Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

7 6 /

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

9. የዚህ የሚሽን እንደ ዘመናት ፍቅር ጭብጥ ዋና ዋና አንድምታዎች ምንድናቸው? እግዚአብሔር አህዛብን ከመረጠበት ከዚህ መልእክት ጋር በተያያዘ ሚሽን ምን ማድረግ ይፈልጋል?

የክርስቲያን ሚሽን ራእይ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት: ክፍል 2 ሴግመንት 2: ሚሽን እንደ ሽፍቶች ጦርነት

ቄስ ዶ/ር ዶን ኤል ዴቪስ

የሴግመንት 2 ማጠቃለያ

ሚሽን እንደ ዘመናት ፍቅር የተሰኘውጭብጥ ምናልባትም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ካሉት የሚሽን ጭብጦች በጣም ትልቁ የሚሽን ምስል ነው፤ ይህም የሁሉ ፈጣሪ እና ደጋፊ በሆነው የያህዌ አምላክ ሉዓላዊ አገዛዝ ይጀምራል። የእግዚአብሔር አገዛዝ በክፋት ምስጢራዊ አመፅ (በመንግስተ ሰማያት ውስጥ በተካሄደው የሰይጣን አመፅ) ተቃውሞ ደርሶበታል ፤ ይህም የሰው ልጅ ፈተና እና ውድቀት እና የፍጥረት እርግማን አስከተለ ፡፡ እግዚአብሔር በሴቲቱ ዘር እና በእባቡ መካከል ጠላትነትን ያስቀመጠ ሲሆን በሴቲቱ ዘር በኩል አመፅን በሉዓላዊነቱ ለማስቆም ቃል ገባ ፡፡ በውድቀት ምክንያት ፍጥረት ሁሉ በጦርነት ላይ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእባቡ እና አብረውት ከሚገኙት ጋር በጦርነት ላይ መሆኑን አውጇል፡፡ እግዚአብሔር ከወንዝ እና ከባህር ፣ ከፈርዖን እና ከሠራዊቱ እንዲሁም ከከነዓን አሕዛብ ጋር በተዛመደ ከክፋት ጋር በተደረገው ውጊያ ራሱን እንደ መለኮታዊ ተዋጊ አድርጎ አሳይቷል ፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ባለመታዘዛቸውና በእግዚአብሔር ላይ በማመጻቸው ምክንያት እግዚአብሔር ከገዛ ህዝቡ ጋር ተዋግቷል። በተጨማሪም ፣ የእስራኤል ነቢያት በመሲሑ አማካይነት እግዚአብሔርን በመጨረሻ ክፉን ሁሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚያጠፋመለኮታዊ ተዋጊ አድርገውስለውታል፡፡ ይህ መሲሐዊ አገዛዝ በኢየሱስ ማንነት ተከፍቷል፤ ውልደቱ ፣ ትምህርቶቹ፣ ተአምራቱ፣ አጋንንት ማስወጣቱ፣ ስራዎቹ፣ ሞቱ እና ትንሳኤው የእግዚአብሔርን መንግሥት ያስገኙ ናቸው ፡፡ መንግሥቱ “መጥቷል” ደግሞም “ገና ይመጣል” ፣ በኢየሱስ መሲሐዊው ተስፋ ሲፈጽም ተፈጽሟል ነገር ግን በዳግም ምጽአቱ ይጠናቀቃል፡፡ ዛሬ በዚህ ዓለም እና በእኛ ዘመን ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የሙሉ ውርስ ቃል ኪዳን በመሆኗ የመንግሥቱ ምልክት እና ቅምሻ ናት፡፡ ቤተክርሰቲያን በሰይጣን ላይ የክርስቶስ ድልና የደረሰበትን እርግማን ለማወጅና ለማሳየት የተሾመች የዛሬይቱ የእግዚአብሔር መንግስት ምልክት እና ቅምሻ ናት፡፡ ሚሽን እግዚአብሔር በአሁኑ ጊዜ በፍጥረታት ሁሉ ላይ በኢየሱስ ክርስቶስ እና እንዲሁም በወኪሉ በቤተክርስቲያኑ በኩል ስላለው አገዛዝ እያረጋገጠ መሆኑን ማወጅ ነው፡፡ የዚህ “ሚሽን እንደ ዘመናት ፍቅር” የተሰኘው ሴግመንት አላማ የሚከተሉትን ነጥቦች መመልከት ትችል ዘንድ ነው፥

2

Made with FlippingBook - Online catalogs