግባት በሐዋርያትና በነቢያት የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ሃሳብ ምስጢር እንረዳለን፡፡ ስለዚህ ሚሽን ማለት እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ለዘላለም የሚኖሩትን የእርሱን መንግስት አባላት ከአይሁድና ከአህዛብ መካከል መጥራቱን መመስከር ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ሞጁል(ትምህርት) ሚሽንን ለማከናወን የሚያስፈልጉትን በዚህ ክፍል ውስጥ የተካተቱ ዋና ዋና ሃሳቦች ለመቃኘት ሞክር፡፡ መልሶችህን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አስደግፍ፡፡ 1. ሚሽን እንደ ዘመናት ፍቅር የተሰኘውን ጭብጥ በአጭሩ ግለጽ፡፡ በእግዚአብሔር እና በሕዝቦቹ መካከል ያለው የመለኮታዊ የፍቅር ዘይቤ እግዚአብሔር ለራሱ እና ለዓለሙ ያለውን ቁርጠኝነት እንዴት ያሳያል? አብራራ፡፡ 2. በብሉይ ኪዳን ውስጥ የተገለጸውን የሙሽራይቱና የሙሽራውን ሃሳብ ተንተርሰህ መልስ፡፡ ይህ ምስል ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ግንኙነት ጋር የሚዛመደው በምን መልኩ ነው? መሃልየ መሃልይ ከዚህ ጭብጥ ጋር እንዴት ይዛመዳል? 3. በያህዌ እና በሕዝቡ መካከል “የፍቅር ግንኙነት” ከየት ይጀምራል? በእግዚአብሔር ቸርነት ምርጫ ፣ መጠናናት እና ከእርሷ ጋር ጋብቻ ላይ በመመስረት በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ በእስራኤል መካከል ያለው ግንኙነት በምን መንገድ ላይ የተመሠረተ ነበር? 4. በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት እምነት የለሿ እስራኤል በጌታ ላይ “ምንዝር” የሠራችው እንዴት ነበር? በእምነት ማጣትዋ ምክንያት እግዚአብሔር ምን አደረገ? በሰሜኑም ሆነ በደቡባዊ መንግስታት ላይ ምን ተጽዕኖ አሳደረ? 5. የእግዚአብሔር ሕዝቦች ወደ ምድራቸው መመለስ በማን ዓለማዊ ገዥ ስር ተጀመረ? ቅጥሩን እንደገና ለመገንባት ቅሬታዎቹን ወደ እስራኤል የመለሷቸው የሕዝቡ መሪዎች እነማን ናቸው? ለአዲስ ኪዳን የእግዚአብሔር ቃል ምን ዓይነት እና በምን ላይ የተመሠረተ ነበር? አዲሱ ቃል ኪዳን ከፀደቀ በኋላ ለእግዚአብሔር እና ለሕዝቡ ምን ውጤት ያስገኛል? 6. በመጪው የጌታ ማዳን አሕዛብ ቦታ እንደሚኖራቸው በብሉይ ኪዳን ከተሰጡት በጣም ግልፅ የሆኑ “ፍንጮች” ጥቂቶችን ዘርዝር። የሙሽራይቱ - ሙሽራው ዘይቤ በኢየሱስ እና ከህዝቡ ፣ ከቤተክርስቲያኑ ጋር ባለው ግንኙነት እንዴት ይዛመዳል እና ይፈጸማል? በዚህ ግንኙነት ውስጥ የመጥምቁ ዮሐንስ ሚና ምን ነበር? 7. ስለ እግዚአብሔር ሰዎችሙሽርነት በሐዋርያትና በነቢያት የተገለጠውምስጢር ምንድነው? እንደ ክርስቶስ ሙሽራ አባላት ስለ አማኝ አሕዛብ ምን ማለት እንችላለን? የኢየሩሳሌም ጉባኤ የአሕዛብን የክርስቶስ የአካልነትና የሙሽርነት ቦታን ያጠናከረው እንዴት ነው? አሁንስ ስለ ሁሉም ሐዋርያዊ አገልግሎት ባህሪ ምን ማለት ይቻላል? 8. በእግዚአብሔር እና በሕዝቡ መካከል ያለው መለኮታዊ ፍቅር መቼ እና የት ይጠናቀቃል? የሙሽራው አባላት የሆኑት በመጪው የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ስለሚኖራቸው ከፍተኛ ደረጃ እና ሚና ምን ተስፋ አላቸው?
መሸጋገሪያ 1
የተማሪው ጥያቄዎች እና ምላሽ
2
Made with FlippingBook - Online catalogs