Foundations for Christian Mission, Amharic Student Workbook

/ 7 7

የ ክ ር ስ ቲ ያ ን ሚ ሽ ን መ ሰ ረ ቶ ች

• ሚሽን እንደ ዘመናት ፍቅር የተሰኘው ጭብጥ ምናልባትም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ካሉት የሚሽን ጭብጦች በጣም ትልቁ የሚሽን ምስል ነው፤ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት አማካኝነት የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ አገዛዝ ይዳስሳል። • በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያለው የጦርነት ዘይቤ አጭር ቅኝት በያህዌ የሁሉም ፈጣሪነት እና ደጋፊነት ይጀምራል ፡፡ በጥንት እና በሩቅ ጊዜ የክፋት ምስጢር ተከስቷል (በሰማያዊው ስፍራ የነበረው ሰይጣናዊ አመጽ)፣ ከዚያም ያስከተለው ፈተና፣ የሰው ልጆች ውድቀትና እርግማን፤ ሆኖም ግን የተጠናቀቀው በሴቲቱ ዘር አማካኝነት የእባቡ እራስ እንደሚቀጠቀጥ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል ነው፡፡ በውድቀት ምክንያት ፍጥረት ሁሉ በጦርነት ላይ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእባቡ እና አብረውት ከሚገኙት ጋር በጦርነት ላይ መሆኑን አውጇል፡፡ • እግዚአብሔር ከወንዝ እና ከባህር ፣ ከፈርዖን እና ከሠራዊቱ እንዲሁም ከከነዓን አሕዛብ ጋር በተዛመደ ከክፋት ጋር በተደረገው ውጊያ ራሱን እንደ መለኮታዊ ተዋጊ አድርጎ አሳይቷል ፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ ባለመታዘዛቸውና በእግዚአብሔር ላይ በማመጻቸው ምክንያት እግዚአብሔር ከገዛ ህዝቡ ጋር ተዋግቷል። • በዳዊት ሀረግውስጥ የመሲሁ የመምጣትተስፋ እግዚአብሔር ለህዝቡመንግስት የሚመልስን ንጉስ የመስጠት ፍላጎቱን አህዘብን ሁሉ በጽድቅና በፍትህ ማስተዳደር መፈለጉን እንዲሁም እግዚአብሔር ጌታና ንጉስ እንደሆነ እንዲሁም ምድር ሁሉ እንዲያውቁት እግዚአብሔር ያለውን ፍላጎት ማየት ትችል ዘንድ ነው፡፡ • የእስራኤል ነቢያት በመሲሑ አማካይነት እግዚአብሔርን በመጨረሻ ክፉን ሁሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚያጠፋ መለኮታዊ ተዋጊ አድርገው ስለውታል፡፡ ይህ መሲሐዊ አገዛዝ በኢየሱስ ማንነት ተከፍቷል ፤ ውልደቱ ፣ ትምህርቶቹ፣ ተአምራቱ፣ አጋንንት ማስወጣቱ፣ስራዎቹ ሞቱ እና ትንሳኤው የእግዚአብሔርን መንግሥት ያስገኙ ናቸው ፡፡ መንግሥቱ “መጥቷል” ደግሞም “ገና ይመጣል” ፣ በኢየሱስ መሲሐዊው ተስፋ ሲፈጽም ተፈጽሟል ነገር ግን በዳግም ምጽአቱ ይጠናቀቃል፡፡ • ዛሬ በዚህ ዓለም እና በእኛ ዘመን ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ፣ የሙሉ ውርስ ቃል ኪዳን በመሆኗ የመንግሥቱ ምልክት እና ቅምሻ ናት፡፡ ቤተክርሰቲያን በሰይጣን ላይ የክርስቶስ ድልና የደረሰበትን እርግማን ለማወጅና ለማሳየት የተሾመች የዛሬይቱ የእግዚአብሔር መንግሥት ምልክት እና ቅምሻ ናት፡፡ • ሚሽን እንደ ሽፍቶች ጦርነት የሚለውን ማእቀፍ የሚኖረውን እንድምታ እግዚአብሔር በክርሰቶስ ኢየሱስ በኩል ዛሬ በፍጥረታት ላይ ያለውን አገዛዝ ጨምሮ፤ እግዚአብሔር በተቀባው በልጁ በኩል የክፉን ሀይልና የእርግማንን ተጽዕኖ ያሸነፈ ተዋጊ እንደሆነና ሚሽን በዚህ መነጽር ሲታይ እንዴት የእግዚአብሔር መንግስት እዚህና አሁን የመሆኑ ማሳያና አዋጅ ነው፡፡ አህዛብን ደቀ መዛሙርት ማድረግ ማለት በናዝሬቱ በኢየሱስ ሊመጣ ያለውን የእግዚአብሔር አገዛዝ ማስፋት ማለት ነው፡፡ ሚሽን እግዚአብሔር በአሁኑ ጊዜ በፍጥረታት ሁሉ ላይ በኢየሱስ ክርስቶስ እና እንዲሁም በወኪሉ በቤተክርስቲያኑ በኩል ስላለው አገዛዝ እያረጋገጠ መሆኑን ማወጅ ነው፡፡

2

Made with FlippingBook - Online catalogs